በሃሰት ታሪክ እና በሞያው እውቀት በሌላቸው ካድሬዎች የተዘጋጅ ነው:: የፈጠራ ታሪክን ጥላቻ የተሞላበት የታሪክ ማስረጃ የሌላቸውን ታሪኮች ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መማሪያነት ማዘጋጀት ወንጀል ነው።ሌላ ቁስል የሚፈጥር ወይም ቁስሉን በመነካካት ሌላ ቁርሾ የሚሻ የትናንቱን ጉዳት በእርቅና በይቅርታ ከማስቀረት ይልቅ የበለጠ ጥርስ መነካከስን የሚያበረታታ ባለመስማማትና በትችት የተበተነውን ውይይት በስምምነት ጸደቀ የሚል ሰፊ ፕሮፓጋንዳ መንግስት ሊሰራበት ተዘጋጅቷል።
አዲሱ የታሪክ ትምህርት የማስተማሪያ ሞጁል/ሰነድ የኃላ ቁስልን ያልተወ፣ የሚያጋጭ ፣ መልካም የታሪክ ጎንን የማያስተምር ፣ ለፖለቲካ አጀንዳና የግለሰቦችን ፍላጎት የተጻፈ ፣ ሚዛናዊነት የጎደለው፣ ታሪክን ለ አገር ግንባታ ለመጠቀም ያልፈለገ፣ አብሮነትን የጨፈለቀ ፣ ትውልድን የማያፈራ ፣ ከታሪክ እየተማረ ጠንካራ አገር መፍጠር የማያስችል ወዘተ የሚል ትችት በምሁራን ተሰንዝሮበታል። ባሕልን፣ እምነትን፣ የዜግነት ግዴታና የሙያ ክብር ያላገናዘበና ያላከበረ በተወሰኑ ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ የተሞላበት መሆኑ ምሁራን ይናገራሉ።#MinilikSalsawi
