"የዓድዋ ከተማ ወጣቶች ማሕበር ትናንት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ በዓረና ፓርቲ ላይ የሐይል እርምጃ እንዲወስድ ለትግራይ ክልል መንግስት (ህወሓት) ጥሪ አቅርቧል። ያቀረቡት ምክንያት ደግሞ "በ27 ዓመት የህወሓት የስልጣን ዘመን "ስናጣጥመው የነበረ ጣፋጭ ነፋስ ሊቀሙን ላይና ታች እያሉ ነው" የሚል ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በዓረና ፓርቲ አስተባባሪነት "የትግራይ ህዝብ ከላይ በሚላኩለት ፀጉረ ልውጥ ገዢዎች ሳይሆን ህዝብ ራሱ ከራሱ በመረጣቸው መሪዎች ሊተዳደር ይገባል" የሚል ዘመቻ ከፍተን ትግራይ ክልል በሙሉ ማነቃነቃችን ይታወቃል። በዚህ የፍትሕና የእኩልነት ዘመቻ የተደናገጡ የዓድዋ ሰዎች ከስልጣን እንዳይባረሩ በመስጋት የማስፈራርያ መግለጫ አውጥቷል። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ጠላት ማን እንደሆነ ግልፅ አድርገውልናል። በዓረና ሰዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ቢደርስ ተጠያቂዎቹ እነሱ እንደሚሆኑ ይታወቅ። ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን"
መምህር አብርሃ ደስታ
-
- Member
- Posts: 3890
- Joined: 25 Sep 2019, 02:42