ኦሕዴድ በሕወሓት ላይ ዛሬ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሰነዘረው ቢጡ ግን እንዲመዘገብ ይሁን! ይህ በሕወሓት ላይ የተሰነዘረው ቡጢ መመዝገብ ያለበት የኦሕዴድ መኳንንት እየዘረጉት ያለውን የአፓርትያድ ሥርዓት ሕዝቡ ወደ ቀልቡ ተመልሶ አፍንጫው ማሽተት ሲጀምርና ከትናንቱ የሚገማውን የአፓርታይድ አገዛዝ መቃወም ሲጀምር ባለጊዜዎቹ በሕወሓት የተለመደ ዘይቤ የሚነሳባቸውን ተቃውሞ ማፈናቸው ስለማይቀር ያኔ እንድናስታውሳቸው ነው።
እነሆ ኦሕዴድ በሕወሓት ላይ የሰነዘረው ቡጢ፤
«ሕወሓት ኢትዮጵያዊ ማንነት የተገመደበትን ገመድ፣ የታሰረበትን ካስማ በመንቀል ሳይገታየተጋመደበትን ገመድ በፈጠራ ትርክት ለመበጣጠስ ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቧጠጠው አቀበት የለም። የትግራይን ሕዝብ ከቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመነጠል በፈጠራ ታሪክ፣ በአልባኒያ ሶሻሊዝምና በነሌሊንና ስታሊዝ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፤ በማኪያቬሊያዊ የሥልጣን ቀመር ቀለም በመበጥበጥ ተርኳል። ላለፉት 27 ዓመታት ሀገሪቱ በነበረው ፍጹም አምባገነናዊ፣ ሙሰኛና ሴረኛ አገዛዝ ላይ ሕዝብ በአመጽ በተነሳ ቁጥር በትግራይ ሕዝብ ላይ የተነሳ ለማስመሰል በሒትለር የፕሮፓጋንዳ አስገድዶ የማጥመቅ ኅልዮት ለብቻው በተቆጣጠራቸው ሜዲያዎች ሲለፍፍ ኖሯል።»
[ምንጭ፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፥ አጀንዳ አምድ፥ ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም.]
-
MINILIK SALSAWI
- Senior Member
- Posts: 11059
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact: