Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sholagebya
Member
Posts: 494
Joined: 27 Oct 2014, 15:59

በሞጣ የደረሰው የመስጊዶችና የሙስሊም ምግብ ቤቶች ላይ የደረሰው ቃጠሎ የሚያሳዝንና አሳፋሪ ድርጊት ነው

Post by sholagebya » 22 Dec 2019, 20:54

በሞጣ የደረሰው የመስጊዶችና የሙስሊም ምግብ ቤቶች ላይ የደረሰው ቃጠሎ የሚያሳዝንና አሳፋሪ ድርጊት ነው :: ይህን ዜና ስሰማ መጀመሪያ ገምቸ የነበረው ወይ ወያኔ አለበለዚያ ደግሞ ኦነጎች ይሆናሉ ነበር :: ነገር ግን የቪዲዮ ክሊፑን ስመለከት ጉዱ ሌላ ሆኖ አገኘሁት :: ቁጥሩ ብዛት ያለው የከተማው ማኅበረሰብ የተነሳውን ቃጠሎ ተረባርቦ ለማጥፋት ከመሞከር ይልቅ, በዙሪያው ከቦ ልክ ትልቅ የሃብታም ሠርግ እንደተደረገ አሃይ ሎጋ እያሉ ሲጨፍሩ ማየት እጅግ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ቃጠሎው ያስነሱት እራሳቸው መሆኑን ያሳያል :: በዚህ ቃጠሎ ዙሪያ በጣም የታዘብኳቸው የአማራ አክቲቪስቶችንና ስዩም ተሾመን ናቸው :: 1ኛ / አብዛኞች የአማራ አክቲቪስቶች ቃጠሎውን ከአህመድ ጀበልና ከአክራሪ የኦሮሞ ፓለቲከኞችን ይወነጅላሉ :: ይህ ውሸት ብቻ ሳይሆን ቅንጣት ታክል መረጃ የለውም :: 2ኛ / ስዩም ተሾመ ደግሞ በአንዳፍታ የዩቲዩብ ዜናው ላይ ወያኔን ለመወንጀል ይሞክራል :: ይህም ቢሆን ስህተትና ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ካልሆነ በስተቀር ያቃጠሉት እራሳቸው የከተማው ሰዎች መሆናቸው ቪዲዮው ምስክር ነው :: ምንም እንኳን አንዳንድ የሙስሊም አክቲቪስቶች ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ከአሁን በፊት በሰጠው ቅስቀሳ ምክንያት ሊወንጅሉት ቢሞክሩም እሱ የሰጠው የቃጠሎው ምክንያት ግን በጣም ትክክል ሆኖ አግኝቸዋለሁ :: ስለዚህ በዚህ አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ቃጠሎ ሊያፍሩ የሚገባቸው 1ኛ / የአማራ አክቲቪስቶች 2ኛ/ ስዩም ተሾመ የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመልቀቅ ታኣማኒነቱን ( credibility ) አበላሽቶታል :: ከዚህ በኃላ ስለ ወያኔ የሚያወጣውን ዜና የውሸት ፈጠራ መሆኑንና : በዚህ የመስጂድ ቃጠሎ ወያኔ እንደፈጸመው አድርጎ ማቅረቡ ጠቅላላ የሚያወጣቸው ሁሉ ተራ ፕሮፓጋንዳ እንደሆኑ እንጂ እውነት እንዳልሆኑ ተረድቻለሁ ::


ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፌስቡክ ገጽ
ሞጣ ላይ የተፈጸመዉ ነገር አሳዛኝም፤ አሳፋሪም ነው። የሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቃጠሎ አደጋ ገጥሞት በምእመናን ርብርብ ቶሎ ሊጠፋ ችሏል። ነገሩን ከሞጣ ሙስሊሞች ጋር የሚያገናኘው ነገር አልነበረም። የሞጣ ሙስሊሞችኮ በአካባቢው ሁለቱን እምነቶች ሊያጣሉ የሚያስቡ አካላት መኖራቸውን ቀድመው ለክርስቲያኖችና ለመንግሥት ያሳሰቡ ናቸው። የጻፉት ደብዳቤ ምስክር ነው።
የአካባቢው መስተዳድር የሞጣን ሙስሊሞች ጥቆማ በቸልታ ተመለከተው። በዚህ መሐል ሞጣ ጊዮርጊስ ባልታወቀ ምክንያት የመቃጠል አደጋ ገጠመው። ጢሱን በጉልላቱ ላይ ያዩት ሰዎች አስቸኳይ ጥሪ በማቅረባቸው ቶሎ ርምጃ ሊወሰድ ቻለ።
ከዚያ በኋላ መስጊዶችን ማቃጠልና የሙስሊም የንግድ ተቋማትን ማቃጠል ተጀመረ። በሌላ አካባቢ የተቃወምነው ነገር ተገልብጦ ተፈጸመ። አሳፋሪ፣ አሳዛኝ። ''ችግር እንዳይከሠት ንቁ፤ አንዳንድ ነገሮች እያየን ነው'' ብለው ሲያስጠነቅቁ የነበሩ ሙስሊም ወገኖችን ባጎረስኩ ተነከስኩ ዓይነት የሞኝ ብሂል መጉዳት በሰማይም በምድርም ያስጠይቃል።
አሁን፦
1.እንረጋጋ
2.የአካባቢው መስተዳድር የሞጣ ሙስሊም ወገኖቻችን የሰጡትን ጥቆማ ለምን ቸል እንዳለው ክልሉ አጣርቶ ርምጃ ይውሰድ
3. አጥፊዎቹን በጋራ አጋልጠን እንስጥ
4. የጠፋውን በጋራ እንመልስ