Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በትግራይ ህዝብ ስም እናመሰግናለን!!!!

Post by Hameddibewoyane » 09 Jan 2020, 21:03

ህወሓት ፌደራሊስቶች ብላ በትግራይ ህዝብ ገንዘብ, በተደጋጋሚ ብዙ ፀረ ትግራይ ህዝብ የሆኑ ፖለቲከኞች ወጪያቸውን በመሸፈን ወደ ትግራይ ካንዴም ሁሌቴም እንዲጓዙ አድርጋለች። ከስብሰባው ተጠቃሚው ህወሓት የተባለ አሸባሪ ድርጅት እና ተላላኪዎችዋ ናቸው። ዛሬ ትግስቱ አወሉ ከፌደራሊስት ሃይሎች ነን ባዮች ራሱን አግልለዋል፣ ስለሆነም ፌደራል መንግስት ፀረ ለውጥ በሆኑት ሃይሎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ሊመሰገን ይገባል።

ከዚህ ቀጥሎ በትግራይ ህዝብ በጀት ወደ ትግራይ እየሄደ የትግራይን ህዝብ እኔ ነኝ የማውቅልህ የሚል ሁሉ የትግስቱ አወሉ መንገድ ካልተከተለ፣ ፌደራል መንግስት እርምጃ ሊወስድ ይገባል፣ እርምጃው እንደ ጋዜጠኛ ያየሰው ማሰር፣ ወይንም ደግሞ እንደ ትግስቱ አወሉ ከፎረሙ እንዲወጣ ብቻ ማድረግ ሳይሆን፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ሲባል፣ ወደ ትግራይ ተጉዞው ለትግራይ ህዝብ እኛ እናውቅላሃለን ለሚሉቱ በሙሉ ፌደራል መንግስት እርምጃ መውሰድ አለበት። ቀጣዩ እርምጃ ከፎረሙ ያላገለሉ እና አሁንም ወደ ትግራይ እንሄዳለን የሚሉ ግለሰቦች ሆኑ ቡዱኖች ላይ እርምጃ መውሰድ ሊሆን ይገባል።

ከነዚህ ውስጥ
ገነት ዘውዴ
ካሱ ኢላላ
ጋዜጠኛ ሳምሶም ማሞ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪው

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ የገባሀውን ቃል በተግባር እየፈፀምክ ስለሆነ እናመሰግናለን በርታ።