የአማራ ባንክ ከ2.6 ቢልዮን ብር በላይ አክስዮን ሸጠ!! የአክስዮን ሽያጭ ሊያበቃ 15 ቀናቶች ብቻ ይቀሩታል!!
2.6 ቢሊዮን የተፈረመ ካፒታል።
ይህ በምስረታ ላይ ያለው የአማራ ባንክ ሪፓርት ነው፣
የተከፈለ ካፒታል ብር 2 ቢሊየን ሞልቷል።
የመሥራችነት ሽያጭ ግን እስከ ታህሳስ 30 እንደቀጠለ ነው።
የአክሲዮን ሽያጭ መግለጫ ከተነገረበት ነሃሴ 11 ዓ.ም. ጀምሮ ፥ ልክ በአራት ወሩ 2(ሁለት) ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አክሲዮን ተሽጧል።
የ120 ቀናት የአክሲዮን ሽያጭ ውጤት፤
ከ32,000 በላይ ባለአክሲዮኖች ተሳትፎ፤
በ6 የስልክ ጥሪ መሥተንግዶ፤
ያልታከቱ አምስት ግለሰቦች የሰልክ ጥሪ መቀበል አገልግሎት፤
በ10 የመንግስትና የግል ንግድ ባንኮች በመላ ሃገሪቱ የተካሄደው የሽያጭ ክንውን፤ እና
በ Amhara Economic Think Tank ጊዜውን የጠበቀ ሪፖርት አቅርቦት፥ እነሆ ዛሬ ላይ የተከፈለ ካፒታል ብር 2 ቢሊዮን እና የተፈረመ ብር 2.6 ቢሊዮን ካፒታል ደርሷል።
የአማራ ባንክ ፕሮጀክትን ሃሳብ የጠነሰሱ የ12ቱ ወጣት ሙሁራን፥ አክሲዮን የገዙ፥ የባንኩን መመሥረት በጉጉት የሚጠባበቁ፥ አደራጆች እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናፍቀው ባንክ ዕውን እንዲሆን ዛሬም ተግተን እንስራ።
የአማራ ባንክ ካፒታል ከፍተኛ መሆን የአንድ ፋይናንስ ተቋም ጥንካሬ ዋና መለኪያ ስለሆነ፥ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ከጅምሩ ተወዳዳሪ ሆኖ በመቅረብ በሃገር ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።
የ አክሲዮን ሽያጭ ክንውን በአጭር ጊዜ ይህን ያክል ካፒታል ውጤት ሲያስመዘገብ አማራ ባንክ የመጀመሪያው እንደሆነ፥ የተለያዩ ተቋማትና የሚዲያ አውታሮች መስክረውለታል።
ድንቅ አንድነት፤ አመርቂ የሽያጭ ክንውን፤ የተባረኩ የአደራጅ አስተባባሪዎች፤ ቁርጠኛ ባላክሲዮኖች።
ፈጣሪ በያላችሁበት ሰላሙን ያብዛላችሁ!!
Amhara Economic Think Tank
Your Back in Building Institutions!
https://www.facebook.com/amharathinktan ... 0685508947