Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

ቴዲ አፍሮ, ጃኪና ሌሎችም ስለ ትግርኛ ቁንጅና ሲዘፈኑ ሁሌ "አስመሪና- ሽኮሪና - ፊያሜታ - ፊዮሪና ጉዋል አስመራ-1080 ጠብቂኝ-ዳህላክ ላይ ልስራ ቤቴን" እያሉ ስለ ኤርትራ ብቻ ።

Post by MatiT » 09 Jan 2020, 22:40

የመቐለ ቆንጆ!

የኢትዮጵያ የመሃል አገር ድምጻውያን (ለአብነት ቴዲ አፍሮ እና ጃኪ እና ሌሎችም) ስለ ትግርኛ ተናጋሪ ኮረዶች ቁንጅና ሲዘፈኑ ብዙውን ጊዜ "አስመሪና- ሽኮሪና - ፊያሜታ - ፊዮሪና ጉዋል አስመራ - 1080 ጠብቂኝ - ዳህላክ ላይ ልስራ ቤቴን" ሲሉ እንሰማለን። አንድም ጊዜ ስለ "መቐለ ቆንጆ" ሲዘፍኑ ሰምቼ አላውቅም። መቼም የአስመራ እና የመቐለን ኮረዶች በመልክ ቁንጅናም ሆነ በጠባይ ቁንጅና ማበላለጥ አይቻልም። የየራሳቸው ልዩ የቁንጅና ተፈጥሮ እና የቁንጅና ባህርያት ይኖራቸዋል። ይህ አጠቃላይ እውነት ነው።

እንዲያ ከሆነ ታዲያ የተጠቀሱት የመሃል አገር ድምጻውያን አይኖች የመቐለን ኮረዶች ቁንጅና ማየት ያልቻሉበት ምክንያት ምን ይሆን?

ምርምር አያስፈልገውም።
ጉዳዩ ያበደ ፖለቲካ ነው።

የመቐለ ሰዎች ወደ መሃል አገር ይዘውት የሄዱትን ፖለቲካ ስለጠሉ ሁሉን ነገር አብረው ጠሉ። ስለ አስመራ ቆነጃጅትስ ለምን ዳጋግመው ይዘፍናሉ? ይህም ፖለቲካ ነው። ከአስመራ ቆነጃጅት ጀርባ የሰማያዊው ባህር ውበት ተንጣሎ ይታያቸዋል። ይመስለኛል!!

(ይህን ትእዝብቴን መንደፈራ ላይ በተደረገ አንድ የወጣቶች ሴሚናር ላይ ገልጬው ነበር። ይህን ለመግለጽ የተገደድኩት የአስመራ ኮረዶች ለቴዲ እና ለጃኪ ዜማዎች ያላቸውን የዋህ ፍቅር በመታዘቤ ነው። በ'ውነቱ ይህ አባባሌ ስህተት ቢሆን እመርጣለሁ።)
ተስፋዬ ገብረአብ

Horus
Senior Member+
Posts: 40074
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮ, ጃኪና ሌሎችም ስለ ትግርኛ ቁንጅና ሲዘፈኑ ሁሌ "አስመሪና- ሽኮሪና - ፊያሜታ - ፊዮሪና ጉዋል አስመራ-1080 ጠብቂኝ-ዳህላክ ላይ ልስራ ቤቴን" እያሉ ስለ ኤርትራ ብቻ

Post by Horus » 09 Jan 2020, 23:02

ተስፋየ ገብረአብ ይህን እንደ ቆዳ የደረቀው ቁሳአካል ፖለቲካ እንጂ ሴቶች ምን እንደሚወዱ የማያቅ፣ ኢቮሉሽን በወንድነቱ የሰጠውን ባህሪ በዘር ርዕዮቱ የተቀማ ወንድ ነው ማለት ነው !! ያሳዝናል ? ለምን የኤርትራ ሴቶች ቆንጆ ዘፈን ወደዱ ብሎ መቀየም፣ ያውም ላንድ ወንድ እጅግ አስገራሚ ባህሪ ነው። የቴዲ ሚስትኮ ግማሽ ኤርትራዊት ነች !!


Post Reply