Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ትኩስ መረጃዎች!

Post by Ejersa » 14 Nov 2019, 12:43

Please wait, video is loading...

ግራ የገባው ህወሓት በአንድ በኩል defacto state እሆናለሁ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱን የፓርቲው ልሳን ወይን መጽሄት ላይ አስነብቦናል። ይሁንና ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ግምባር የምትወደው ህወሓት እነ ትዕግስቱ አወሉ፣ አየለ ጫሚሶ፣ መስፍን ሽፈራው፣ ሰይድ ሚሊሻው፣ የአገው ሸንጎ፣ ቅዴፓ ወዘተ ጋር በአንድ ላይ ህዳር 14/15 ግምባር ፓርቲ ለመፍጠር ከወዲሁ የግምባሩን ማኒፌስቶ፣ መተዳደሪያ ደንብ እያዘጋጁ ይገኛሉ።

ህወሓት/ትህነግ የማታደርገውን defacto state ብትሆንም ሆነ ግምባር ብትመሰረት ሁለቱም አቋሞቿ አዲስ ከሚመሰረተው ፓርቲ የሚያስገልላት ነው። እነደ እኔ ስገምት ህወሓት እንደዚህ ግራ የገባው ሁለት አቋም ቢኖረውም መጨረሻ ላይ ከሁለቱም አቋሞቹ በተቃራኒ ከተቻለ በድርድር አዲሱን ፓርቲ ሊቀላቀል ይችላል የሚል እምነት አለኝ። ያ ካልሆነ ደግሞ ህወሓት ከሁለት የመሰንጠቅ አደጋ እንደሚያጋጥመውና አንደኛው ተሰንጣቂ ራሱን ችሎ ከአዲሱ ፓርቲ ጋር መዋሃዱ የማይቀር ነው። በዚህ መልኩ ከተፈጸመ ተደማሪውና ያልተደመረው ቡድን የሚኖራቸው ፍጥጫ ከፍ ያለ እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት ይቻላል።

ሌላው መረጃ የህወሓት ህጋዊ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጺዮን ድርጅቱን እንደማይመሩትና የድርጅቱ ህገወጥና ባለጉልበት መሪ የቀድሞው የደህንነት ኃላፊ ጌታቸው አሰፋ እንደሆነ የሚጠቁም ነው። በዛሬው እለት በመቐለ ከተማ ጌታቸው አሰፋ የህወሓት ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አለም ገ/ዋህድን እና አማካሪውን ጌታቸው ረዳን በመጥራት Bullet Proof Mercedes መኪና ውስጥ ሆኖ ኢህአዴግ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በሚያደርገው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸውና እንዴት ማሰናከል እንዳለባቸው ዝርዝር ተልዕኮ ሰጥቷቸዋል። ከሁለት ቀን በፊትም ለሌላኛው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለዓይነ ስውሩ አስመላሽ ወ/ስላሴ ተመሳሳይ ተልዕኮወችንና አቅጣጫወችን ሰጥቷል። የህወሓት ሊቀመንበርና የክልሉ ህጋዊ አስተዳዳሪ ዶ/ር ደብረጺዮን ቢሆንም እያስተዳደረና እየመራ ያለው ጌታቸው አሰፋ ነው።

በመጨረሻም በሀረርጌ ቆቦ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ከተማ ውስጥ መንገድ እንዘጋለን ያሉትን ቄሮወች በሙሉ ድራሻቸውን እንዳጠፋና እየያዘ በማሰር ላይ መሆኑን ከቦታው ሰወች አሳውቅውኛል። ሕዝቡም በፌደራል ፖሊስ እርምጃ እንደተደሰተ ለመረዳት ችያለሁ።

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ትኩስ መረጃዎች!

Post by Ejersa » 14 Nov 2019, 12:47

EthioWikiLeaks በደረሰው መረጃ መሠረት ጃዋር መሃመድ የፌስቡክ ገፁን ሙሉ ለሙሉ Yaya Beshir ለተባለ ግለሰብ አሳልፎ ሰጥቶታል። በመሆኑም ሰሞኑን በጃዋር የፌስቡክ ገፅ ላይ እየፃፈ ያለው ያዬ በሽር የተባለው ግለሰብ ነው። በሌላ በኩል ሃሰተኛ መረጃ (Fake News) በማሰራጨት የሚታወቀው ልፋእተ ተስፋይ የተባለ የህወሓት ተላላኪ የፌስቡክ ገፅ ተዘግቷል። ገፁ የተዘጋው በተደጋጋሚ ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱን አስመልክቶ ለፌስቡክ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የልፋኣተ ገፅ የተዘጋው ለምን ያህል ግዜ እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ትኩስ መረጃዎች!

Post by Ejersa » 14 Nov 2019, 14:06

በአዲሱ ውህድ ፓርቲ መቀላቀል የማይፈልግ የኢህአዴግ አባልም ሆነ አጋር ፓርቲ ይቀራል እንጂ!
በአዲሱ ውህድ ፓርቲ መቀላቀል የማይፈልግ የኢህአዴግ አባልም ሆነ አጋር ፓርቲ ይቀራል እንጂ በአብላጫ ድምጽ እንደማይወሰን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ሕወሃት ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥናቱ ሲደረግ ተቃውሞ አለማቀርቡንና ይልቁንም ጥናቱን ሲመራና ሲደግፍ መቆየቱን ገልጿል።

በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የጥናትና ምርምር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ተመስገን ቡርቃ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በሌሎች ፌዴራሊዝም ስርዓት ባላቸው እንደ ህንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ ቤልጅየም፣ ናይጀሪያ ባሉ አገሮች የሚገኙ ፓርቲዎች አገር አቀፍ ናቸው።

በግንባርነት የቆየው ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን አንድ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባት ራዕይ ለማሳካት ተቸግሮ መቆየቱን ገልጸዋል።

”በዚህም በተቀናጀ አስተሳስብ አገር ለመምራት ኢህአዴግ ሕብረ ብሔራዊ ውህድ ፓርቲ ለመሆን ወደመጨረሻው ተቃርቧል” ብለዋል።

ውህደቱ በአራት የግንባሩ እህት ድርጅቶችና በሌሎች አጋር ፓርቲዎች በድምሩ ዘጠኝ ብሄራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከታችኛው አባል ድረስ በግልጽ ተነጋግረው የሚወስኑት መሆኑን ገልጸዋል።

የትኛውም ፓርቲም ሆነ የፓርቲ አባል በውህዱ ፓርቲ ውስጥ እንደማይቀጥል ከወሰነ ይቀራል እንጂ በሌሎች ድርጅቶች አብላጫ ድምጽ እንደማይወሰን ተናግረዋል።
የውህደቱ ጉዳይ የአገር ጉዳይ ቢሆን በድምጽ ብልጫ ይወሰናል እንጂ በፓርቲ አስተሳስብ ለመደራጀት በአብላጫ እንደማይወሰን ገልጸዋል።

እስካሁንም ዘጠኙ ብሔራዊ ፓርቲዎች ወደ አገራዊ ፓርቲ ለመሸጋገር ውይይት እያደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ በጥናቱ መሰረት በሁሉም ብሔራዊ ድርጅቶች እስከ ማዕከላዊ ኮሚቴ ድረስ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቁመዋል።

በኢህዴግ አባል ፓርቲዎች ሽኩቻ በውህደቱ ሂደት ላይ ተጽዕኖ አያሳድርም ወይ ለሚለው ጥያቄም፤ ኢህአዴግ ተራማጅ ፓርቲ በመሆኑ ሁሌም ክርክርና ሽኩቻ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ሕወሃት ውህደቱን እንደሚቃወም በይፋ ሙሉ መግለጫ አለማውጣቱን ገልጸው፤ ላለፉት ሶስት ዓመታት የኢህአዴግ ውህደት ጥናት ሲደረግ ተቃውሞ አለማቅረቡን፤ ይልቁንስ ጥናቱን ሲመራና ሲደግፍ መቆየቱን ገልጸዋል።

የሕወሃት አባል በሆኑ ግለሰቦች ደረጃ ውህደቱን የሚቃወሙ ሃሳቦች ሲንጸባረቁ እንደሚስተዋል ገልጸው፤ ”ውህደቱ የራሱ ሂደት ያለው እንደሆነ በመግለጽ የመጨረሻው ሕወሃት ውሳኔ ወደፊት የሚታይ ነው” ብለዋል።

ምንጭ፡-ኢዜአ

Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ትኩስ መረጃዎች!

Post by Ejersa » 14 Nov 2019, 14:20


Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

Re: ትኩስ መረጃዎች!

Post by Ejersa » 14 Nov 2019, 18:23

ይኼ ሁሉ ትርምስና ምስቅልቅል ለምን አሁን?

Post Reply