Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40038
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

እኔ አቢይን አልጠላውም ግን እርካቡን ስቶ ከፈረሱ እየወደቀ ነው

Post by Horus » 04 Nov 2019, 00:40

አንደኛ ፣ ባዶ ስብከት ማቆም አለበንት፤ አሁን እጅ እጅ እያለ ነው።

ሁለተኛ ፤ ያኔ የጃዋር ሽብር ሲጀመር ስብሰባውን ትቶ ወደ አገሩ ተመልሶ ስለሚሞቱት ዜጎች መናገር ነበረበት ። ይህ ግዙፍ ስህተት አንድ ነበር !

ሶስተኛ ፣ ልክ አገር ሲመለስ ብሄራዊ ሃዘን አውጆ ለሰው ህይወት ያለውን ዋጋ ማሳየት ነበረበት ። ይህ ግዙፍ ስህተት ሁለት ነበር !

አራተኛ ፣ አገር እንደ ተመለሰ ጃዋን ከመደለል ጃዋር እንዴት ሃይል እንዳለውና እሱን አላሰራ እንዳለው ለህዝቡ ገልጾ እውነት መናገር ነበረበት ። ሕዝቡ እወቱን ሁል ግዜ ያውቃልና ።

አምስተኛ፣ ከኦሮሞም ከኢትዮጵያም ፣ ከዘርም ከጎሳም ለመሆን ሲሞክር ዋሾ የመሆን ገጽታ ከመያዝ እውነተኛ ልቡን ለሕዝቡ አሳይቶ ሃቀኛ መሪነት ማሳየት ሲገባው በተበላ እቁብ የህዝቡን የመገመት ችሎታ በመናቅ እጅግ ግዙፍ ሰህተት ሰራ !

ስድስተኛ ። ከዚያም ራሱ እየወጣ ችግሩንም ድክመቱንም ችሎታውንም፣ ኣማወንም ለህዝቡ ፊት ለፊት እንደ ማቅረብ ዙሪያ ጥምጥም ሲዞር በራሱ ላይ ሌላ ችግር ፈጠረ !

አሁንም አጉል ብልጣብልጥነትን ወዲያ ብሎ ሕዝብ ሁሉ የሚያውቀን ውጥንቅጥ የኦሮሞ ዘር ፖለቲካ ከገበያ አውጥቶ የእውነት መሪ መሆኑን ማሳየት ግድ ይለዋል !!

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: እኔ አቢይን አልጠላውም ግን እርካቡን ስቶ ከፈረሱ እየወደቀ ነው

Post by TGAA » 04 Nov 2019, 01:11

የአብይ ትልቅ ስህተት ወይም ድክመት ንግግሩና ተግባሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየተላያየ መሄዱ ነው፡፡ ከአንድ አመት ንግግር በኋላ የራሱ ፓርቲ እንኳን የማይከተለው እርሱ የሾማቸው እርሱን እየተቃረኑ ሲናገሩ ምንም ከበሬታ እንደማይሰጡት በግልጽ እየታየ ነው ፡ መሪ ማለት ሰብካ አይደለም ፡ ምንም አይነት ወርቅ የሆኑ ንግግሮች ቢያደርግም ተግባራዊ ማድረግ ካልቻለ ለስነጽሁፍ ምሳሌነት ካልሆነ ፓለቲካውንና ሀገርን በተመለከተ ባዶ አየር እየሆነ ነው ፡፡ አሁን ይህንን ለመመለስ መጀመርያ ማድረግ ያለበት የሚናገረው ነገር በእውነት የሚያምንበትን ነው ? ካላመነበት ስልጣኑን የሚናገረውን ተግባር ማድረግ ይችላል ብሎ ለሚያስበው
ስልጣኑን ይስጥ ፡፡

Horus
Senior Member+
Posts: 40038
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: እኔ አቢይን አልጠላውም ግን እርካቡን ስቶ ከፈረሱ እየወደቀ ነው

Post by Horus » 04 Nov 2019, 03:33

TGAA
ያለከው ሁሉ ትክክል ነው ፤ ግን ስልጣን ይልቀቅ ሳይሆን ስልጣን ከሌሎች ጋር ይጋራ ነው መልሱ ። አቢይ መውደቅ ካልፈለገ የመንግስት ስልጣን ከሁሉም ፓርቲዎችና ጎሳዎች ጋር በችሎታ መሰረት ማሰራጨት ግድ ይለዋል። ባዶ ስብከቱ አሁን ባዶ ነው፣ በቃ !!!

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: እኔ አቢይን አልጠላውም ግን እርካቡን ስቶ ከፈረሱ እየወደቀ ነው

Post by Za-Ilmaknun » 04 Nov 2019, 11:31

After a good fresh start when taking the helm a year and half ago, PM Abiy seemed to be destined to unify and pacify the country tormented by TPLF looting gangs for close to 30 years. Those who thought he was the answer to their prayers elevated him to the status of sainthood. They took him as a savior and the man to lead them to the Promised Land. A year and half later, things do seem not as rosy as once thought.

His reluctance to decisively deliver a blowing punch to the bleeding TPLF nose at the outset coupled with his invitations of unsavory ethnic opportunists to the country is now setting the stage for a bloody confrontation. His unwittingly appointing die-hard ethnic cadres to the detrimental positions in the federal structure and, sidelining those who served as stepping stone for his ascent is now compounding the problems that he has to deal with. His anger and agitation against the “Balderas” movement and his haste in declaring as a coup what transpired in Bahirdar, further fuels the perception of him as having antipathy to the genuine Ethiopianist blocks.

While he is practically doing everything possible to transfer power to the hands of his ethnic party, his base unfortunately is embroiled with what he has to say as the leader of the country. They are vying to hear hateful and condescending speech targeting the Amara people for the base’s ephemeral pleasure like Meles Zenawi habitually used to do.

https://www.zehabesha.com/the-pm-abiy-a ... conundrum/

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: እኔ አቢይን አልጠላውም ግን እርካቡን ስቶ ከፈረሱ እየወደቀ ነው

Post by Ethoash » 04 Nov 2019, 12:39

አንተ በክት ጉራጌ

አስር ጉራጌ በሞት እና አንደ አማራ ቢሞት በአንድ ቀን ለማነ ነው ለቅሶ የምንቀመጠው ለአማራው ውይስ ለጉራጌው ፤

ድንቄም ነጥብ በነጥብ አስቀምጠሻል ። እንቺም ብሎ መካሪ ልፍስፍስ ዘረኛ ። መጀመሪያ ከሊስቲሮነት ሚንታሊቲ (አስተሳስብ ) ወጣ ። መላውን ጎራጌ የምታሳፈር ነህ። ታውቀዋለህ ምን ብለህ አትጠይቀኝ።

ፕለቲካ ሱቅበደሬቴ መስለህ ውይ። ፖለቲካ ዋጋ ማጭበርበር መስለህ ውይ፤ ፖለቲካ አየር በአየር መስለህ ውይ።


Maxi
Member+
Posts: 5951
Joined: 06 Mar 2014, 04:33

Re: እኔ አቢይን አልጠላውም ግን እርካቡን ስቶ ከፈረሱ እየወደቀ ነው

Post by Maxi » 04 Nov 2019, 22:09

አብይ አሀመድ ከሞተበት አንስቶ ያመጣው ኦነግ ራሱን አብይ አሀመድን ሊገለብጠው ነው!!! ቅቅቅቅቅ

Post Reply