


ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ/ (ኢትዮጵያዊ)? ታሪክን በትክክል ለማወቅ ለሚፈልግ ብቻ የተፃፈ!!
“ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራዊነት ተረት ነዉ ወይስ እዉነት ነዉ?
የኢሳያስ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቂ አባት አቶ አፈወርቅ አብርሃ ይባላሉ፣፣ እናቱ ወይዘሮ አዳነች በርሄ ይባላሉ፣፣ ልጆቻቸዉም
(1) አቶ አማረ አፈወርቅ (አፈወርቂ) (ይህ ስያሜ ኤርትራዊነትን ለማስመሰል ነዉ፣፣)
(2) አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ
(3) አቶ አማኑኤል አፈወርቅ
(4) አቶ ኤርሚያስ አፈወርቅ
(5) አቶ ዮናስ አፈወርቅ
(6) ወ/ሮ ጽጌረዳ አፈወርቅ
(7) ወ/ሮ አርዮን አፈወርቅ
ከኤርትራ ፕረዚዳንት ቤተሰብ በስተጀርባ ያለዉ ታሪክ፣- የኢሳያስ አባት አቶ አፈወርቅ የመጡት ከትግራይ ተምቤን ሲሆን ዘራቸዉ የኢትዮጵያ አካል ከሆነዉ ከአጋሜ አዉራጃ የተዉጣጣ ነዉ፣፣ የአቶ ኢሳያስ አባት ይሰሩ የነበሩት በትግራይ አስተዳደር ክፍለ ሃገር በመቀሌ መዲና ነበር፣፣ ጡሮታ እስከወጡ ም ድረስ በመሬት ንብረት ይዞታ ማሻሻያ ሚኒስቴር ዉስጥ ነበር የሚሰሩት፣፣ ጥቁር ሙሉ ልብስና ጥቁር ክራባት ለባሽ ተብለዉ ይጠሩ እንደነበር ይነገራል፣፣ (“ካንትሪ ጀንትል ማን”ተብሎ አንዳንዴ ከሚታወቀዉ ከጥቁር ሱፍ የተሰራ ክብ ቆብ ከራሳቸዉ አይለዩም ነበር፣፣ ጋዜጣም ከእጃቸዉ በፍጹም አይለዩም ነበር፣፣
በናታቸዉ በኩል የኢሳያስ አጎቶች፣- (1) ደጃዝማች ሰለሞን አብርሃ (2) ካፒቴን መኮንን አብርሃ (3) አቶ ሓጎስ አብርሃ ናቸዉ፣፣
የአቶ ኢሳያስ አጎት ደጃዝማች ሰለሞን አብራሃ በሃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት ማለት (በ1946 ዓ.ም) የወሎ እንደራሴ ሆነዉ ያገለገሉ ናቸዉ፣፣ በዚያ ጊዜ መቀሌ ከተማ ዉስጥ ተደራጅቶ የነበረዉ የባህል ቡድን አስመራን ከጎበኘ በሗላ ወደ ደሴ መጣ፣፣ እንደራሴዉ ደጃዝማች ሰለሞን ለክብር እንግዶቹ በተዘጋጀዉ የእራት ግብዣ ላይ ምስጋናቸዉን ለቡዱኑ ከገለጹ በሗላ እሳቸዉም ትግሬ መሆናቸዉን አንስተዉ የባህል ቡድኑ የትግራይ ባህላዊ ሙዚቃ እና ባህላዊ ዉዝዋዜ ለማስፋፋት ላደረገዉ አስተዋጽኦ አድናቆታቸዉ ገለጹ፣፣ በተጨማሪም የደጃዝማች ሰለሞን እናትም አጋሜ አዉራጃ ዉስጥ ተወላጅ ትግሬ መሆናቸዉን እና አባታቸዉም በትግራይ ክ/ሃገር ዉስጥ የተምቤን ተወላጅ መሆናቸዉን አንስተዉ ለባህል ቡድኑ ገልጸዉላቸዋል፣፣ የባሕር ሃይል ካፒቴን የሆኑት ካፒቴን መኮንን አብርሃ የኢቴጌ መኮንን ትምሕርት ቤት ተማሪ የነበረቺዉ የደጃዝማች ገብራይ ልጅን አግብተዉ ሦስት ልጆች እንደወለዱ ይታወቃል፣፣ አቶ ሐጎስ አብርሃም ቢሆን በአዲስ አባባ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የጥንት ተማሪ ሲሆን ለዚያዉ ተማሪ ቤት የእግር ኳስ ቡድን በረኛ ነበር፣ ሆኖም በበሽታ ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ ለጥቂት ጊዜ በብሔራዊ ባንክ ስራ ተቀጥሮ እየሰራ እንዳለ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ ይታወቃል፣፣
የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አያቶችና ሌሎች ዘመዶቻቸዉም - በሚመለከት፣-
በእናቱ በኩል የኢሳያስ አፈወርቂ አያት (የእናት እናት)ወይዘሮ መድህን “በራድ” ይባላሉ፣፣ በራድ (ተብለዉ በቅጥያ ስም የተጠሩበት ምክንያት ወ/ሮ መደህን በጠጅ ስራ ንግድ ተሰማርተዉ ይኖሩ ስለነበር “ጠጅ”ባካባቢዉ የሚቀዳዉ “በራድ” ተብሎ በሚታወቀዉ “ማንቆርቆርያ” ስለነበር ነዉ፣፣ መድህን የኢሳያስ እናት የወይዘሮ አዳናች በርሄ እናት ናቸዉ፣፣ ኢሳያስ የልጅነት ትምርቱ የተከታተለዉ በሴት አያቱ በወይዘሮ መድህን ተንከባካቢነት ነዉ፣፣ በቅንፍ የተጻፈዉ- ጌታቸዉ ረዳ)፣፣ ወ/ሮ መድህንም በትዉልዳቸዉ ዓድዋ ሲሆኑ፣ የፊታዉራሪ ኪዳነ መስቀል አጎት ናቸዉ፣፣ ፊታዉራሪ ኪዳነ የአቶ የማነ ኪዳነ (የየማነ ጃማይካ)-አባት ናቸዉ ይባላል ፣፣ ይህ እዉነት ከሆነ የአቶ የማነ ኪዳነ (ጃማይካ)-እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ “በኢትዮጵያ አጠራር” ወንድማማቾች ናቸዉ ናቸዉ፣፣ በአዉሮጳዉያኖች አጠራር ግን “የአጎት ልጆች ናቸዉ”፣፣ባጭሩ አሥመራ የሚገኙ አክራሪ ጠላቶች ናቸዉ የሚባሉት አብዛኛዎቹ የትግራይ ዝርያ የሆኑና በተለይ ከትግራይ በጠቅላላም ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ የስጋ ፣ የአጥንት እና የደም ቁርኝት ያላቸዉ ናቸዉ፣፣
የኢሳያስ አክስት (የኢሳያስ እናት እህት) ወ/ሮ ሃና ይባላሉ፣፣ የአቶ በላይ ባለቤት ናቸዉ፣፣ አቶ በላይ የዓድዋ ሰዉ ናቸዉ፣፣ እንደሚባለዉም ልጆቻቸዉ ስዊድን ሃገር ዉስጥ ይኖራሉ፣፣ በእናታቸዉ በኩል የአቶ ኢሳያስ አጎት የሆኑት ከዓድዋ ተወላጅ ከሆኑት በአሁኑ ጊዜ ጀርመን ዉስጥ የሚኖሩ ወ/ሮ ዘዉዴ የሚባሉትን ወልደዋል፣፣ ከላይ በተገኘዉ መረጃ መሰረት የአቶ ኢሳያስ ኤርትራዊነት ኤርትራ መሬት መወለዳቸዉ ብቻ ነዉ፣፣የአቶ ኢሳያስ ባለቤትም ወ/ሮ ሳባ ሃይለ ይባላሉ፣፣ ኤርትራዊት ናቸዉ፣፣
ይህ የሚያስገርም ነገር ነዉ፣፣ለእዉነተኛ ኤርትራዉያኖችና በጭፍን ኢሳያስን በጭፍን ለሚደግፉ ይህ ግልጽ የሚሆነዉ ከብዙ ዘመናት በሗላ ነዉ፣፣አእምሮአችን ዉስጥ ስለ ኤርትራዊዉ ፕረዚደንት ማንነት ታሪክ አዳዲስ ነገሮች እየታወቀ ሲመጣ ስሜታቸዉ እንደሚለወጥ አያጠራጥርም፣፣ ኤርትራዎቹ አስመልክቶ ልጆቻቸዉንና ሌላም ዓይነት መስዋእትነት ለሰላሳ ዓመታት የከፈሉ ፣የኢሳያስ ዉሸትና ተግባር በጣም አስነዋሪ፣ የክፍለዘመኑ የእዉነት ታሪክ ያለመሆኑ ቀስ በቀስ እየተረዱት እንደሚሄዱ እርግጠኞች ነን፣፣
እነኚህ ሰዎች ለሰላሳ ዓመታ ቤተሶቦቻቸዉ ይህንን አመጸኛ ሰዉየ ሥልጣን ላይ ለማቆት መስዋእትንት የከፈሉና የዉሸት የ ኤርትራዊነቱ ዜግነትበጭፍን ይደግፉ ነበር፣፣ ከዚህ በፊት አቶ ኢሳያስ ትግሬ ነዉ ያላልንበት ምክንያት ስለሟች ወላጆቹ ማንነታቸዉ በቂ መረጃ ስላልነበረንና ሕዝባችንን ባልተረጋገጠ ነገር ለማጣደፍ ወይም ስሕተት ነገር ላለመስጠት ስለፈለግን ነዉ፣፣ በጥብቅ ለማስገንዘብ የምንፈልገዉ ይህንን መረጃ የሰጡን ግለሰቦች ሰለ ኢሳያስ በቂ ዕዉቀት እንዳላቸዉ ስለቤተስቡና ዘመዶቹ በቂና ምስጢራዊ ዕዉቀት እንዳላቸዉ እናዉቃለን፣፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ ላላቸዉ ሰዎች በዚህ አጋጣሚ ለሁሉም ኤርትራዊያኖች የራሳቸዉ ጥናት አካሂደዉ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ እንማጸናለን፣
ምንጭ.= ጌታቸው ረዳ https://ethiopiansemay.blogspot.com/200 ... -post.html