Subscribe to Mereja Youtube Channel: https://bit.ly/2WbsDeL
Re: የናዝሬት ወጣቶች የጃዋርን የአመጽ ጥሪ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃወሙ
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ጃዋር የደረገውን የድረሱልኝ ጥሪ ተከተሎ የመጣውን ጥፋት ማስረሻ ሰጤ በአማራ ክልል አድርጎት ቢሆን ኖሮ ምን ይሆን ነበር?
መጀመሪያ ከአዴፓ ስራ አስፈፃሚዎች የተወሰኑት ወደ አማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያቀኑና ማስረሻ ምን አይነት ጠባጫሪ ሰው እንደሆነ፣እንዴት የአማራን ህዝብ እንዳዋረደ ያወሳሉ፡፡ጊዜ ካላቸው ነገም ተመልሰው መጥተው ትናንት የረሱትን ወይ ደሞ ትናንት ያልመጡ ጓዶቻቸውን ጨምረው ተጨማሪ ውግዝ ያሰማሉ
ይህን ተከትሎ አበረ አዳሙ ወንጀለኛውን ከነግበረ- አበሮቻቸው እያሳደደ እንደሆነ፣በቅርብ ቀንም በእጁ እንደሚያስገባው ፈርጠም ብሎ ይናገራል፡፡ሰፋ ያለ መግለጫ ለመስጠት ነገ እንደሚመለስ ቀጠሮ ያስይዛል፡፡ ሲመለስ ወንጀለኛው ከጤና ጋር የተያያዘ ችግርም እንዳለበት ይጠቁማል!
በነጋታው የዘጠኙም ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣የሃገሪቱ ሚኒስትሮች፣የሃይማኖት መሪዎች፣የሃገሪቱ ሁሉም ከተሞች አንዳንድ ነዋሪዎች ግለሰቡ ያደረገው ነገር ህገወጥ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ፍርድ መቅረብ እንዳለበት ያወሳሉ፡፡ይህ አይነቱ አካሄድ ጊዜው ያለፈበት እንደሆነና መቅረት ያለበት ነገር እንደሆነም አጥብቀው ይናገራሉ፡፡ሕወሃት ድርጊቱን የሚያወግዝ፣አዴፓን የሚያጥረገርግ ደብዳቤ ትፅፋለች፡፡ኸርማን ኮህንም ወደ ትዊተር አቅንተው ድርጊቱን ከአማራ ታሪካዊ ትምክህት ጋር እያሰናሰሉ ያወግዛሉ፡፡
ከዛ ቀን በኋላ የማስረሻ ዱካ ይጠፋል! መከላከያ ሰራዊት በአቅራቢያው ከሚገኘው ዕዝ ማስረሻ ወደ ከተመበት የገጠር ከተማ ይተማል፡፡ወሬው ማስረሻ ቆሰለ ወይስ ሞተ የሚል ይሆናል፡፡የማስረሻን ስም መጥራት ከበጥባጭ በመወገን ያስወግዛል፡፡
ከዛ ወዲህ ማስረሻ የሚባል ሰው የበላው ጅብ አይጮህም፡፡ተው ባክህ የሚሉ ሽማግሌዎችም ወደቤቱ አይሄዱም፡፡ከዘነጠ ቪላው ወጥቶ መግለጫ አይሰጥም፡፡በፌስ ቡክ ገፁ ብቅ ብሎ መንገድ ክፈቱ፣የቆሰሉትን እርዱ፣ከተጣላችሁት ሁሉ ጋርም ከዛሬ ጀምሮ ታረቁ ሲል የሰላም አባት ሊሆን እርግብ ይዞ አይመጣም፡፡ካለመምጣቱ የተነሳ እንዳልተወለደ ተቆጥሮ ይረሳል።እንዲህ ነው ተዛነፋችን፤ከዚህ በላይ አያዛንፈን፤አሜን!
መስከረም አበራ