Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 13896
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by Abere » 15 Nov 2022, 09:42

እንደተረዳሁት ከሆነ ይህን የጻፈው ሰው እራሱ አሉቧልታ የሚዘራ እንጅ ስንጥር መረጃ እንኳን ሰብስቦ መሰነድ አልቻለም። ይህን ትችት የሰነዘረው ግለሰብ ስለተጻፈ ብቻ በልማድ ሳይንሳዊ ይሆናል ሰዎችም ይቀበሉታ ብሎ በመገመት አማራን ኢላማ ያደረገ እና ያተኮረ ልብወለድ ነው። ጎሳ ላይ ያነጣጠሩ እንድህ አይነት ፍረጃዎች ከወያኔ ጋር አብረው የተወለዱ ቀድመ ወያኔ ያልነበሩ ነገሮች ናቸው። የጋርዮሽ ማህበረዊ ንቃተ-ህሌና ወይም አገራዊ የጋርዮሽ እሴት አስተሳሰብ የሆነ ሁሉ የአንድ ጎሳ የማድረግ እና ያንን ጎሳ የማጥላላት የመክሰስ እና የመወንጀል ስራዎች የወያኔዎች ገጸ ባህርይ እና መሪ ሃሳብ ነው። ይህን ኦነጎችም ይጋሩታል- በመጀመሪይ ይህ የፈጠራ ስራ ዋና አላማም ኦነጎች ዋና የሸቀጠ-ሃሳቡ ፍጆታ ገዥዎች ናቸው በሚል ስሌት ነው። የፈጠሩት ገጸባህርይ ስህተት እንደ ሆነ ወያኔዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ። በአጭሩ ዝንብ ፈጥረው ንብ ናት በማለት ያልነቃ እና የዋህ ዝብ ማታለል ነው። የአገራችን ሰው ሞኝ ነው። የተጻፈ ያምናል። አንድ ቃልቻ ወይ ቄስ ይህ ከአጋንንት ይጠብቅሃል ብሎ ወረቀት ተብትቦ በአንገትህ ያዝበት ቢለው በእውነትም ያድናል ብሎ በቡትቶ ጨርቅ ወረቀት በአንገቱ ተሸክሞ ይኖራል። ታዲያ አስኮላ ትምህርት የተማረ ውሸት ከተረከለት እንደት አይቀበል?!

አንዱ አፍቃሪ ወያኔዎች አምባገግ ውሸት እና የአማራ ጥላቻቸው አንድ ሺ አንድ ጥላቻ አዘል ውሸት በአማራ ላይ ሲተርኩ አንድት እንኳን ጥሩ ነገር ይህን አበርክቷል ብለው ሲናገሩ ተደምጠው አያውቁም። በኢትዮጵያ በጎሳ ላይ ይጠነጠነ ገጸባህርያት ሙሉ በሙሉ የተፋለሰ እና የተሳሳተ ነው። ቅድመ-ወያኔ የነበረው ማህበራዊ እሳቤ የጋርዮሽ እንጅ የጎሳ ፍልስፍና አይደለም። አንድ ነገርን ለህዝብ ለማቅረብ የሚዳሰስ ማስረጃ ወይም እሙን ሰነድ ያስፈልጋል።


Meleket wrote:
15 Nov 2022, 07:49
የኣጼ ሱስንዮስን ኣሟሟት እንዲሁም ስለ ልጃቸው ኣጼ ፋሲል የተፈበረኩ "የገጽታ ገደላ" ትርክቶች በተመለከተ ያሰመርንበትን ክፍል ብታነቡት ለግንዛቤ ይረዳችኋል . . . "ግዮናዊነት" ከሚል ጽሑፍ የተቀነጨበ ነው። :mrgreen:
Meleket wrote:
07 Nov 2022, 10:53
ቢያነቡት ዕውቀት ከመገብዬት ሌላ የሚከስሩት ነገር የለም። ለትንታኔው ምስጋናው አንዱዓለምን አመስግነናል። :mrgreen:
ሰብእና ገደላ (ገጽታ ገደላ) _ የምስጋናው አንዱዓለም እዪታ

የተቃዋሚ ዋና መሳሪያ የሆነው ሰብእና ገደላ በዚህ የአማራነት እንቅስቃሴ ውስጥ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ነው፡፡ ብዙዎችን ደህና ሰዎች ደጋግሞ እያደናቀፈ አላሰራ ያለ፡፡ ሰብእና ገደላ፤ ወይም ገጽታ ገደላ፡፡ ሰብእና (ገጽታ) ገደላ በተለይ በፖለቲካው ዓለም የፖለቲካ ተቋማትን እድሜ የሚተካከል ነው፡፡ ይሄ ዘዴ ሰውን ከስራው ለማደናቀፍ፣ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነቱ እንዲሳሳ፣ ትግሉን ተስፋ ቆርጦ እንዲተው፣ ሞራሉ እንዲነካ እና ሁለተኛ አያሳየኝ ብሎ ከሚወደው ስራው ወይም ህዝብ እንዲነጠል ማድረጊያ ስልት ነው፡፡

ገጽታ ገደላ የደካሞች መሳሪያ ነው፡፡ በአካል የማይገድሉትን በምላሳቸው ይገድሉታል፡፡ በተግባርና በሀሳብ የላቃቸውን በአሉባልታና ሀሜት ሊያወርዱት ይሞክራሉ፡፡ ጀግናውን ፈሪ ያደርጉታል፡፡ ሰውን አውሬ ያስመስሉታል፡፡
በታሪካችን ከሚታወቁት ገጽታ ገደላዎች አንዱ አጼ ቴዎድሮስ ላይ የደረሰው ነው፡፡ አጼ ቴዎድሮስን በምላስ ለማሸማቀቅ “የኮሶ ሻጭ ልጅ” አሏቸው፡፡ እስካሁን የካሳ እናት ኮሶ ስለመሸጣቸው በአራት ነጥብ የደመደመ የታሪክ ምስክር የለም፡፡ ቢሆን እንኳ የእናቱ ኮሶ መሸጥ በምንም መልኩ ካሳን ሊገድለው አይችልም ነበር፡፡ አይሻል፣ ጉራምባና ሌሎችም የጦር አውድማዎች ላይ ያንበረከካቸው በኮሶ ማውራ (ዋንጫ/ቅል) ሳይሆን በጦርና በጎራዴ ነበር፡፡ ደካሞች ጦርና ጎራዴን በክንዳቸው መግጠም ሲያቅታቸው በምላሳቸው የኮሶ ማውራን ገጠሙት፡፡

አጼ ፋሲል ሰውነቱ ሁሉ ጸጉር ነው፣ ሴት አብሮ አሳድሮ ያንን እንዳትናገርበት ወደውሀ ይጥል ነበር፣ ለዛ ንስሀ ነው ሰባት ድልድይ እና 44 አብያተ ክርስቲያናት ያሰራው ይሉት ነበር፡፡ ይህ ገጽታ ገደላ ነው፡፡ ንጉሱ ሰው አልነበሩም ወይም የተለዩ ፍጥረት ነበሩ ለማለት ነው፡፡ ያሰሩት ያ ሁሉ የስልጣኔ አሻራ ከንጉሱ ረቂቅ አእምሮ የመነጨ እቅድ እና ፍላጎት እንዳልሆነ በመናገር ስራውን ሲያዳፍኑት ነው፡፡ የጎንደርን ስልጣኔ የዝሙት ንስሀ ፍሬ ሲያደርጉት ነው፡፡ የፋሲል አባት አጼ ሱስንዮስ ብርቱው ጦረኛ ዜና መዋእሉ እንደሚያስረዳው ለ28 አመታት ያለረፍት የተዋጋ ሰው ነው፡፡ ሰበቡ ምንም ሀይማኖት ቢሆንም ቅሉ ምላሱ ተጎልጉሎ ሞተ እየተባለ ነው አሙሟቱ እንኳ የሰው እንዳልሆነ ሲነገር የቆየው፡፡ ያ ሁሉ የዋለው ውለታ በሀይማኖት ባለመስማማቱ ብቻ በምላስ መጎልጎል መሞት ብቻ ነው የተዘጋው፡፡ አጼ ምኒልክን የተፈጥሮ ጥበባቸውንና የመሪነት “ካሪዝማቸውን” ለመካድ ስንት እና ስንት ነገር ይሏቸው ነበር፡፡ አሉላ አባ ነጋን በአጼ ዮሐንስ ዙሪያ የተሰባሰቡ ምላሰኞች “ወዲ ቁቢ” ወይም የደሀ/ገበሬ ልጅ እያሉ እስከማሳሰርና ማሻርም ደርሰው ነበር፡፡ አጼ ሀይለ ስላሴን የንጉሱን ጥበብና ማስተዋል ለመካድ ሲባል ቆሪጥ ምናምን እያሉ ስሙን የሚያጠፉበትም ምክንያት ያው የገጽታ ገደላ ስራ ነው፡፡ ልጅ ኢያሱ ያ ሁሉ ያደረገውንም ያላደረገውም ተጠቅሞ ስሙን በማጉደፍ ከጨዋታ ውጭ የተደረገው በዚሁ በገጽታ ገደላ ስራ ነው፡፡ ልጅ ኢያሱ በወቅቱ ከጀርመንና ቱርክ ጋር ወዳጅነት መመስረቱ ያንገበገባቸው እንግሊዝና ፈረንሳዮች ሴራ ሸረቡበት የሚሉም አሉ፡፡ እንግሊዞች በተለይ ከሱማሌ ሴቶች ጋር ሆኖ የሚያሳይ የሀሰት የፎቶ ቅንብር ግብጽ ውስጥ በ20 ሽህ ኮፒ አባዝተው አምጥተው በተኑ የሚሉ አሉ፡፡ ወግ አጥባቂው የወቅቱ ህዝብም ልጅ ኢያሱን ተቀየመ፡፡ የተባለውን ነገር ልጅ ኢያሱ አድርጎ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ለዛ የሚያበቃው አልነበረም፡፡ ያው ገጽታ ገዳዮች ከባዶ ነገር ገጽታ መግደያ ንጥረ ነገር የሚቀምሙትን ያህል ከትንሽ እውነት ላይ ተራራ የሚያክል ገጽታ ገዳይ ቁልል ይፈጥራሉ ለማለት ነው፡፡

ገጽታ ገደላ የነፍስያ ገደላ ምዕራፍ አንድ ነው፡፡ ገጽታውን ሲገድሉ አልሞትላቸው ያለውን በአካል ለመግደል ይሞክራሉ፡፡ ብርቱዎች ግን ያንን ገጽታ ገደላ ተቋቁመው ያልፉታል፡፡ ወደ እውነተኛ እና ታሪክ አይሽሬ ሰብእናም ይቀይሩታል፡፡
ቴዎድሮስ ኮሶ ሻጭ ለተባለው ሰብእና ገደላ ተነበርክኮ በቋራ በረሀዎች ቀርቶ ቢሆን ዛሬ የማይሞተውን ዋናውን ሰብእና ለታሪክ አያስተላልፍም ነበር፡፡ አጼ ምኒልክ ለተነሳባቸው ሰብእና ገደላ ተነብርክከው ቢሆን ኖሮ ዛሬ “ያለምጣም” አይሆኑም ነበር፡፡ ይሄ የጥንት በሽታ አሁንም አለ፡፡ ሲሻው በግላጭ፣ እንዲያ ሲል ከሀሳዊ ማንነት ጀርባ ሆኖ፡፡ ለዚህ በሽታ ዘመናዊ ቴክኖሎጅው የበለጠ ጥንካሬ ሰጥቶታል፡፡ የዛሬ መቶ አመታት ገደማ ግብጽ ድረስ የውሸት ፎቶ በማቀናበር የተጀመረው የገጽታ ገደላ ዛሬ ቴክኖሎጂውን ተጠቅሞ የት እንደደረሰ በየእለቱ የምናየው ነው፡፡ ነገር ግን ገጽታ ገደላን ያላለፈ እውነተኛውን ሰብእና ለታሪክ አያወርስም፡፡

የኮሶ ሻጭ ልጅ እየተባለ ስሙ የጠፋው ቴዎድሮስ ግን በዘመኑ ከነበሩት መሳፍንት ሁሉ የላቀ የፖለቲካ ራእይ የነበረው ሰው ነው፡፡ ለምሳሌ ለ21 ወራት የንጉሱ እስረኛ የነበረው እንግሊዛዊ ሄንሪ ብላንክ ስለሀበሻ አገር የእስራት ዘመኑ ሲያትት እንዲህ ይላል፡ - በሚቀጥለው የዘመቻ እለት ንጉሱ አስተርጓሚ የነበረውን ሳሙኤልን አሁንም አሁንም ጥያቄ እያስያዘ ይልከው ነበር፡፡ ከጥያቄዎቹም፡- የአሜሪካ ጦርነት አበቃ እንዴ? ምን ያህሉ ሞቱ? ምን ያህል ወታደሮች ነበሯቸው? እንግሊዞች ከአሻንቴዎች ጋር ተዋግተዋል እንዴ? ተዋግተው ወረሯቸውን? አገራቸው ችግር አለበት? እንደዚህ እንደኛ አገር ነው? የዳሆሜ ንጉስ ለምንድነው የራሱን ዜጎች እንደዛ የጨፈጨፋቸው? ምን ነበር ሀይማኖቱ?

ቴዎድሮስ በዚሁ በሄንሪ ማስታወሻ እንደምናነበው በቆራጣ በኩል ጣና ላይ ጀልባዎች እንዲሰሩለት ብዙ ደከመ፡፡ ፈረንጆቹም ችሎታ አልነበራቸውም፡፡ “ማንም የሚረዳው እንደሌለ ሲያውቅ ራሱ ግሩም የሆነ ከወደመደቡ ጠፍጣፋ በጣም ወፍራም የደንገል ታንኳ ሰራ፡፡ በሁለት ሰዎች እጆች የሚሽከረከሩ እንደ ኃይል መስጫ መርገጫ አይነት እጀታዎች ከጎንና ጎን ሰራለት፡፡ በእርግጥ የጋዝ መቅዘፊያ ፈልስፎ ሰራ-- የማሽከርከሪያው ክፍል ብቻ ችግር ቢኖርበትም፡፡ ውሀው ላይ ለረጅም ጊዜ አየነው፡፡ ይሁንና በደንብ ተሸከርካሪ እጀታዎቹ በደንብ እንዲቀዝፉ ወደ መቶ ሰዎች ያስፈልጉት ነበር፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ይህንን ብዙም ጥቅም ሊሰጠው የማይችለው ስራ ላይ ጊዜውን ሲያጠፋ ከሰፈረበት ካምፕ አራት ማይሎች በማይርቅ ቅርበት በአመጸኛ ሽፍቶች መከበቡን ዘንግቶት ነበር” ይላል ሄንሪ፡፡ ስለመቅደላው መንገድ ሲጽፍም “ቀስ በቀስ መንገዱን ሰራው፡፡ መንገዱ በአውሮፓዊ መሀንዲስ አይን እንኳ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነበር፡፡ በዛም መንገድ ሞርታሮቹን እና መድፎቹን አጓጓዘበት” ብሏል፡፡ ይሄንን ባለ ራእይ ግን በኮሶ ሻጭ ልጅነት ከመንገዱ ለማሰናከል ብዙ ተብሎበት ነበር፡፡

ገጽታ ገደላ የመጀመሪያውን የአማራ ድርጅት መስራችና መሪ እንዲሁም መስዋእት ፕ. አስራት ወልደየስንም አልለቀቃቸው፡፡ ፕ. አስራት ዘለፋ፣ ስድብና አድማ የገጠማቸው ከራሳቸው ወገን እንደሆነ ዛሬ ብዙዎቹ በቁጭት ይናገሩታል፡፡ አማራ እየታደነ በገደል እየተጣለ በነበረበት ወቅት አማራ ለምን ይነካል በማለታቸው ብቻ በህብረ-ብሄር ኢትዮጵያዊያን እና አማራ-ጠል የ60ው ትውልድ አባላት “አክራሪ፣ ዘረኛ” እየተባሉ ይወነጀሉ ነበር፡፡ አስራት ግን ከትምህርትም እጅግ የተማሩ፣ ከዝናም ዝና የነበራቸው ሰው ነበሩ፡፡ በእርሳቸው ዘመን “እኔ አማራ አይደለሁም፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ ይኮፈሱ የነበሩት ሁሉ ሲያሳብቡ የነበሩት ተማርኩ ባይነትን እና ሁለንተናዊ ሰውነትን ነው፡፡ ነገር ግን ከአስራት አይደርሱም ነበር፡፡ አስራት እውነተኛ ትምህርት ስለነበራቸው እውነተኛ የህዝብ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ከእውነተኛ እውቀትና ትምህርት የህዝብ ፍቅር፣ የሰው ፍቅር ይመነጫል፡፡ ከይስሙላ እውቀትና ትምህርት ግን ሌብነት፣ ሀሜተኝነት፣ ጨካኝነት፣ አሉባልተኝነትና ግብዝነት ይወጣሉ፡፡

የሀበሻ ትምህርት በእውነት ወይም ሀሰት ሞዴል መስራቱ ራሱ ሌላው ችግር ነው፡፡ መሀል አልባ የኢትዮጵያዊያን ህይወት እንግዲህ መቸም ከ66ቱ አብዮት ፍንዳታ ጊዜ የበለጠ የተንጸባረቀበት ጊዜ የለም፡፡ ጤዛ ፊልም ላይ ፕሮፍ. ኃይሌ ገሪማ የጭብጥ መሪም አድርገውታል፡፡ ተስፍሽ “ወይ ከእኛ ነህ ወይ ከዛኛው ነህ፣ መሀል ላይ መሆን አትችልም፤ መሀል ሰፋሪ በሁለት ጥይት ይመታል ይሉሃል” ብሎ ለአንበርብር የሚያስረዳበት ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህ ምን ያመለክታል? በኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ልጅ መሀል ላይ መኖር አይችልም፡፡ ዳር እና ዳር ሆነህ ትጓተታለህ፡፡ ኃይል ያገኘው ጎትቶ ወደመሀል ያመጣህና ይከሰክስሀል፡፡ መሀሉ የምትከሰከስበት እንጅ በሰላም የምታርፍበት አይደለም፡፡

ይህን በሽታ የምናድግበት ሸፋፋ የትምህርት ስርዓት ያባባሰው ይመስላል፡፡ ለተማሪዎች ከመዋእለ ህጻናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ “እውነት/ሀሰት” የሚል ፈተና ብቻ ነው የሚቀርበው፡፡ ይህም ማለት ለኢትዮያዊ ሁሉም ነገር እውነት ነው ወይም ሀሰት ነው ማለት ነው፡፡ መሀል ላይ ለአከራካሪ ሀሳብ ቦታ የለም፡፡ አከራካሪ ሀሳብ በኢትዮጵያዊያን አእምሮ የለም፡፡ ሁሉም ነገር እውነት ወይ ውሸት ከሆነ ለምን ክርክር ያስፈልጋል!! እውነትነቱን የሚጠራጠር የግድ እውነት ወይ ሀሰት ማለት ስላለበት አንዱን ይመርጣል፡፡ አንተ እውነት እንዲል ፈልገህ እሱ ውሸት ካለ በዱላ ብለህ እውነት እንዲል ታስገድደዋለህ፡፡

በዚህ እውነት/ሀሰት የአእምሮ ስሪት ላደገ ማኅበረሰብ መከራከር አዲስ፣ መፈረጅ ግን ልማድ (“ኖርማል”) ነው፡፡ አእምሮአችን በጥንዳዊ አስተሳሰብ የሚሰራ ነው፡፡ ሌቪ ስትራውስ የተባለ ፈረንሳዊ አንትሮፖሎጅስት/ሶሲዮሎጅስት “ባይናሪ ኦፖዚሽን” ይለዋል፡፡ ምን ማለት ነው? የሰው ልጅ አእምሮ የአሰራር ስርዓት ጥንትም አሁንም በሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ማለትም በጥንድ ተቃራኒ ዘዴ ነው የሚያስበው ይላል፡፡ ለምሳሌ የሰው ልጅ አእምሮ ጨለማ ካለ ብርሀን አለ ብሎ ያምናል፡፡ ሞት ካለ ህይወት አለ ብሎ ያምናል፡፡ መሄድ ካለ መምጣት አለ፤ ጥሬ ካለ የተቀቀለ አለ ብሎ ያስባል፡፡ ነገር ግን ይሄንን ጥንዳዊ የአእምሮ ስሪት ባህል (ስልጣኔ) ከጥንዳዊነት ወደ ተተንታኝ አሳብነት ቀይሮታል፡፡ በብርሀን እና በጨለማ መካከል ጸሀይ ግባት፣ ምሽት፣ ውድቅት፣ ወጋገን፣ ንጋት፣ ጠዋት፣ ቀን እየተባለ የሚተነተን ብዙ አሀድ አለ፡፡ በሌላውም ሁሉ አስተሳሰብ እንደዛው፡፡

የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ግን ያው የጥንቱ የአእምሮ ስሪት ውስጥ እንደተወሸቀ ነው፡፡ እውነት ወይ ውሸት በሚል አስተሳሰብ፣ ወይም ነው ወይም አይደለም በሚል አስተሳሰብ የተቃኘ ነው፡፡ በእውነት እና በውሸት መካከል ገና እውነት እና ውሸትነቱ ያልለየ፣ ያልተጠና፣ ያልተረጋገጠ አስተሳሰብ መኖሩን አይረዳም፡፡ አንዳንድ በማህረሰቡ እንደ እውነት የተወሰደ ነገር ግን ቆይቶ ውሸት የሚሆን፤ አንዳንድ በማህበረሰቡ እንደውሸት የተወሰደ ግን እውነት የመሆን እድል ያለው አስተሳሰብ መኖሩን አያውቅም፡፡ ለምሳሌ የዚህ ጥንዳዊ አስተሳሰብ ውጤቶችን እንይ፡፡ ምኒልክ ጨቋኝ ነው ወይ አይደለም፡፡ ከነው እና አይደለም ውጭ ሌላ ምርጫ የለህም፡፡ ነው ብለህ ትስማማለህ ወይም አይደለም ብለህ ትጣላለህ፡፡ አማራ አለ ወይም የለም ይልሀል፡፡ ለምን ብለህ ብትጠይቅ መልስ አታገኝም፡፡ አለ ብለህ ትወገዛለህ (አሁን መፈራት ነው በእርግጥ)፤ ወይም የለም ብለህ ገልፍጠህ ይገለፈጥልሀል፡፡ የአማራ ብሄረተኝነት አለ ወይም የለም ተብለህ ትጠየቃለህ፡፡ አእምሮህ በተሰራበት የእውነት/ሀሰት ጥንዳዊ አሰራር መሰረት የለም ወይ አለ ብለህ ትመልሳለህ፡፡ ለምን ብሎ የሚጠይቅህ የለም፡፡ ቢጠይቅህም የምትመልስለትን ሊረዳው አይችልም፡፡ ምክንያቱም አእምሮው ለጥንዳዊ ድምዳሜ እንጅ ለመካከለኛው ትንተና ስላልሰለጠነ፡፡ አማራ ጨቋኝ ነው ወይስ አይደለም ተብለህ ትጠየቃለህ፡፡ አይደለም ብለህ ትጣላለህ ወይም ነው ብለህ ይጨበጨብልሀል፡፡

[ “ግዮናዊነት የአማራ መነሻ እና መድረሻ” ምስጋናው አንዱዓለም (መለክ ሐራ) ከጻፈው መጸሐፍ ገጽ 311-314 የተቀነጨበ]

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10105
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by ethiopianunity » 15 Nov 2022, 15:09

Right on the money Abere. But do not forget who created them, Eplf, still alive and well deceiving Ethiopians and government today. I have suspicion that Eplf aka Shania is probably wants the take over of Olf for government because it can control it via the olf leader in Welega, Dawd Ibsa, who was indoctrinated for years in Eritrea. Where is the main killing if. Amaras now? Isn't it in Wellega? How come no one is talking about in Ethiopia about Dawd Ibsa? He is killing Ethiopians left and right unless it controls or break Ethiopia. Whever killings occur, no one is talking about Dawd Ibsa. Why? This is why the fake alignment of Ethiopia and Eritrea, while killing Ethiopians by eritrean-allied Dawd Ibsa. You can't trick me, l have the ability to connect the dots. Eritrea also has alliance with Egypt too.

Wedi
Member+
Posts: 8457
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by Wedi » 15 Nov 2022, 15:18

Abere wrote:
12 Jan 2022, 11:10
ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

ሶስቱም ህሌና የሌላቸው አንዳችም ሰዋዊ ይሁን ሞራላዊ ብቃት የማይገኝባቸው ናቸው። የተሰራውን እና የተገነባውን ለማፈረስ እንጅ ምንም አስተዋጽ ኦ የማያደርጉ አገር እና ትውልድ የሚያፈርሱ እና የሚያኮላሹ ናቸው። ከወያኔ ይሁን ከኦነግ ጋር ሀሳብ ማበልጸግ እና ማንሸራሸር ማንም አይችልም እንድሁም ከጴንጤ እንድሁ ክርክር እና ግጭት እንጅ አንድም ቁም አዘል ሞራላዊ የሆነ ነገር የለም። ጴንጤ ልድፈርህ እንጅ የአንተ ሞራል እና እምነት ጥልቀት ምን እንድሆነ እንኳን አያውቅም። 3ቱም የጥፋት በሽታዎች ግን በውጭ ቀኝ ገዥዎች የተሰደዱ የጥፋት አውሬዎች ናቸው። 3ቱም ደግሞ በበታችነት የስሜት ደዌ የሚሰቃዩ የአእምሮ እና የመንፈስ ህሙማን ናቸው። የአእምሮ ደዌ እና መንፈስ ደካማ መሰብሰቢያ የጥፋት ጉሬዎች ናቸው። ኢትዮጵያ እንደት ከእነዚህ በሽታዎች ትላቀቃለች?

ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:-


1) ኢህአዴግ /ብልጽግና 2) ጴንጤ 3) ወያኔ 4) ኦነግ

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10105
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by ethiopianunity » 15 Nov 2022, 15:30

I do believe, since tplf take over, foreigners are the handlers of Ethiopia secretly, I think London and Israel. They are anti Orthodox that is why they decide who to be leaders in Ethiopia, I think. There is a say, " you are what your leader is" society changes based on who their leader is. Between H Mariam Desalegn and Any, more Ethiopian society is dangerously converting to Protestant. At the same time, millions is pouring into the country to convert more the Orthodox, they don't target the Muslims., Because through Saudi, there is natural alliance between West and Islam. Don't forget, Saudi helps West convert societies to Islam to help West when societies like Indonesia became problem, that is why they got converted to Islam. Islam, not religious itself is the problem but through Saudi, creates weak societies and oppressive, head cutting belief. Islam destroyed advancement Middle east where geometry, number was invented pre Islam. Through Egypt Islam leadership, Egyptian orthodox as well as Ethiopian Orthodox was deliberately weakened through false belief, that is why our King H Selassie refused Egypt Orthodox influence and leadership from Egypt as Egyptian Orthodox itself is losing Orthodox belief system and it's population and now remained only 3% and it's belief is corrupt. Through Tplf, Egypt succeeded in destroying Ethiopian Orthodox as well.

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10105
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by ethiopianunity » 15 Nov 2022, 15:37

Noble Amhara wrote:
12 Jan 2022, 12:37
What about Ethiopianwit? The beshitaw of the amaras you forgot to mention that which is the reason why cadres abiy worshippers and stupid idiots that think Amhara can coexist any where in the country exists. What is the purpose of amhara artificsts being in addis muesuem ? The gallas threaten to destroy that city in fact wealthy amharas should move to bahir dar amharas if smart would try to bankrupt addis nazret debrezeyt as revenge to geday opduma . Amhara wouldn’t be suffering this much if it didn’t hold Ethiopianism. Amhara has no place in hellhole shxthole welega and most of oromia. So that is the real disease. Ethiopia is not my problEm but Amhara gain 0 out of it ethiopianism is more dangerous to amara then anything else

If all amhara dont live in oromia let see how PP Oromunna government can survive! Oromia will crumble and its economy will become like afghanistan the shane is anti economic anti universal village tribal mindist. This means Shimlees Abdisa oromia is going to hell shane will destroy and empty oromia and its former pp blessings

The issue of penteism should also be dealt with in Amhara region. Ban all white missionary or any missionary from other region then build orthodox nationalism to counter it. The building of pente churches can also be banned in amhara region but that is a very small and minimal problem
Abere wrote:
12 Jan 2022, 11:10
ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

ሶስቱም ህሌና የሌላቸው አንዳችም ሰዋዊ ይሁን ሞራላዊ ብቃት የማይገኝባቸው ናቸው። የተሰራውን እና የተገነባውን ለማፈረስ እንጅ ምንም አስተዋጽ ኦ የማያደርጉ አገር እና ትውልድ የሚያፈርሱ እና የሚያኮላሹ ናቸው። ከወያኔ ይሁን ከኦነግ ጋር ሀሳብ ማበልጸግ እና ማንሸራሸር ማንም አይችልም እንድሁም ከጴንጤ እንድሁ ክርክር እና ግጭት እንጅ አንድም ቁም አዘል ሞራላዊ የሆነ ነገር የለም። ጴንጤ ልድፈርህ እንጅ የአንተ ሞራል እና እምነት ጥልቀት ምን እንድሆነ እንኳን አያውቅም። 3ቱም የጥፋት በሽታዎች ግን በውጭ ቀኝ ገዥዎች የተሰደዱ የጥፋት አውሬዎች ናቸው። 3ቱም ደግሞ በበታችነት የስሜት ደዌ የሚሰቃዩ የአእምሮ እና የመንፈስ ህሙማን ናቸው። የአእምሮ ደዌ እና መንፈስ ደካማ መሰብሰቢያ የጥፋት ጉሬዎች ናቸው። ኢትዮጵያ እንደት ከእነዚህ በሽታዎች ትላቀቃለች?
Shabian Noble Amara,

Your agenda is to separate Amara from Ethiopia pausing as Amara😉we know your agenda, tsk tsk

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10105
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by ethiopianunity » 15 Nov 2022, 16:12

kibramlak wrote:
13 Jan 2022, 03:04
To say Ethiopiawinet is same as Oromuma is exactly what Abiy is telling us implicitly. But practically speaking, they are in a diametrically opposit direction.

Ethiopiawinet embresses peace among its people regardless of ethnicity, religion,....and it doesn't restrict anyone to work and prosper anywhere in Ethiopia. Ethiopiawinet doesn't destroy its own history and conspire with internal and external enemies. Oromomuma on the other hand conspires with both internal and external enemies, use ethnicity to loot and ulwafully prosper, destroy Ethiopian history, wants to expand paganism, aka gada system and Satan cult (aka irecha), burn and loot the hard earned properties of others, never want to co-exist with others,.... Oromuma is from the same OLF collection of idi@ts who salivate to invade and destroy the culture and properties of others while protecting their own. Oromuma is expanding lawlessness and anarchy in the country. Oromuma want to destroy the script of Ethiopia while shamelessly using foreign Latin script, borrowing missionary religion,...

I entirely agree that OLF (aka Oromuma), TPLF and Pente are the main ils of Ethiopia causing violence and discord among people.

By the way, Muslim and Christians coexisted seamlessly for centuries and Ethiopia is a unique country in the world where we see such peaceful coexistence, until the evils (tplf, pente, oromuma) came into existence. Despite all their evil effort, the centuries old strong bond between the traditional Muslims and Christians are found to be unshakeable. I love Ethiopiawinet whenever I thing of our Muslim and Christan brotherhood, peaceful and seamless coexistence. That is what Ethiopiawinet is. Ethiopiawinet fights evils while Oromuma nurture evils. That's it.

Naga Tuma wrote:
13 Jan 2022, 01:48
Abere wrote:
12 Jan 2022, 17:45
One point I would like to stress though is no region can survive without Ethiopiwinet, those sh!t Orommuma can't even survive a single day if Ethiopia is not there; the sh!t Ormumma is so far on artificial breathing system, if for one or another reason Ethiopiawinet is unplugged …
As a side note, conceptually, there is no practical difference between ኢትዮጵያዊነት፣ ኦሮሙማ፣ ሃደ ልቢ ሃደ ህዝቢ፣ የኣፍርካ ቀንድንት።

At least in my understanding, all are affronts to intra rivalries in favor of unity of purpose. Some may have projected it against others. Unity of purpose can be meritocratic and on different scales. You can talk about the opposite of clean a thousand times by just talking about clean a thousand times.
Sometimes, those Ethiopians fight is like shooting themselves on the toe because if lack of knowledge and diplomacy thus in fact what is hurting Ethiopia is not the internal and external enemies but us. When one thinks about Ethiopia, must not attack what existed before communists and liberation fronts and pentes took over Ethiopia. If you recall, Ethiopia embraced all ethnicity, faith that was there before. What Ethiopia should have worked in before evil derg, liberation fronts, pente took over on democracy or system that will power all areas of Ethiopia, instead of centralized system, economically, governing, systems. That is all. Today, everything is wrong system, the so called liberation fronts lied there was oppression under the king but tplf oppressed the entire population, looted economically , with the benefit it collected from Ethiopians, bought military to continue the oppression. But today there are Ethiopians even telling you the kingdom rule was oppressive than Tplf and derg. Derg did absolutely no benefit at all for Ethiopia. Tplf benefited and those worshipping tplf talk about benefiting Ethiopia, l am laughing... First tplf is minority, so has to buy people and alliance, plus 100% benefit was killing the entire population in every way while benefiting itself. Those worshippers of tplf do not see Ethiopia or themselves beyond tplf, they demoted themselves, by accepting Dabo Ferefari from tplf, telling you they still support tplf. While speaking tolf, the enemy has set up a new type of enemy, pente and olf before we complete tplf. When every person is being appointed around Aby government, find out their background and who they are. They are chose for purpose. Soon most pro Ethiopians will be sidelined, imprisoned, etc once tplf is gone, us it gone? For example, why was Bethany Julia chosen over Bacha Debele? Is Berhanu julla more sympethise with olf than Bacha? Why were Bacha and Seleshi bekele were deceptively sent to work outside of Ethiopia because, they are pro Ethiopians, are not wanted in Ethiopia so that Dawd Ibsa and Olf can operate freely against Ethiopia. Not to mention pente

My main purpose to respond to you kibreamlak us that, we had Great system and animist practicing before the real enemies came in Ethiopia. So don't go there and add gas to the fire unecessariky. Ethiopia in the past had embraced these to exercise their faith, today should not be sany difference. Choose your battles

Meleket
Member
Posts: 4594
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by Meleket » 17 Nov 2022, 06:28

ለግንዛቤ ያህል ነው። ምንም እንኳ በመጸሐፉ ሙሉ ይዞታ ሙሉ በሙሉ ባንስማማም፤ የደራሲውን ትጋት በፍጹም አለማድነቅ አይቻልም። አማራ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ ቢያነበው ብዙ ቁምነገር ሳይቀስምበት አይቀርም። ትንሽ እስቲ ከመጸሐፉ ይዞታ ቀንጨብ አድርገን እናካፍላችሁ።

"የግዮናዊነት" ደራሲው ምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ “መሪ ኣንቀጽ” ባለው አርእስት ስር ስለመጸሐፉ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል
ይህንን መጽሃፍ ሳዘጋጅም አብዛኛውን ማስረጃ የወሰድኩት በሳይንሳዊ መንገድ የተጻፉ ሰነዶችን ተገቢ እና ትክክለኛ በሆነ አግባብ በማጣቀስ ነው። በሳይንሳዊ መድብሎች ያልታተሙ የአገር ውስጥ ጸሀፍት የስራ ውጤቶችም ጥቅም ላይ መዋላቸው ሳይዘነጋ፡፡ እናም መጽሀፉ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ እና ብርቱ ጥረት የተደረገበት የጥናትና ምርምር ውጤት ነው፡፡


ጸሃፊው ስለ "ቤተ አማራ እንቅስቃሴ" በገጽ 18-19
1) አማራ እንደህዝብ ህልውናው ላይ የተደቀነበት አደጋ፤ 2) አማራ በተናጠል እየገጠመው ያለው የየእለት ስጋት፤ 3) አማራ የተዘፈቀበት አሰቃቂ የድህነት አረንቋ፤ 4) ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች የደረሱበት የብሔረተኝነት ደረጃ፤ 5) የአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች ለፍረድ አለመቅረብ፤ 6) ራሱን አቅልጦ የሰራት አገር ያልበጀችው መሆኑ፤ 7) እስካሁን አማራ ላይ የደረሰው በደል አብሮነትን አደጋ ላይ የጣለው መሆኑ፤ 8. ሁሉም ብሔረሰቦች የየራሳቸው ጸረ አማራ ድርጅት ሲኖራቸው አማራ ግን ለራሱም የሚሆን የሌለው መሆኑ፤ 9) በህብረ ብሔራዊ አደረጃጀት ውስጥ መቆየት ጉዳት እንጅ ጥቅም የሌለው መሆኑ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡


ደራሲው ስለ "ኣማራ መንገድ" በገጽ 155-157
ብዙ መንገድ ተጉዟል፡፡ ሲወድቅ ሲነሳ አያሌ ፈተናዎችን አሳልፎ እዚህ ደርሷል፡፡ ይሄንን መንገዱን ከማሰሳችን በፊት አማራ ማን ነው የሚለውን ከኮግኒቲቭ (ስነአእምሮአዊ) ሳይንስ (አንትሮፖሎጅ እና ሳይኮሎጅ) አንጻር እንየው፡፡ ማለትም የሚከተለው ዝርዝር የማንነት ገለጻ የተመሰረተው ከኮግኒቲቭ አንትሮፖሎጅ ንድፈ-ሀሳቦች ውስጥ በአንዱ ስኬማ ንድፈ-ሀሳብ ወይም የራስ ትውስታና ምልከታ ዓለም ንድፈ-ሀሳብ (Cultural schema theory) ላይ ነው፡፡ በካልቸራል ስኬማ ንድፈ ሀሳብ (እሳቤ-ምናብ) መሰረት የአማራ ህዝብ የሚጋራቸው፣ የራሱ ብቻ የሆኑ መገለጫዎች አሉት፡፡ እነዚህ መገለጫዎች ሌሎች ብሄሮች/ዘውጌዎች ከአማራው የተለየ የራሳቸው ስኬማ እንዳላቸውም የሚያሳይ ነው፡፡ ይሄንን አስተሳሰብ በቀላሉ ለማስረዳት ለምሳሌ በግለሰብ ደረጃ አዛሉ ስለራስዋ ያላት ትውስታ፣ የህይወት ምልከታ፣ ያለፈችበት ታሪክ፣ ምልከተ ዓለም ወዘተ ከታደሰ የተለየ ነው፡፡ ሁለቱ የየራሳቸው ስኬማ አላቸው፡፡ ወደ አማራ እንደ ህዝብ ስንመጣ ደግሞ የራሱ ህዝባዊ የሆነ እሳቤ-ምናብ አለው፡፡ (ለበለጠ ግንዛቤ የካስቶን ሮናልድን325 Schemata in Cognirive Anthropology አንብብ፡፡)

ከስኬማ ወይም ምልከታ-ዓለም-ወትውስታ አንጻር ይህ አማራ የህዝብም፣ በግለሰብም የየራሱ የሆነ መገለጫም ያለው ህዝብ ነው፡፡ ሲራመድ ዝግ ብሎ የሚሄድ፤ አጠገቡ ላለ እንቅፋት የማይሆን፤ የራሱን መንገድ ብቻ የሚሄድ፤ የወደቀ ሰው ካገኘ የሚያነሳ፤ ደካማን ረግጦ የማያልፍ ህዝብ ነው፡፡ አማራ ቤት የእግዜር ነው ብሎ አልጋውን ለእንግዳ ለቆ ወለል ላይ የሚተኛ ህዝብ ነው፡፡ እርቦት እንኳ ቢሆን የያዘውን ለአላፊ ወይም ለእንግዳ የሚያበላ፤ ጾሙን አድሮ ፈጣሪውን “ለእንግዳየ የማበላው ስላላሳጣሀኝ አመሰግንሀለሁ” ብሎ አይኑን ወደ ሰማይ ከፍ አድርጎ የሚያመሰግን፡፡ እንኳን መብላት ማብላት ይቀራል የሚል አስገራሚ የሆነ ራሱን ጥሎ ለሌላው የሚኖር ባህል ያለው፡፡ ክፉን በክፉ አልመልስም ብሎ እየተገፋም በትእግስት አሜን ብሎ የሚኖር፡፡ እሱ ዛኒጋባ ውስጥ እየኖረም ቢሆን እንኳ የአምላኩን ቤት አስጊጦ የሚሰራ፡፡ ምግብና መጠጥን ለሞተ እህል ትዝብት ውስጥ አልወድቅም በማለት በልግስና የሚያበላ፤ የሚያጠጣ፡፡ ያበደረውን ገንዘብ ሲያልፍልህ ትሰጠኛለህ በማለት ራሱን ችግር ላይ የሚጥል፡፡ ባለው ነገር ሁሉ የማይኮራ፤ ዓለምና የዓለም ሁሉ አላፊ ጠፊ ነው ብሎ የወዲያኛውን ዓለም በማሰብ ራሱን ረስቶ የሚኖር፡፡

አማራ በጣም የሚያስገርም ለሌላው መስዋእት የመሆን ስሜት ያለው፡፡ ዘር ማንዘሬ ብሎ አድሎ የማይሰራ፤ በወንድሙና በሩቅ ሰው መሀል እኩል የሚፈርድ፡፡ ፍትህን የማያጣምም፤ ታማኝ እና እውነተኛ፡፡ ሲናገር አስቦና አስልቶ፤ ክፉና በጎውን መዝኖ የሚናገር፡፡ ለተጎዳ ሁሉ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ፡፡ ራሱን መውደድን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ እኩልነት የሚለውን ብሂል በእምነት፣ በሀሳብ፣ በስራ እና በኑሮ የሚተገብር፡፡ ታላቁን አክባሪ፤ የማይቅለበለብና በአደባባይ ሁሉ ኩሩ የሆነ፤ ለራሱ ያለውን ክብር በመብልም ሆነ በመጠጥ የማይሸጥ፤ ክብርን ከመጣል ራስን መጉዳት የሚመርጥ፡፡ ቢማርም ባይማርም አርቆ የሚያስብ፡፡ ከጫፍ እስከጫፍ ከአንድነቱ የተነሳ በአይን ጥቅሻ ብቻ የሚግባባ፡፡ ትእግስትን እንደ ሀብት የሚቆጥር እና የሚንከባከባት፤ ተበድሎ እንኳ ፍቅርን የሚያሳይ፤ ይቅርታን የሚያደርግ፤ ምህረትን የሚወድ፡፡ ስርቆትና ቅጥፈትን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ ሀቅን ሀብቱ ያደረገ፤ ለልጆቹ ማታ ማታ ሰብስቦ መልካምነትን እና ጀግንነትን የሚያስተምር፡፡ ጭካኔና አረመኔነት በልቡ የሌለበት፤ ቆራጥ እና ገደቡን ሲያልፍ አትንኩኝ ባይ፡፡ መማርን እና ማወቅን እንዲሁም ማስተማርን የሚወድ፡፡ ላመነበት ነገር የማያመነታ፤ ብርቱ ወታደር እና ታማኝ አገር ጠባቂ፡፡ አድሎን የማይወድ፡፡ ታሪኩን ጠንቅቆ የሚያውቅ፡፡ በሆይ ሆይታ የማይመራ፡፡ አሽሙረኝነትን የሚጠላ እና እውነትን ፊት ለፊት የሚጋፈጥ፡፡ አገርና ወገኑን የሚወድ፤ ክብርን የሚወድ እና ሰውን የሚያከብር፡፡ የማይከዳ እና ሸፍጥ የሌለው፤ ቀልማዳነትን የሚጸየፍ ቀጥተኝነት ያለው ነው--አማራ ማለት፡፡

አማራ ሲናገር፤ ሲራመድ፤ ሲመገብ፤ ሲቆምና ሲቀመጥ አማራነቱን የሚያስታውቅ የስነ ስርዓት ማህተም የታተመበት ህዝብ ነው፡፡ አደራ ጠባቂ፤ ሁልጊዜም ከራሱ አልፎ ቀጣዩን ትውልድ የሚያስብ፤ ለቀጣዩ ትውልድ አገርና በጎ ታሪክ ለማስረከብ የሚታትር፤ ለልጆቹ ክፉውን እየተወ በጎ በጎውን ብቻ የሚያስተምር፤ ሰለራሱም ሆነ ስለሌላው ህዝብ ጥላቻን የማይሰብክ፤ ለልጆቹም ጥላቻን እና ቂምን የማያወርስ፤ ከፍተኛ የሆነ ራሱን የመቻልና የነጻነት መንፈስ ያለው፤ ከውስጥም ከውጭም የገጠሙትን ፈተናዎች አልፎ ለራሱ እዚህ የደረሰ እና ሌሎችን ማሰባሰብ የቻለ፤ ከጥንት እስከዛሬ ድረስ አንድ አይነት ፈተና እያጋጠመው ያለ፤ ሌሎችን እየወደደ እና ለሌሎች እየኖረ ክፉ የሚመለስለት ህዝብ ነው፡፡ ባህሉን ጠባቂ እና ከማንም ማነስን እንደ ነውር የሚቆጥር፤ በራሱ የሚያምን፡፡ በሁሉም አይነት ስነ ምግባር ምሳሌ የሚሆን እና በአንጻራዊነት ሲታይ ይህ ቀረው የማይባል ጨዋ፤ አርቆ አሳቢ፤ እንደግለሰብም እንደህዝብም ሁልጊዜም እያመነ ግን ያመናቸው የሚከዱት፡፡ ተስፋን የሚወድ እና ሁልጊዜም ነገን ብርሀናማ አድርጎ የሚያስብ፤ ጠብ አጫሪነትን እና ተንኳሽነትን ከደሙ የሚጠላ፤ ክፉ በደልን ባይረሳው እንኳ ይቅር የሚል፤ ፍትህን እና ፍርድን የሚወድ፤ ግፍ መስራትን በልጆቸ እንዳይደርስ በማለት አጥብቆ የሚፈራ፤ ከክፋት ሁሉ ለመራቅ የሚጥር፤ በወላጅነቱ ለልጆቹ ብቁ እና መልካም ምሳሌ የሚሆን ህዝብ ነው፡፡ ይህ የአማራ መንገድ ይባላል፡፡ አማራ የመጣበት መንገድ፡፡ አማራ የሚሄድበት መንገድ፡፡

አማራ በጠባቦች መካከል ሁሉን አቀፍ አንድነታዊ ስሜት ይዞ መኖሩ በጅምላ ወደ መጨፍጨፍ አድርሶታልና እየከበደንም ቢሆን፣ ማነስና መጥበብ ቢመስልብንም፤ ወደ አማራዊነት አስተሳሰብ መግባት ግድ ብሎናል። ለመሰንበት፣ ከተጠነሰሰልን የዘር ማጥፋት እራሳችንን ለመታደግ፣ ለወገን መከታ ለመሆን፣ አማራ በአማራነቱ ይደራጅ ዘንድ፤ አማራዊ አስተሳሰብ እና አማራዊ ስነልቦና መላበስ ግድ ነው። በዙሪያችን ካሉ ሊውጡን ካሰፈስፉ ግለሰቦች፤ ቡድኖችና ማህበረሰቦች ልናመልጥ የምንችለው በመለማመጥና የነሱን አፈታሪክ እንደ እውነት እየተቀበሉ፣ አንድነት እያሉ ጨፍጫፊዎችን በማሽሞንሞን ሳይሆን፣ በራስ ማንነት ኮርቶ፣ ለራስ ቆሞ፣ በራስ ለራስ በማሰብና በመስራት ነው፡፡

ለህዝባችን ህልውና ይህ የአማራዊነት እንቅስቃሴ ወደርየለሽ ቅዱስ ተግባር ነው፡፡ ይህ አማራዊነት ንቅናቄ ቀድሞ ለኢትዮጵያ ሲባል በአደራ መልክ ያስቀመጥነው የክት ማንነታችን ነው፡፡ አሁን ብንሰፋው ብንሰፋው ሊገናኝ ያልቻለውን የኢትዮጵያዊነት አይጨበጤ አደረጃጀት ትተን ወደ መደበኛውና ጥንተ ማንነት ተመልሰናል፡፡ ተመልሰንም ስንጎበኘው እጅግ ጣፋጭ፤ መሳጭ፤ ኃይል የታመቀበት፤ የሚያጉዋጉዋ ተስፋ ያለው፤ ከክስ የነጻ፤ እጅግ ሰላማዊ፤ እንደ ስሙ ነጻ ህዝብነት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህንን ነጻነት ከነ ሙሉ ክብሩ ለመመለስና ለማጣጣም እንቸኩላለን፤ ለዛውም እንታገላለን፡፡ የአማራ አማራነት ንቅናቄ ትክክለኛ ፈውስ ነው፡፡

Abere wrote:
15 Nov 2022, 09:42
እንደተረዳሁት ከሆነ ይህን የጻፈው ሰው እራሱ አሉቧልታ የሚዘራ እንጅ ስንጥር መረጃ እንኳን ሰብስቦ መሰነድ አልቻለም። ይህን ትችት የሰነዘረው ግለሰብ ስለተጻፈ ብቻ በልማድ ሳይንሳዊ ይሆናል ሰዎችም ይቀበሉታ ብሎ በመገመት አማራን ኢላማ ያደረገ እና ያተኮረ ልብወለድ ነው። ጎሳ ላይ ያነጣጠሩ እንድህ አይነት ፍረጃዎች ከወያኔ ጋር አብረው የተወለዱ ቀድመ ወያኔ ያልነበሩ ነገሮች ናቸው። የጋርዮሽ ማህበረዊ ንቃተ-ህሌና ወይም አገራዊ የጋርዮሽ እሴት አስተሳሰብ የሆነ ሁሉ የአንድ ጎሳ የማድረግ እና ያንን ጎሳ የማጥላላት የመክሰስ እና የመወንጀል ስራዎች የወያኔዎች ገጸ ባህርይ እና መሪ ሃሳብ ነው። ይህን ኦነጎችም ይጋሩታል- በመጀመሪይ ይህ የፈጠራ ስራ ዋና አላማም ኦነጎች ዋና የሸቀጠ-ሃሳቡ ፍጆታ ገዥዎች ናቸው በሚል ስሌት ነው። የፈጠሩት ገጸባህርይ ስህተት እንደ ሆነ ወያኔዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ። በአጭሩ ዝንብ ፈጥረው ንብ ናት በማለት ያልነቃ እና የዋህ ዝብ ማታለል ነው። የአገራችን ሰው ሞኝ ነው። የተጻፈ ያምናል። አንድ ቃልቻ ወይ ቄስ ይህ ከአጋንንት ይጠብቅሃል ብሎ ወረቀት ተብትቦ በአንገትህ ያዝበት ቢለው በእውነትም ያድናል ብሎ በቡትቶ ጨርቅ ወረቀት በአንገቱ ተሸክሞ ይኖራል። ታዲያ አስኮላ ትምህርት የተማረ ውሸት ከተረከለት እንደት አይቀበል?!

አንዱ አፍቃሪ ወያኔዎች አምባገግ ውሸት እና የአማራ ጥላቻቸው አንድ ሺ አንድ ጥላቻ አዘል ውሸት በአማራ ላይ ሲተርኩ አንድት እንኳን ጥሩ ነገር ይህን አበርክቷል ብለው ሲናገሩ ተደምጠው አያውቁም። በኢትዮጵያ በጎሳ ላይ ይጠነጠነ ገጸባህርያት ሙሉ በሙሉ የተፋለሰ እና የተሳሳተ ነው። ቅድመ-ወያኔ የነበረው ማህበራዊ እሳቤ የጋርዮሽ እንጅ የጎሳ ፍልስፍና አይደለም። አንድ ነገርን ለህዝብ ለማቅረብ የሚዳሰስ ማስረጃ ወይም እሙን ሰነድ ያስፈልጋል።
እንደየ አስፈላጊነቱ፡ አንድ ሁለት ንኡስ አርእስቶቹን መርጠን ልናካፍላችሁ እንሞክራለን። ይዞታውን አንብባችሁ ትገመግሙት ዘንድም ይረዳችኋል፡ በዚህ ጽሁፍ ተገፋፍታችሁም ሙሉ መጸሐፉን ለማንበብም ትበረታቱ ይሆናል። ይህን ጽሑፍ ለታላቁ አጼ ስሱንዮስ ክብር እንዲሁም ለጸሐፊው ክብር ስንል አጋርተናችኋል። :mrgreen:

Meleket
Member
Posts: 4594
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by Meleket » 18 Nov 2022, 04:29

"ግዮናዊነት" የሚል ርእስ ያለውን የምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ ጥናት እንዲያው በጨረፍታ ለማሳዬትና ሙሉ ጽሑፉን ታነቡትና ትወያዩበት ዘንድ ለማበረታት ያህል ነው።

ውንጀላ አማራ፤ ከባሮን ፕሮቻዝካ እስከ የደቡብ ጎታች ሊቃን” ባለው ንኡስ አርእስት ደራሲው እንዲህ ይገልጻል (245 – 247)

ተሻለ ጥበቡ በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ጭቆና አልነበረም፣ ጨቋኝ ብሄርም አልነበረም፡፡ እንደ ጭቆና ተደርጎ የተወሰደው የአማርኛ መስፋፋት እና የአማራ የባህል የበላይነት ነው፡፡ ይሄም የሆነው፤ ከዚህ የተሻለ ሀሳብ ላይ ለመጨመር፤ አማርኛ ተቀባይነት በማግኘቱ እና የራሱ የሆነ የጽህፈት ቃላት ስላሉት ጭምር ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች እንዳደረጉት ከላቲን ከማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉለኝ አላለም። አማራም አማርኛን ለአፍሪካዊያን የራሳቸውን የአፍሪካ ምድር-በቀል ቋንቋና ባህል ከማስተማር የዘለለ በደል የለበትም፡፡ ከዛ በተረፈ አማራው ጨቋኝነቱን አያውቅም፣ ከሌላው የተለየ ህይወትም አልነበረውም፡፡ ነገር ግን፤ ተሻለ ይቀጥላል፤ የነበረውን የአማርኛ ቋንቋ የበላይነት እንደ ብሄራዊ ጭቆና የወሰደው የሌኒን-ስታሊን ግርፍ ተማሪ እጅግ ከባድ ስህተት እንደሰራ ይተቻል፡፡ የራሱን ድምዳሜ ሲያስቀምጥም ኢትዮጵያ ውስጥ መካሄድ የነበረበት የቋንቋ ጥያቄ እንጅ የብሄር ጥያቄ አልነበረም በማለት ነው፡፡ ይህ የተሻለ ክርክር ቀደም ብለን በጠቀስነው የሌኒንና መሰሎች የተደገፈ ነው፡፡ አማራ ወንጀል ስለሰራ ሳይሆን የወቅቱ እንጭጭ እና ዘረኛ ተማሪዎች የግድ ወንጀለኛ ህዝብ ማግኘት ስለነበረባቸው ለራሳቸው አፋአዊ ማርክሲዝም-ሌኒኒዝም ቀኖና የለጠፉበት ስም ነው፡፡ የቋንቋ ስርጭት አድማስ ብሄራዊ ጭቆና ተደርጎ የተወሰደው እነዚህ የ60ዎቹ ተማሪዎች በበቀሉበት አገር ኢትዮጵያ ነው፡፡

ለማጠቃለል፡- 1) ጣልያናዊው ባሮን ነጮች በአማራ ላይ እንዲነሱ ከባድ ቅስቀሳ አደረገ፡፡ 2) አማራው ዋለልኝ መኮንንና በሱ ይመራ የነበረው ተማሪ የባሮንን ሀሳብና የማርክሲዝምን-ሌኒኒዝምን ሀሳብ በማዳቀል ሁሉም ብሄሮችና ህዳጣን ብሄረሰቦች እንዲሁም የወቅቱ ፊደላዊ (ተማሪ) አማሮች በአማራ ህዝብ ላይ እንዲነሱ ከባድ ቅስቀሳ አደረገ፤ ያደርጋልም፡፡ 3) እንደነ አሰፋ ጃለታ አይነቱ ኦሮሞና ቡድኑ አፍሪካዊያን በአማራ ላይ ተነሳስተው እንዲያጠፉት ከባድ ቅስቀሳ አደረገ፤ ያደርጋልም፡፡ 4) ህወሀት መላው ትግሬ እና መላው የኢትዮጵያ ብሄሮችና ህዳጣን ብሄረሰቦች እንዲሁም ወዳጅ አገሮቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በአማራ ላይ እንዲነሳሱበት ከባድ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡ 5) የእነ ፕሮፍ. መስፍን አማራ የለም ባይ ቡድን ይህ ሁሉ ቢላ እየተሳለለት ያለውን አማራ እንዳይነሳ የለህም እኮ እያለ ያደነዝዛል፡፡ 6) እንደእነ አቶ ተክሌ የሻው ያሉት ይህ ሁሉ ቢላ እየተሳለለት ያለውን የአማራ ስጋት በመደፍጠጥ “የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት” መረጋገጥ ዋስትና እንደሆነ በመስበክ ሁሉም ብሄሮችና ህዳጣን ብሄረሰቦች የበለጠ እንዲጨክኑና አማራን በሞላ እንዲገጥሙት ቅስቀሳ ከማድረጉም በተጨማሪ “አማራ ማለት አማርኛን የሚናገር እና አማራ ነኝ በሎ የተቀበለ” ነው ሲሉ የአማራን ህልውና በመካድ ተባብሮ እንዳይቆም በነበሩበት ስታሊናዊ ፍልስፍና የአማራን ህልውና ጠቃሚ መስለው በመታየት ይክዳሉ። 7) የጎጥ፡ የወንዝና የክፍላተ-ሀገራት ማህበራት ከህወሀትና ሌላው ጎታች ኃይል ጋር በማበር አማራው አንድ ላይ እንዳይቆም በርትተው ይሰራሉ፡፡ 8. በደቡብ ሊቃን እየተመራ የሚገኘው ጎታች ኃይል አማራን በተራየ ሳልጨቁነው ራሱን ችሎ ሊቆምብኝ ነው ብሎ በመርበትበት ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ አማራውን በማፈን ላይ ይገኛል፡፡ 9) የትግራይ ወኪል በአማራ ወይም የትናንቱ ኢህዴን የዛሬው ብአዴን “ዴሞክራሲያዊ ብሄረተኝነት” በሚል የሎሌነት ፈሊጥ አማራን ለትግራይ አንበርክኮ ለማስገዛትና ዘሩን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ጉድጓድ ሲጭር ያድራል፡፡ ይህ ሁሉ እንግዲህ ከጣልያን ጀምሮ ሲቆጠር ላለፈው 50 እና 60 አመታት በአማራው ላይ የተደረተው ውንጀላ ውጤት ነው፡፡ አዲሱ የአማራ ትውልድ እንግዲህ ዳግም ላይቀለበስ በጀመረው የህልውና እና የማንነት ትግል ይህንን ሁሉ ተገንዝቦ ለዚህ የስጋት ቀለበት እልባት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ የትግሉ ሙሉ ተቆጣጣሪም ሆነ መሪ እራሱ ወጣቱና ወጣቲቱ መሆን መቻላቸው ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ መሆን የለበትም።


አንድ ያልሆነ አንድነት” በሚለው ንኡስ አርእስት ውስጥ ደራሲው በገጽ 326 – 328

በህይወት ውስጥ ሁለት ነገሮች ማእከላዊ ቦታ ይይዛሉ፡ አብዝተው የሚወዱት እና አብዝተው የሚጠሉት ነገር፡፡ የምትወደው ሁልጊዜ ትዝ ይልሀል፡፡ የምትጠላው ሁልጊዜ ይመጣብሀል፡፡ በአማራ ህይወት ውስጥ እንደዚህ አይነት አያሌ ሁለት-መደቤ ነገሮች አሉ፡፡ በአንድ ጊዜ የሚወደዱና የሚጠሉ፡፡ እንደ “አንድነት” የሚሆን ግን አለ ለማለት አይቻልም፡፡ እስካሁን ያለው የአማራ ታሪክ ይህን ያሳያል፡- አማራ ከኖረ ለአንድነት ነው፤ የሚጠፋም ከሆነ ለአንድነት ነው፡፡ አንድነት ህይወታችንን የተቆጣጠረ፣ አይረሴ ትውስታችን እና የአሁን ጊዜ ህልውናችን እንዲሁም የወደፊት ስጋት እና ተስፋችን ነው፡፡ እንደ አማራ አንድ ስንል አንድን ነገር እንወዳለን፡፡ እንደ አማራ አንድ ስንል አንድን ነገር በጣም እንፈራለን፡፡ ይሄን አንድነትን አለቅጥ እንወደዋለን፡ የዛን ያህልም አለቅጥ እንፈራዋለን፡፡ ይሄ አንድነት በፍቅርም በስጋትም እስረኛው አድርጎናል፡፡

ለአንድነት ስንል የሰው ልጅ የማይሆነውን ሁሉ ሆነናል፡፡ ለአንድነት ስንል በሰው ሊደርስ የማይገባ ደርሶብናል፡፡ ለአንድነት ስንል ራሳችን ሽጠናል፡፡ ለአንድነት ተዋግተናል፡፡ ለአንድነት ተዋደናል፡፡ ለአንድነት ጨክነናል፡፡ ለአንድነት ስስ ልብ ሆነናል፡፡ ለአንድነት ጀግነናል፡፡ ለአንድነት ፈሪ ሆነናል፡፡ ለአንድነት መጫወቻ ሆነናል፡፡ ለአንድነት ጅል ሆነናል፡፡ ለአንድነት ተጎሳቁለናል፡፡ ለአንድነት ተዘባብተውብናል፡፡ ለአንድነት የህዝባችንን ህልውና አደጋ ውስጥ ጥለናል፡፡ አንድነት በህይወታችን ውስጥ ትልቅና ማእከላዊ ቦታ በመያዙ እስረኛም ምርኮም አድርጎናል፡፡ አንድነት በህይወታችን ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው አስተሳሰብ በመሆኑ ታሪክ ይቅር ለማይለው ውድቀት ዳርጎናል፡፡ በአንድነት አስተሳሰብ የተነሳ እንደ አንበሳ ተነስተን እንደዝሆን ወድቀናል፡፡ ለአንድነት በመኖራችን ዋናውን ህይወታችንን ህይወት ነስተነዋል፡፡ ለአንድነት ወደን ፈሪ፣ ወደን ተማራኪ፣ ወደን ትሁት ሆነናል፡፡ የአንድነት ጽንሰ ሀሳብ ሀይላችንን ሁሉ ቀፍድዶ ደካማ አድርጎናል፡፡

አማራ የአንድነት እስረኛ ህዝብ ነው፡፡ እጅና እግሩ በአንድነት ሰንሰለት ስለታሰረ የማንም መጫወቻ የሆነ ህዝብ፡፡ ለአንድነት ያለንን ፍቅርና ስስት በመጠቀም የአንድነት ጠላቶች ነገር ግን ተጠቃሚዎች እስረኛ አደረጉን፡፡ አንድ አለመሆንን እጅግ እንደምንፈራ በማወቃቸው አቆላማጭ አደረጉን፡፡ አርቆ አሳቢነታችን እያሸነፈን ስለ አንድነት የምንከፍለው መስዋትነት የቃየልን እየሆነ አንድነት ለአማራ ኑሮውን ከሰማይ የከበደ ከገደልም የተናደ አድርጎበታል። አማራ ስለ አንደነት ደሙን በአፈሰሰ አጥንቱን በከሰከሰ ቤተክርስቲያን እንደገባ ውሻ ማንም እየተነሳ ይቀጠቅጠዋል።

ይህ እጅግ የምንወደውና እጅግ የምንፈራው አንድነት ማነው? የኢትዮጵያ አንድነት፡፡ የኢትዮጵያ የታፈረች ትልቅ እና አንድ አገርነት አስተሳሰብ፡፡ አማራ በአጭር አገላለጽ የኢትዮጵያ አንድነት እስረኛ ህዝብ ነው፡፡ አለቅጥ አፍቅሯት፣ አለቅጥ ፈርቷት የሚኖርላት አስተሳሰብ የኢትዮጵያ አንድነት ናት፡፡ ስለኢትዮጵያ ሲወራ ከምንም ነገር ቀድሞ የሚመጣው አንድ አገር ወይም የኢትዮጵያ አንድነት የሚለው ሀሳብ ነው፡፡ በንግግራችን፣ በጽሁፋችን እና በኑሯችን አንድ ወይም አንድነት የማንልበት አጋጣሚ የለም፡፡ አንድነት ይሄንን ያህል በህይወታችን ውስጥ ጠቃሚ ሚና የሚጫወትበት ምክንያት ብዙ ነው፡፡ ዋና ዋናዎቹን ለመጥቀስ ያህል፡ አማራ ፈጣሪ ገነትን ሲሰራ ከአምላኩ በመማር ኢትዮጵያን የሰራ ህዝብ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ሲሰራ ህልቆ መሳፍርት የሌለው ህዝብ መስዋእት ሆኗል፡፡ አገር በመጠበቅ እንቅልፍ አልባ ሆኖ የቀረ ህዝብ ስለሆነ ለዚህ እንቅልፍ አጥቶ ለኖረባት አገር ልዩ ፍቅር አለው፡፡ ሲዋጋላት፣ ሲደማላት፣ ሲሞትላት የኖረች አገር ናት፡፡ ከደሙ አፍስሶ፣ ከአጥንቱ ከስክሶ በላብና እምባው ለውሶ የሰራት አገር ናት፡፡ አጥንቱ አጥር፣ ደሙ ምልክት ነው፡፡ በየዘመናቱ ሊጠብቃትና ሊዋጋላት ግድ ስለነበር ራሱን ረስቶ ህይወቱን በፍቅሩ ለውጧል፡፡ ለሰው መኖርን ረስቶ፣ እንደ ሰው መኖርን ዘንግቶ ለዚህች አንድነት ለተባለች አስተሳሰብ ብቻ መኖር ከጀመረ ሽህ አመታት አለፉ፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት የተባለውን ሀሳብ አለቅጥ ከማፍቀሩ የተነሳ ወደ ሀይማኖትነት የተቀየረበት ህዝብ ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያን አንድነት አጥብቆ ይሻል፡፡

አማራ የኢትዮጵያ አንድነት ጽንሰ ሀሳብን የትልቅነት ምኞቱን የቋጠረባት ከረጢት ናት፡፡ ለዘመናት ትልቅ፣ ሀያል አገር ለመሆን ብዙ ተመኝቷል፡፡ በየዘመናቱ የከፈለው መስዋእትነት ለሀያልነት እና ታላቅነት እንደሆነ ሲያስብ ኖሯል፡፡ ይሄንን ምኞቱን እውን የሚያደርግለትም አንድነት እንደሆነ ያምናል፣ ያውቃልም፡፡ አንድ አገር፣ አንድ ህዝብ፣ የተባበረ ህዝብ፣ ሰፊ መሬት ለሀያልነት መሰረት እንደሆኑ ያስባል፡፡ ስለዚህ ምኞቱ ይሳካ ዘንድ አንድ አገር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህም አንድነትን አጥብቆ ከነፍሱ ይወዳል፡፡

አማራ ስለኢትዮጵያ አንድነት ድንጉጥ ሆኗል፡፡ የሚወዳት እና የሚሳሳላትን ኢትዮጵያ ላለማጣት ይባትታል፡፡ ገንጣዮችን ያቆላምጣል፣ አኩራፊዎችን ይለማመናል፣ የበደሉትን ካሳ ይከፍላል፡፡ ኢዮብን የሚያስንቅ ትግስት ያሳያል፡፡ እያበላ ይራባል፡፡ እያጠጣ ይጠማል፡፡ የሚጠሉትን ጎጆ በብርሀን እየሞላ የእሱን ቤት በጨለማ ያስውጣል፡፡ ወደፊት መሄድ ትቶ እኩል ለመሆን ወደኋላ ይጓዛል፡፡ ሲረግሙት ይመርቃል፡፡ ሲጠሉት ይወዳል፡፡ ተበድሎ ይክሳል፡፡ አስቀይመውት ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ዛሬን እየቀሙት ነገን ተስፋ ያደርጋል፡፡ ሁሉ እያለው ምንም የሌለው ሆኗል፡፡ ይሄ ሁሉ ለአንድነት፣ ለአንዲት ኢትዮጵያ የሚከፍለው ዘላለማዊ ክፍያ ነው፡፡ ከፍሎ አይጨርስም፡፡ ተከፋዮችም አይረኩም፡፡ አማራ በትክክል ይገለጽ ከተባለ አመድ አፋሽ በደንብ ይገልጠዋል፡፡ ወርቅ ያበድራል፤ ጠጠር ይመለስለታል፡፡ ወርቅ ለማበደር አልታከተም፣ እፋሽ አመድ ለመቀበልም ደከመኝ አላለም፡፡

አማራ የኢትዮጵያ አንድነት ለሚላት ጽንሰ ሀሳብ ወይም ሀይማኖት ቢገዛላት የሚደንቅ አይደለም፡፡ አንድነት መልካም ነው፡፡ በአንድ አገር እንደ ሰው እያሰቡ መኖር በጎ ነው፡፡ ትልቅ አገር መመኘትም አይከፋም፡፡ አንድነት አስፈላጊ ነው፡፡ ገንዘብ ባለበት በዚያ ልብ አለና አማራ ዋጋ የከፈለላት አገር ስለሆነች ሊወዳትና ሊንሰፈሰፍላት ግድ ነው፡፡ አማራ በኢትዮጵያ አንድነት ልቡ አለመጨከኑ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ጠቢቡ ሶሎሞን የሁለቱን ሴቶች ልጅ ለማካፈል ቢላ ሲያነሳ ያልወለደችው ልጁ ተከፍሎ ይሰጠኝ አለች፡፡ የወለደችው ግን ልጀ ከሚሞት እሷ ትውሰደው አለች፡፡ አማራና ኢትዮጵያም እንዲህ ናቸው፡፡ ስለበሉባት እንጅ ስላልሞቱላት፣ ደማቸውን ስላልገበሩላት የኦሮሞና ትግሬ ብሄረተኞች እንደ ዶሮ ሊገነጣጥሏት ቢላ ይዘው ይዞራሉ፡፡ አማራም ከምትገነጣጥሏትስ እኔ ይቅርብኝ፣ ብሏት ጠጧት፣ እኔንም ከፈለጋች አጥፉኝ፣ ብቻ አገሪቷ ትኑር፤ ያለእኔም ቢሆን ትኑር ይላል፡፡ በተለይ የትግሬ ሊቃን አገርን ለማጥፋትና ለመበተን ጽናት በታሪክ ውስጥ ሳይቋረጥ ይልቅም ተባብሶ መቀጠሉን በገሀድ እያየን ነው፡፡
Abere wrote:
15 Nov 2022, 09:42
እንደተረዳሁት ከሆነ ይህን የጻፈው ሰው እራሱ አሉቧልታ የሚዘራ እንጅ ስንጥር መረጃ እንኳን ሰብስቦ መሰነድ አልቻለም። ይህን ትችት የሰነዘረው ግለሰብ ስለተጻፈ ብቻ በልማድ ሳይንሳዊ ይሆናል ሰዎችም ይቀበሉታ ብሎ በመገመት አማራን ኢላማ ያደረገ እና ያተኮረ ልብወለድ ነው። . . .

ይህን ብርቅ የጥናት ውጤት ለታላቁ ኣጼ ሱስንዮስና ለልጃቸው ለአጼ ፋሲልም ክብር ስንል እንዲሁም ለጽሑፉ ደራሲ ለምስጋናው አንዱዓኣለም ምሕረቴም ያለንን ክብር ለመግለጽ እዚህ ብዙሃን ያውቁትና ይወያዩበት ዘንድ ከፊል ይዘቱን ኣጋርተናችኋል። :mrgreen:

Abere
Senior Member
Posts: 13896
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by Abere » 18 Nov 2022, 09:58

ይህን ማስገንዘብያ ደራሲው ስለተጻፈ ብቻ ጽሁፉ በሳይንሳዊ መንገድ የተጠናቀረ ፥የተመዘነ ወይም የተረጋገጠ ነው ማለት በፍጹም አይቻልም። መደበኛ የምርምር እና ጥናት አካሄድ እና መስፈርቶችን የግድ ስለማሟላቱ የሚያረጋግጥ አቻ (peer reviewers) የምርምር እና ሳይንሳዊ ቡድን ትችት እና ግምገማ ማለፍ አለበት - በተለይም እንደዚህ አይነት ዐብይ ጉዳዮችን በማቅረብ። ሰይጣን ለአመሉ ከመጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅሳል ይባላል - ምክንያቱም አንድ ሁለት ከመጽሀፍ ቅዱስ እየጠቀሰ እስሩ የሚፈልገውን ተንኮል አልፎ አልፎ እንደ ጋሬጣ እሾህ የተክላል እና። እንድሁም የፓለቲካ አክቲቪስቶች እና የህዝብ ስሜት ኮርኳሪ-ነክ ሸቀጣሸቀጦችን አቅራቢ ጸሀፊዎች አንድት ነገር ጣል አድርገው ሌላ ውሸት ይደባልቃሉ - ይኸ የነገር መናጆ ይባላል። ለምሳሌ አንድ ገበሬ በግ ገበያ ለመሸጥ የምትሸጠውን በግ ብቻዋን አይነዳም - እምቢ አልሄድም ብላ ስለምትቀርበት ። ስለዚህ የግድ ቢያንስ ሌሎች 2 ወይም 3 በጎች መናጆ አድርጎ ገበያ ይነዳቸዋል - መናጆዎቹ ይመለሳሉ ለገበያ አላማ የታሰበችው ትሽጣለች። አንድ በቅረብ የተጻፈ ጽሁፍ ነበር። ደራሲው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ነው።የመጽሀፉ አርዕስት "የኦሮሞ እና የአማራ የዘር ምንጭ" ይላል።ይህ ጸሀፊ በርካታ እውነታዊ ታሪኮችን ይጠቃቅሳል - አጻጻፉ ድብልቅ ወይም ውጥንቅጥ ነው - ሳይንሳዊም ኢ-ሳይንሳዊም። ሙከራው አማራ እና ኦሮሞን ለማቀራረብ ነው - ህዝብ ለህዝብ ሳይሆን ሊህቃን ነን ባይ በጥባጮችን። ምክንያቱም እንደ እኔ ህዝብ ለህዝብ ተጣልቶ አያውቅም - የአራዊት ባህርይ ነው፡ የሰው ልጅ ለሰው ልጅ ያዝናል። ለማንኛውም ጸሀፊው አንድ ኢ-ሳይንሳዊ ተረተ ሲያቀርብ የኦሮሞ እና የአማራ ወላጂ እናት ገላዋን ስትታጠብ ከጣና ሃይቅ የወንድ መሻት(የዘር ፍሬ ) ማህጸኗ ውስጥ በውሃ አማካኝነት ገብቶ ነው ይልሃል። ተዐምር(miracle) እና ሳይንሳዊ ሀቅ(fact/data) አብረው አይሄዱም። ግን ብዙ ሰዎች ሀሳቡን ገዝተውታል። ጸሀፊው የአንባቢውን የግንዛቤ ደረጃ እየመዘነ የሚያቀርብ ከሆነ ይህ ለሳይንስ አስቸጋሪ ነው። This more like marketing strategy, the author synthesizes to his or her target audience eager for sensational characters in stead of the boring facts. And the claims in the abstract is just a pure promotion to his/her target readers of consumers.

Meleket wrote:
17 Nov 2022, 06:28

"የግዮናዊነት" ደራሲው ምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴ “መሪ ኣንቀጽ” ባለው አርእስት ስር ስለመጸሐፉ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል
ይህንን መጽሃፍ ሳዘጋጅም አብዛኛውን ማስረጃ የወሰድኩት በሳይንሳዊ መንገድ የተጻፉ ሰነዶችን ተገቢ እና ትክክለኛ በሆነ አግባብ በማጣቀስ ነው። በሳይንሳዊ መድብሎች ያልታተሙ የአገር ውስጥ ጸሀፍት የስራ ውጤቶችም ጥቅም ላይ መዋላቸው ሳይዘነጋ፡፡ እናም መጽሀፉ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ እና ብርቱ ጥረት የተደረገበት የጥናትና ምርምር ውጤት ነው፡፡

Meleket
Member
Posts: 4594
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኢትዮጵያን የለከፏት ሦስት ክፉ በሽታዎች:- 1) ጴንጤ 2) ወያኔ 3) ኦነግ

Post by Meleket » 22 Nov 2022, 05:15

ወዳጃችን Abere እውነት ነው አንዳንዱ የጽሑፉ ይዘት ኢሳይንሳዊ ኣገላለጽ ሊኖረው ይችላል። ቢሆንም ግን ጸሐፊው እንዲህ ኣይነቶችን ዐብይ ጉዳዮችን በድፍረት ማቅረቡ ጀግንነትም ነው ምክንያቱም ህዝቤ ያለውን ኣካል ለመታደግ ወጥኖ ያደረገው በመሆኑ። የፕሮ ፍቅሬ ቶሎሳም ኢሳይንሳዊ አገላለጾች ያሉት ጽሑፍ መሆኑን ፕሮ ጌታቸው ኃይሌ የሰጡትን ግምገማ ተመልክተን ነበር። ይሄን የምስጋናውን ደግሞ እስቲ ምሁራን አስተያየት ስጡበት። ለማንኛውም አሁንም ከመጸሐፉ ስለ "ክሹፉ ትውልድ" ያለውን እስቲ እንመልከት፦
“ክሹፉ ትውልድ፤ ሊማርም ሊያስተምርም አልቻለም” በሚለው ንኡስ አርእስት ደራሲው በገጽ (399-400)

በአማራ ውስጥ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ክሹፍ ትውልድ ተከስቷል፡፡ አጥፍቶ የጠፋ እና እስካሁን እያጠፋ ያለ ትውልድ፡፡ ከአባቱ የተቆራረጠ፣ በራሱ ያልቆመ፣ ለልጁ አባት መሆን ያልቻለ ትውልድ፡፡ በጣት ዱካ የሚፈርሙ አባቶቻቸው አስተማሯቸው፣ ገና ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ አባቶቻቸው ላይ መጮህና ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡ የአገር፣ የህዝብ ችግር ይፈታሉ የተባሉት ተማሪዎች ራሱን ህዝቡን የችግሩ ተጠያቂ አደረጉት፡፡ የችግሩ ተጠያቂ አድርገውትም አላበቁ፣ እነሱ የፈጠሩት አዲስ ችግርም ተጠቂ አደረጉት፡፡ ተማሪዎች ተብለው በህዝቡ በመከበራቸው ያንን ክብር ለመጥፎ አላማና ህዝቡን ለማጥፋት ተጠቀሙበት፡፡ ከአማራው ባህል በተለይ፣ ከኢትዮጵያ ባህል በጠቅላላው የማይገጥም፣ የአገሪቷን ችግር መነሻ ያላደረገ የምስራቅ አውሮፓ አስተምሮህት በማርክሲስዝም-ሌኒንዝም ሰበብ ይዘው ገብተው አገር አፈረሱ፡፡ እንደ ሸቀጥ ከውጭ በገባ አስተሳሰብ አገሪቱን ካፈረሱ በኋላም እነሱ ወጡ፡፡

የኤርትራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ተማሪዎች የሚፈልጉትን ያውቁ ነበር፡፡ አማራውን በመወንጀል፣ ከአማራው ነጻ በመውጣት የየራሳቸው አገር መመስረት፡፡ የየራሳቸውን አገር ለመመስረትም ሲነሱ ፕሮግራሞቻቸው (በተለይ የህወሀት እና የኦነግ) በአማራው መቃብር ላይ ነበር፡፡ አማራን ተቀራምተው የየራሳቸውን አገር ለመፍጠር የተማሪዎች እንቅስቃሴን መጠቀሚያቸው አደረጉት፡፡ የእነዚህ አጫፋሪ የነበረው ደግሞ አሳፋሪው ይሄው የጠፋው የአማራ ትውልድ ነው፡፡ አባቶቹ ያለፉበትን መከራ በቅጡ ሳይረዱ፣ የተጠቀሱት ብሄረተኛ እንቅስቃሴዎች ግብ አማራን ማጥፋት መሆኑን እያወቁ በተራማጅነት ስም አጫፈሩ፣ አጀቡ፣ ደገፉ፡፡ ራሱን ሊያጠፉት ሲያደቡ የመጥፊያ ጉድጓዱን የቆፈረ ትውልድ ቢኖር ይሄ በተለምዶ የ1960ዎቹ ትውልድ የሚባለው ትውልድ ነው፡፡ በኤርትራ፣ ትግሬና ኦሮሞ ብሄረተኞች መጠቀሚያ በመሆንም የራሱ ወላጅ አማራ ላይ ዘመተበት፣ ምድሪቷንም የደም አበላ አደረጋት፡፡

ይሄ ትውልድ በተሳሳተ መንገድ ሄዶ አባቶችን የአውሬ ራት አድርጓል፡፡ በዚህም ስራው ኤርትራ እንድትገነጠል በተዘዋዋሪ ሚና ተጫውቷል፣ የትግሬ ብሄረተኞች ከኤርትራ የተረፈችውን ኢትዮጵያ እንዲቆጣጠሩ አስተዋጽኦ አድርጓል፣ የኦሮሞ ብሄረተኞች ጎልምሰው አሁንም ድረስ ከባድ ስጋት እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ከሁሉም በከፋ ሁኔታ የአማራ ህልውና አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል፡፡ በተለይ ህወሀት አማራን ለማጥፋት ሰነድ ማዘጋጀቱን እንኳ እያወቀ ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታክል አላሰበም፡፡ ከእነዚህ ይልቅ ደርግ ሲመጣ እና የነገሮችን አዝማሚያ ገምግመው “ይሄ ነገር አማራን ለማጥፋት ነው” ብለው ተቃውመው፤ ተታኩሰው፤ የተሰውት ደጃዝማች ፀኃዩ ዕንቁ ስላሴ በቅድሚያ ለአማራ የቆሙ ሰው ያደርጋቸዋል፡፡

ይህ ትውልድ አባቶችን ገደል በመክተት አገር ማፍረሱ ሳያንስ፣ አማራውን ለ50 አመታት የጠባብና አውዳሚ ብሄረተኞች መጫወቻ አድርጎ አገሪቷን መና ማስቀረቱ ሳይበቃው ዛሬም አማራው ጨርሶ ካልጠፋልኝ በሚል አቋሙ እንደጸና ነው፡፡ አዲሱን የአማራነት እንቅስቃሴ በመቃወም የውግዘት ናዳ ለማውረድ ማንም አልቀደመው፡፡
በ60ዎቹ የለመደውን ጠልፎ የመከስከስ ፖለቲካ በተግባር ላይ ለማዋል ሲነሳም ወፍ አልቀደመችውም፡፡ ይሄ ትልድ እንደገና የአማራነት አብርሆታዊነት እንቅስቃሴ ውስጥ አንሰራርቶ በመግባት አላራምድ ብሎ መታየቱ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ከስህተቱ የማይማር፣ ከአባቶቹ አምስት ሳንቲም ጸባይ ያልወረሰ ትውልድ ነው፡፡ ላደረጉት ሁሉ መጸጸትና ንስሀ መግባት ነበር የሚጠበቅባቸው፡፡ በተቃራኒው መሪ እና አስተማሪ አልባ የሆንነው የአማራ ወጣቶች በራሳችን እንዲሁ ተነሳስተን ራሳችን ለማትረፍ ለምናደርገው እንቅስቃሴ ዋናው እንቅፋት ሆኖ የተገኘው ይሄ ትውልድ ነው፡፡ የአማራውን ችግር በመረዳት ደርግ ውስጥ የነበሩት እና በተአምር የተረፉት አማሮች በብዙ እጥፍ ይሻላሉ፡፡ የተወሰኑት ጸጸትም አለባቸው፡፡ ለእነሱ ክብር አለን፡፡ ኢህአፓ ውስጥ ከነበሩት ግን የአማራውን ችግር ተረድተው ወጣቱን የመደገፍ አዝማሚ ያሳዩት ውስን ናቸው፡፡ በጣት የሚቆጠሩ፡፡

ይህ ክሹፍ ትውልድ በተማሪነቱ እንቅስቃሴ ወቅት አማራውን እንደጨቋኝ ብሄር ስለፈረጀ በውስጡ አማራ ለሰራው በደል ይቅርታ መጠየቅ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ በዚህ የዝቅተኛነት እና ራስን የመጥላት ባህርይውም “አማራ የለም” የሚለውን የከንቱዎች ልፍለፋ አንደኛ አራጋቢ ሆኖ አማራውን እጅና እግሩን አስሮ ያስደበደበ ነው፡፡ ራሱን ሲከስ የሚኖር ትውልድ በመሆኑ ለአማራ መናገርን እንደ ትልቅ በደል ይቆጥራል፡፡ አማራው አሁን የሚደርስበት ግፍ በታሪክ የሰራው ብድራት እየተመለሰለት ነው ብሎ ያምናል፡፡ አማራን መኖሩን የሚያምነው ደግሞ በድሏል እና መካስ አለበት ለማለት ነው፡፡ ከዛ ውጭ ግን አማራ ተበደለ ሲሉት “አማራ እኮ የለም” ነው የሚለው፡፡ አማራ ሌሎችን በድሏል ብሎ ስለሚያምን ለወጣቱም ያንን በሽታውን ለማሸከም ቀን ተሌት ደፋ ቀና ሲል ይውላል፡፡ እስካሁን በታዩት አመታት (ከፕሮፍ. አስራት ዘመን ጀምሮ) አማራነትን ከትግሬ፣ ኦሮሞ ብሄረተኞችና የደቡብ ሊቃን ባልተናነሰ መልኩ ተዋግቷል፡፡ እንደ አዲሱ ትውልድ አካል ሲታሰብ አውራሽ አልባ ሆኖ መገኘት ቅሬታን ይፈጥራል፡፡ ሆኖም አዲሱ የአማራ ትውልድ ራሱን በራሱ ቀርጾ የራሱን የወደፊት በራሱ እጆች መጨበጥ ይገባዋል፡፡

Abere wrote:
18 Nov 2022, 09:58
ይህን ማስገንዘብያ ደራሲው ስለተጻፈ ብቻ ጽሁፉ በሳይንሳዊ መንገድ የተጠናቀረ ፥የተመዘነ ወይም የተረጋገጠ ነው ማለት በፍጹም አይቻልም። መደበኛ የምርምር እና ጥናት አካሄድ እና መስፈርቶችን የግድ ስለማሟላቱ የሚያረጋግጥ አቻ (peer reviewers) የምርምር እና ሳይንሳዊ ቡድን ትችት እና ግምገማ ማለፍ አለበት - በተለይም እንደዚህ አይነት ዐብይ ጉዳዮችን በማቅረብ። . . . አንድ በቅረብ የተጻፈ ጽሁፍ ነበር። ደራሲው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ነው።የመጽሀፉ አርዕስት "የኦሮሞ እና የአማራ የዘር ምንጭ" ይላል።ይህ ጸሀፊ በርካታ እውነታዊ ታሪኮችን ይጠቃቅሳል - አጻጻፉ ድብልቅ ወይም ውጥንቅጥ ነው - ሳይንሳዊም ኢ-ሳይንሳዊም። ሙከራው አማራ እና ኦሮሞን ለማቀራረብ ነው - ህዝብ ለህዝብ ሳይሆን ሊህቃን ነን ባይ በጥባጮችን። ምክንያቱም እንደ እኔ ህዝብ ለህዝብ ተጣልቶ አያውቅም - የአራዊት ባህርይ ነው፡ የሰው ልጅ ለሰው ልጅ ያዝናል። ለማንኛውም ጸሀፊው አንድ ኢ-ሳይንሳዊ ተረተ ሲያቀርብ የኦሮሞ እና የአማራ ወላጂ እናት ገላዋን ስትታጠብ ከጣና ሃይቅ የወንድ መሻት(የዘር ፍሬ ) ማህጸኗ ውስጥ በውሃ አማካኝነት ገብቶ ነው ይልሃል። ተዐምር(miracle) እና ሳይንሳዊ ሀቅ(fact/data) አብረው አይሄዱም። ግን ብዙ ሰዎች ሀሳቡን ገዝተውታል። ጸሀፊው የአንባቢውን የግንዛቤ ደረጃ እየመዘነ የሚያቀርብ ከሆነ ይህ ለሳይንስ አስቸጋሪ ነው። This more like marketing strategy, the author synthesizes to his or her target audience eager for sensational characters in stead of the boring facts. And the claims in the abstract is just a pure promotion to his/her target readers of consumers.


ይህን ብርቅ የጥናት ውጤት ለታላቁ ኣጼ ሱስንዮስና ለልጃቸው ለአጼ ፋሲልም ክብር ስንል እንዲሁም ለጽሑፉ ደራሲ ለምስጋናው አንዱዓለም ምሕረቴም ያለንን ክብር ለመግለጽ እዚህ ብዙሃን ያውቁትና ይወያዩበት ዘንድ ከፊል ይዘቱን ኣጋርተናችኋል።:mrgreen:

Post Reply