ከአፍሪካ የተለያየ አገራትና መገናኛ ብዙኀን ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በስልክ ቃለ መጠይቅ በሰጡበት ወቅት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የሚቀርበው ትችትና ወቀሳ ከተሰሳተ መረጃ በመነሳት ነው ብለዋል።
ማይክ ፖምፒዮ አሜሪካ ምንም እንኳ ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ ብታቋርጥም ከመቼውም ጊዜ በላይ በዓለም አቀፍ ጤና ላይ ገንዘቧን ማፍሰስ ትፈልጋለች ብለዋል።
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ፖምፒዮ ማንም አገር አድርጎትም የማያውቀውንና ሊያደርገውም በማይችለው መልኩ ለዓለም አቀፍ ጤና እንታገላለን ብለዋል።
ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አገራቸው በአፍሪካ ብቻ በኮሮናቫይረስ መከላከል ላይ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ 170 ሚሊየን ዶላር ለማፍሰስ በጅታለች ብለዋል።
ፖምፒዮ አክለውም የውጪ አገር መንግሥታትና መገናኛ ብዙኀን ስለ መንግሥታቸው የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ደግሞ የአፍሪካ አገራትን ትንሽ እርዳታ እየሰጧቸው ወደማይወጡት ብድር እየከተቷቸው ነው ሲሉ ተችተዋል።

በዩኬ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 360 በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ሚንስቴር እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ ከተያዙት መካከል 21,092 ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀ።
ከሞቱት መካከል የጤና ባለሙያዎች የሚገኙበት ሲሆን እነዚህም 82 የብሔራዊ ጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) አባላት፣ 16 ደግሞ እንክብካቤ ሰጪ ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።
በዩኬ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 360 በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
በተጨማሪም " ከነገ ጀምሮ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) ሌሎች አገልግሎቶች፣ እንደ ካንሰርና የአእምሮ ጤና ያሉት፣ መሰጠት ይጀምራሉ" ተብሏል።
"የጤና አገልግሎቶቹ ሙሉ በሙሉ መሰጠት የሚጀምሩት መቼ እንደሆነ የሚወሰነው በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ከታየ በኋላ ነው" ብለዋል የጤና ሚኒስትሩ ሃንኩክ።





