Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
wazzupdog
Member
Posts: 1915
Joined: 16 Jun 2018, 22:10

BREAKING NEWS: Terrorist Ja-war's Qeero has attacked displaced residents of Dire Dawa who were sheltered in a school

Post by wazzupdog » 30 Oct 2019, 00:56

...................Residents of Dire Dawa who were displaced by terrorist Ja-war's qeerroo, and were sheltered in a school were attacked by the same qeerroo after federal security forces that were keeping peace in the area left their post unannounced. It is not clear who gave the order for the military to vacate the area. It is possible the order might have come from General Birhanu Jela or Defense Minister Lemma Megersa................

Ethio 360 Media
36 mins ·
በድሬደዋ ተፈናቃዮች የተጠለላችሁበትን ለቃችሁ ውጡ በሚል ቄሮ የሚባለው ቡድን ድብደባ ተፈጸመባቸው።-የኢትዮ 360 ምንጮች

(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 19/2012)በድሬደዋ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚል ቄሮ የሚባለው ቡድን ድብደባ እንደፈጸመባቸው ተሰማ።

ለኢትዮ 360 የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው 200 የሚጠጉት ተፈናቃዮች አካባቢውን ልቀቁ በሚል ድብደባ የተፈጸመባቸው ትላንት ከምሽቱ 4 ሰአት ጀምሮ ነው።

በተለምዶ ዝንጀሮ ገደል በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩት ተፈናቃዮች አካባቢያቸውን እንዲለቁና በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ለመጠለል የተገደዱት በዚሁ የጥፋት ሃይል መሆኑን ይናገራሉ።

ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ከተደረጉም በኋላ በአካባቢው በሚገኘው ሳቢያን አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው መቆየታቸውን የኢትዮ 360 የመረጃ ምንጮች ይገልጻሉ።-ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ማቋረጡን በመናገርም ጭምር።

እንደ ምንጮቹ ከሆነ ተፈናቃዮቹ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከተጠለሉ በኋላ አካባቢውን ይቆጣጠር የነበረው የመከላከያ ሃይል ነው።

ዛሬ የመከላከያ ሃይሉ ምንም አይነት ተለዋጭ የጸጥታ አስከባሪ ባልተመደበበት ሁኔታ አካባቢውን እንዲለቅ መደረጉ ታውቋል።

ይህን ተከትሎም ማማሻውን ቄሮ የተባለው የጥፋት ሃይል በተፈናቃዮቹ ላይ ድብደባና አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ወከባ ሲፈጽም አምሽቷል እንደ ምንጮቹ ገለጻ።

በተፈናቃዮቹ ላይ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊትም የድረሱልን ጥሪውን የሰማው የአካባቢው ወጣትና ነዋሪ በአካባቢው ደርሶ የጥፋት ሃይሎቹን ማባረር ችሏል ይላል መረጃው።

የጸጥታ ሃይሉ በአካባቢው ቢደርስም ድጋፍ የሚያደርገው ለወንጀለኛው ቡድን እንጂ ለንጹሃን ዜጎች አይደለም ሲሉም ይናገራሉ።

የመከላከያ ሃይሉ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ትዕዛዝ መተላለፉን እንጂ በማን ትዕዛዝ አካባቢውን ለቆ እንደወጣ እንደተደረገ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም።

የከተማ አስተዳደሩንም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከተውን አካል ለማግኘት ኢትዮ 360 ጥረቱን ሲያደርግ ቢቆይም ለዛሬ ሊሳካ አልቻለም።

wazzupdog
Member
Posts: 1915
Joined: 16 Jun 2018, 22:10

Re: BREAKING NEWS: Terrorist Ja-war's Qeero has attacked displaced residents of Dire Dawa who were sheltered in a school

Post by wazzupdog » 30 Oct 2019, 01:16

..........Ethiopians hurry up and organize. The 7th King is unwilling to protect citizens from terrorist Ja-War's marauding qeerroos.........

Post Reply