Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣ እና በህወሃት ዘመን ከ14 በላይ የተለያዩ ስልጣኖችን ጨምድዶ ይዞ የነበረው አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ከነቤተሰቦቹ በእንግሊዝ ጥገኝነት ጠየቀ!!

Post by Maxi » 09 Nov 2019, 08:48

የህወሃት ከፍተኛ ባለስልጣ እና በህወሃት ዘመን ከ14 በላይ የተለያዩ ስልጣኖችን ጨምድዶ ይዞ የነበረው አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ ከነቤተሰቦቹ በእንግሊዝ ጥገኝነት ጠየቀ!!
Please wait, video is loading...


አቶ አስመላሽ ወልደስለሴ የተባሉትን የህወሓት/ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባልን በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በጥቅሉ 14 ስልጣኖች ጨምድዶ ይዞ ነበር። የወያኔይቱ ኢትዮጵያ አንድ ሰው በአንድ ግዜ 14 ስልጣኖችን ሰብስቦ የሚይዝባት ሀገር ነች። የአቶ አስመላሽ ወልደስለሴ 14 ስልጣኖች፡-

1) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣
2) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የመንግስት ዋና ተጠሪ.፣
3) በኢፊዴሪ መንግስት የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ፣
4) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣
5) የበጎ አድርጎት ድርጅቶች ቦርድ ሰብሳቢ፣
6) የብሮድካስት ባለስልጣን ቦርድ ሰብሳቢ፣
7) የሜቴክ ቦርድ አባል፣
8.) የዳኞች አስተዳደደር ጉባኤ ሰብሳቢ፣
9) የትግራይ አካል ጉዳተኞች ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ፣
10) የኢፈርት ድርጅቶች ቦርድ አባል፣
11) የኢትዮጵያ ፓራኦሎምፒክ ሊቀመንበር፣
12) የኢትዮጵያ ወዳጅነት ፎረም ሰብሳቢ፣
13) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቦርድ ሰብሳቢ፣ እና
14) የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ ነበር።