Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ተገኘተውው በሰጡት ማብራሪያ ምርጫን በተመለከተ የተናገሩት!!!!

Post by Hameddibewoyane » 22 Oct 2019, 06:05

‹• የውጭ አገር ዜጋ የሆናችሁ የሚዲያ ባለቤቶች የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላችሁ የሚዲያ ባለቤቶች ስትፈልጉና ሰላም ሲሆን እዚህ ተጫውታችሁ እኛ ችግር ውስጥ ስንገባ ጥላችሁ የምትሄዱበት ሁለት አገር ያላችሁ ሰዎች ትግስት እያደረግን ያለነው አውዱን ለማስፋት ነው።

• በማንኛውም ሰዓት በኢትዮጵያ ሰላምና ህልውና ላይ ከመጣ አማረኛ ብትናገሩም ኦሮምኛም ብተናገሩም እርምጃ መውሰዳችን የማይቀር መሆኑን በጥንቃቄ መገንዘብ አስፈላጊ ይሆናል።

• ሁለት ቤት መጫወት አይቻልም። እኛ የምንሄድበት አገር የለንም። አገራችን ይሄ ስለሆነ ሰላም እንፈልጋለን።

• ተቀያሪ ያላችሁ ሰዎች በነጻነት ሰላማችን፣ ልማታችንነ ዴሞክራሲያችንን ካገዛችሁ እሰዬው በደስታ! ከዚያ ውጭ ግን ለመነገጃ የምትጠቀሙበት ከሆነ በዚህ ሁኔታ በነጻነትና በዴሞክራሲ ስም የሚቀለድ እንዳልሆነ ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል።››

• ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም፤

• ኢህአዴግ አንድ ቢሆንም ባይሆንም ኢትዮጵያ ትቀጥላለች፤

• ምርጫውን አሁን አንችልም በሚቀጥለው እናድርግ ካልንነ ብዙ ችግር አለው፤ ማድረጉ በብዙ መንገድ ይጠቅመናል፤

• ምርጫውን ለማድረግ በቂ ዝግጅት አለ። ለምርጫ ቦርድ የተመደበው ሀብት (በጀት) ባለፉት አምስት ምርጫዎች ከተመደበው የበለጠ ነው፤

• የምርጫ ቦርድ አደረጃጀት በንጽጽር ከምንጊዜውም የተሻለ ነጻ ነው፤

• ኢትዮጵያ ውስጥ አሸንፎ መምራት ብቻ ሳይሆን ተሸንፎ በሰለማዊ መንገድ መስጠትም ትልቅ ታሪክ ነው፤

• የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫን ተከትሎ የሚፈጠሩ ግጭቶች ምን እንደሚያስከትሉ ከምርጫ 97 ተረድቷል፤ ስለዚህ ምርጫን ተከትሎ የሚነሳን ግጭት አይፈልግም፤ ቢፈጠረም እንዴት እንደሚያልፈው ያውቃል፤

• የፖለቲካ ፓርቲዎች አሸንፈው መንግስት በመሆን ብቻ የሚያምኑ ከሆነ የፖለቲካን ሙሉ ቅርጽ አያሳይም፤ መሸናፍንም መለማመድ ያስፈልጋል፤

• በቤተሰብ፣ በጓደኛ በማህበር የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት አያዋጣም፤ ሰብሰብ ማለት ነው የሚበጀው፤ ለኢህአዴግ ጭምር፤

• መንግስትና ፓርቲን ፓርቲና ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ማየት ተገቢ አይደለም፤››