አጭቤው ያለፉትን ወስነው ነው የሚመጡት (ለውይይት አይደለም) በማለት ይፈርጅና መሆን የነበረበትን ሊገልጽ ሲሞክር ያቺን የደበቃትን ግን ላለማስነቃት ይቃትታል፡፡ እንፈትሸው እስኪ፡፡
አሁን ነው ለመጀመርያ ጊዜ up priori substance (ቀድሞ በተወሰነ ጭብጥ) ሳይኖር በፕሮሰስ እንስማማ የሚለው ነገር important (ጠቃሚ) የሆነው፣ ምክንያቱም ዴሞክራሲ እንደ ፓለቲካ ሥርዓት በአብዛኛው ፕሮሰስ ነው፡፡ የትም አገር ብትሄድ በዚያ ፕሮሰስ ላይ ስምምነት አለ ይላል፡፡ ከዚያ በኃላ የሚደረገው የፓለቲካ ውይይት በዚህ ስምምነት ነው፡፡ ስለዚህ መጀመርያ በፕሮሰስ ስምምነት ሳይኖር የሚደረግ ውይይት፤ ውይይት አይደለም ይላል፡፡ እስከ አሁን አጭቤው ያነሳው ነጥብ ጠቃሚና ልክ ሊሆን ይችላል እላለሁ፡፡
አጭቤው አሁን የገጠመን ለውጡ በመሰረት ሀሳብ ደረጃ (in principle) ይህን ይበል እንጂ አብዛኛው ፓለቲካ ውስጥ ያለው ሀይል በዚህ ፕሮሰስ ውስጥ ወደ ውይይት የገባ አይደለም እያለ ይከሳል፡፡ ደህና፤ እስከ አሁን ያለውን የብርሁኑ ነጋን ሀሳብ መልካም ነው ብዬ ልቀበል፡፡ ግን ቀጥሎ በማነሳው ሀሳብ ውስጥ የአጭቤውን ገመና ለማጋለጥ እገደዳለሁ፡፡
አጭቤው ብርሀኑ የኢትዮጵያ የፓለቱካ ችግር መነሻ ነው ብሎ የሚያስበው (ያደረገው) እሱን በሚመች ሁኔታ ከቀረታ በኃላ ነው፡፡ በጥሞና ተከተሉኝ፡፡
ቀድሞ ነገር ውይይት ያስፈለገው የፖለቲካን ችግር ለመፍታት ነው፡፡ ችግሩ ከተፈታ ደግሞ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ሀሰቡን ሽጦ ሊመረጥ/ላይመረጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ነጻ ሀገር እንዲመሰረት እሻለሁ ወይም አሀዳዊ ሕዝብና አማርኛን ብቻ ብሔራዊ ቋንቋ በሚሉት መካከል ወድድር በነጻነት ሊቀርብ ይችላል፡፡ ይህ እንዲሆን ግን በውይይት ሊፈታ የሚገባው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር ያለው የት ላይ ነው የሚለው ነው፡፡
አጭቤው ብርሀኑ ታሳቢ አድርጎ (intuitively) ለውይይት እንዲከፈት የሚሻው ታዲያ የኢትዮጰያን ማንነት/ምንነት በጋራ ለመረዳት በሚያስችል መልኩ የሚደረግን ውይይት ሳያጠቃልል ነው፡፡ እሱ የሚሻው በውይይት ሰበብ ሕገ-መንግስት መቀየር የሚያስችለው ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ይህን ደግሞ በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ አስቀድሞ ኢትዮጵያና ባንዲራዋ (ሉዓላዊነቷ) መነካት የለበትም የሚል ፖሊሲው ያሣብቅበታል፡፡ መጀመርያ በዚህም ላይ ፖለቲካ ድርጅቶች ተወያይተው መፍትሄ እንዲገኝለት ወይም በሕዝቤ ውሳኔ ይለይለት ቢባል ይኸማ … እያለ እንደሚቃመው አምናለሁ፡፡ ሕዝቤ ውሳኔ ግን ዓለም የሚስማማበት (እጭቤውም የጠቀሰው) ፕሮሰስ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ጥያቄው ታዲያ፤ አጭቤው ብርሀኑ የዚህ አይነት ሂደት ከሆነ የሚሻው ከሚከሳቸው ቀደምት መንግስታት አስተሳሰብ ጋር ምን ይለየዋል የሚለው ነው?
ስለዚህ የፓለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ሊተማመኑበት የሚገባ ወይም ሕዝቡ መፍትሔ እንዲሰጥበት ለውይይት መቅረብ ያለበት ችግር ያለው ኢትዮጵያ በሚለው ላይም ስለሆነ ያለገደብ ክፍት ሆኖ ወይይት ሊደረግ ይገባል ማለት ነው፡፡
በመሆኑም እንደ ፕሮሰስ አጭቤው የደበቃትን ለማጋለጥ ነውና ድርሻዬን አቅርቤያለሁ፡፡
Please wait, video is loading...