Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40205
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ፣የግብጽ ሕይወት፣ ብርሃን ባይኖር ግብጽ በጭለማ ትኖር ነበር ! አባይ ባይኖር ትጠፋ ነበር !! ግብጽ ያለ ኢትዮጵያ ሰውነት ያለ ነፍስ ማለት ነው !!!

Post by Horus » 04 Jun 2020, 01:49

Naga Tuma,
ፒራሚድ በእስራኤል እስሌቮች ጉልበት ተሰራ የሚለው ውሸትና ተረት በሳይንስ ተሽሮአል ። በአንድ አምላክ ማምለክ የፈለሰፉት ግብጾች እንጂ ይሁዲዎች አይደሉም።
የሙሴ ሚቶሎጂ ተረት ነው ። ሙሴ ማለት ልጅ ማለት ነው። ሙሴ በቅርጫት ወስጥ አባይ ላይ ስለ ተጣለው ህጻን ሌጀንድ ተከታተል። ሙሴ ቀይ ባህርን በዱላ ከፎል አልተሻገረም ። ችግሩ አበሻ መማርም መመራመርም አይፈልግም ። ሰነፍ ሕዝብ ነው። ከዚህ በታች አንድ ጥቁር አመሪካዊ ያደረገውን ምርምር ስማ !! ኬር

Naga Tuma
Member+
Posts: 6852
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: አባይ፣የግብጽ ሕይወት፣ ብርሃን ባይኖር ግብጽ በጭለማ ትኖር ነበር ! አባይ ባይኖር ትጠፋ ነበር !! ግብጽ ያለ ኢትዮጵያ ሰውነት ያለ ነፍስ ማለት ነው !!!

Post by Naga Tuma » 05 Jun 2020, 22:33

ሆረስ፥

በኣንድ ኣምላክ ማመን ጥንት ጊዜ ግብጽ ዉስጥ መጀመሩ በሰፊዉ የተዘገበ ነዉ፣ ልክ ነህ። ይህን ግብጽ ዉስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የጀመረዉ ፈረኦ ኣክናተን ነዉ።

ኣህመድ ኦስማን ኋላ ሙሴ የተባለዉ ፈረኦ ኣክናተን የነበረ ነዉ ብሏል። ይህን የሚቃረን ታሪክ እስከ ኣሁን ኣልሰማሁም። ይህ ማለት በኣንድ ኣምላክ ማመንን ጥንት ጊዜ ግብጽ ዉስጥ የጀመረዉ ሙሴ ራሱ ፈረኦ ኣክናተን የነበረ ጊዜ ነዉ ማለት ነዉ።

ፈረኦ ሞስስ የሚባልም ነበረ። ሙሴ እና ሞስስ ይቀራረባሉ። ሞስስ ደግሞ ትርጉሙ ከሞኣ ጋር ይቀራረባል። ያ ማለት ከሞኣ ኣንበሳ ታሪክ ጋርም ይገናኝ ኣይገናኝ ጥልቅ ጥናት ልያስፈልግ ይችላል ማለት ነዉ።

ሙሴ እና ሙጬ ወይም ሙጫ ትርጉማቸዉ የሚገናኝ ከሆነ ሙሴ ሁለቴ ስሙን ቀይሯል ማለት ነዉ፣ ከሙሴ ወደ ፈራኮ ኣክናተን ካዛ መልሶ ወደ ሙሴ። ይህም ሊሆን ይችላል። ይህን ማረጋገጥ ከሰማነዉ ሌጀንድ ያለፋ ሳይንሳዊ ጥናት ያስፈልጋል።

ህብረተሰባችን በጭለማ ዉስጥ የኖረ ታታሪ ይሁን በብርሃን ዉስጥ የኖረ ሰነፍ ይሁን ለእኔ ግልጽ ኣይደለም። ሌጀንድን መርምሮ ሳይንሳዊ መንገድ መጀመር ወደ ብርሃን መዉጣት ነዉ።

ሙሴ ኣዲስ ሌጀንድ ቢጀምርም የሌጀንዱ ኣባት በመሆኑም ተወቅሷል። ልብ ማለት የምያስፍልግ ይመስለኛል።

ለቪድዮዉ ኣመሰግናለሁ።

ነጋን፣ ኬር።

Horus
Senior Member+
Posts: 40205
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ፣የግብጽ ሕይወት፣ ብርሃን ባይኖር ግብጽ በጭለማ ትኖር ነበር ! አባይ ባይኖር ትጠፋ ነበር !! ግብጽ ያለ ኢትዮጵያ ሰውነት ያለ ነፍስ ማለት ነው !!!

Post by Horus » 06 Jun 2020, 01:00

Naga Tuma,

ይህ ለጥናትህ ይረዳህ እንደ ሆነ አላቅም ። ሙሴ ማለት ምን እንደ ሆነ ያለው በኢትዮፒክ ቋንቋ ውስጥ ነው። ሞሳ የሚባል ቃል ሰምተው ከሆነ ልጅ ማለት ነው። እላም ወልዳ ልጇ ሞሳ እንለዋለን። ሞሳ ትንሽ የክብት ልጅ ማለት ነው። ይህን ከጠረጠርክ ጎል ማሳ ምን ማለት እንደ ሆነ ተመራመር። ሙሴ ማለት ልጅ ማለት ነው።

ትክክል ብለሃል። ሙጬ (ዛሬ ጎንደር አካባቢ) በሰፊው ያለ ቃል ነው ። ልጄ ማለት ነው ። በሸዋ ወልዴ እንላለን፣ በጎንደር ሙጬ ይላሉ ። ሙጬ ማለትና ሙሴ፣ ሞሼ ማለት ሁሉም አንድ ስረ ቃልና ስነ ቃል ነው ያላቸው።

ሙጣ ማለትም ትሽሽ ልጅ ማለት ነው ።

እኔ ኦሮሞኛ ተናጋሪ ስላልሆንኩ በውል መደምደም ያዳግተኛል እንጂ ሙጬ ማለት እና ሙጫዮ (ኦሮሞፋ) አንድ ቃል ይመስሉኛል ! ኬር

Horus
Senior Member+
Posts: 40205
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አባይ፣የግብጽ ሕይወት፣ ብርሃን ባይኖር ግብጽ በጭለማ ትኖር ነበር ! አባይ ባይኖር ትጠፋ ነበር !! ግብጽ ያለ ኢትዮጵያ ሰውነት ያለ ነፍስ ማለት ነው !!!

Post by Horus » 08 Jun 2020, 02:09

የእኔ ፊሎሎጂ እንደ ሚያሳየው የበጃ ሕዝብ የበጌምድር ሕዝብ የግብጽና የከርሚያ የኑቢያ ህዝብ ናቸው ። ግብጽ ኢትዮጵያዊ ስልጣኔ ነው ።

Post Reply