Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

የሙታን ፖለቲካ ያጣመራቸው የዕልቂት መልዕክተኞች!

Post by Hameddibewoyane » 28 Oct 2019, 17:59

በእርግጥ የአብዮቱ ፖለቲካ የሚቀጥል ከሆነ በጥቂት አመታት ውስጥ #ኢትዮጵያ ትፈርሳለች። ስለዚህ አዲሱ ትውልድ እንኳን የሚመራው መንግስት የሚኖርበት ሀገር አይኖረውም። ኢትዮጵያ ከፈረሰች ደግሞ አሁን በውስጧ ያሉት ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች የየራሳቸውን ሀገር መስርተው በጉርብትና የሚኖሩ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ከዚያ ይልቅ ሀገሪቱ ከፈረሰች ምስራቅ አፍሪካን የሚያጥለቀልቅ የደም ጎርፍ ይፈስሳል፣ ተቆጥሮ የማያልቅ ሬሳ በየስርቻው ይከመራል። ኢትዮጵያ ወደ ምድራዊ ሲዖል ትቀየራለች። ስለዚህ አዲሱ ትውልድ የትላንቱን ያረጀ የፖለቲካ አመለካከትና ዛሬ ላይ የሚስተዋለውን ጭፍን ብሔርተኝነት ማስወገድ አለበት።

በዚህ መሰረት የወደፊቱን አስከፊ እልቂትና ውድቀት ለማስቀረት አዲሱ ትውልድ አበክሮ ማሰብ፣ መስራትና መተባበር ይጠበቅበታል። ለዚህ ደግሞ ከፊት ለፊቱ ቆመው የዕልቂት ነጋሪት እየጎሰሙ ያሉትን የፖለቲካ ቡድኖች በግልጽ መጋፈጥ አለበት። እነዚህ የሙታን ፖለቲካ ያጣመራቸው የዕልቂት መልዕክተኞች ህወሓት እና ጃዋር (ኦነግ) ናቸው። ለአዲሱ ትውልድ የሁለቱ ጥምረት ትክክለኝነት እና አግባብነት ፍፁም ሊያሳስበው አይገባም። ምክንያቱም የህወሓቶች ዓላማና ግብ ምን እንደሆነ ባለፉት 27 አመታት በተግባር የታየ ነገር ነው። ህወሓቶች በ1997ቱ ምርጫ ደንግጠው ልክ እንደ አሁኑ ወደ መቀሌ ሸሽተው ከተመለሱ በኋላ በአስር አመት ውስጥ በህዝብ ላይ ያደረሱትን ስቃይ እና በሀገር ላይ የፈፀሙትን ዘረፋ ሁላችንም እናውቃለን።

አሁን ደግሞ ተመልሰው ከመጡ በምድር ላይ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ አሰቃቂ ነገር ሊፈፅሙ እንደሚችሉ ጥርጥር የለኝም። በሌላ በኩል እነ ጃዋር መሃመድ የሚያራግቡት አክራሪ ብሔርተኝነት እነ ሌንጮ ለታ እና ሌንጮ ባቲ እድሜ ልካቸውን ሞክረው እውን ሊሆን እንደማይችል በተግባር ያረጋገጡት ነገር ነው። ህወሓት እና ጃዋር/ኦነግ ጥምረት የፈጠሩበት ምክንያት፤ አንደኛ፡- ሁለቱም ስር የሰደደ የስልጣን ጥማት እና የቁሳዊ ኃብት ፍላጎት ስላላቸው፣ ሁለተኛ፡- ሁለቱም የሙታን ፖለቲካ የሚያራምዱ የአብዮቱ ትውልድ ርዘራዦች በመሆናቸው ነው። በአጠቃላይ የህወሓት እና ጃዋር/ኦነግ ቅንጅት ላለፉት አርባ አመታት የመጣንበትን በጥላቻነ ቂም የታጨቀ፣ በግጭትና ጦርነት፣ እንዲሁም በጅምላ ፍረጃና ግድያ የሚታመስ፣ ያን ያረጀና ያፈጀ የሙታን ፖለቲካ ለማስቀጠል ያለመ ነው። በዚህ ምክንያት ገፈት ቀማሽ የሚሆነው ደግሞ አዲሱ ትውልድ ነው! የሙታን ፖለቲካ ያጣመራቸው የዕልቂት መልዕክተኞች የሁላችንም ስጋት ናቸው!
****
ሙሉ ፅሁፉን ለማንበብ :arrow:
https://ethiothinkthank.com/2019/10/28/ ... bTSvA1fM2w