፩ኛ፥ ነጉሰ ነገስታት ዮሃንስ
የኢትዮጵያን ኣረንጓዴ፣ ብጫ፣ እና ቀይ ቀለማት ሰንደቅ ኣላማ መጠቀምን ያስፋፉት እሳቸዉ ናቸዉ ይባላል። ይህ እዉነት ይሁን ሃሰት ኣላዉቅም። እዉነት ከሆነ እሳቸዉ ያስፋፉት ሰንደቅ ኣላማ ሌላዉን ኣከባቢ በሰፊዉ ስያሸበርቅ (ለምሳሌ በቅርቡ ባህርዳር የነበረዉን ያስታውሱ) እሳቸዉ ተወልደዉ፣ ኣድገዉ፣ ነግሰዉ የኖሩበት ኣከባቢ በሌሎች ቀለማት (ቀይ እና ብጫ) ስያሸበርቅ ይታያል። ለመሆኑ የትግርኛ ሙዚቃ ቃና ቋንቋዉን የማይችሉትን ጨምሮ ሲስብ ለምንደነዉ እነዚህ ቀለማት የሚጥመዉ ሙዚቃ ቃና ዉስጥ የሚታዩት ልብሶች ላይ የማይስቡት?
፪ኛ፥ ነጉሰ ነገስታት ምንይልክ/ምኒልክ
ኣህጉር ኣቋርጦ የመጣን ጠላት ገጥመዉ ከኣሸነፉ በኧላ (ሙሉ በሙሉ ባይሆንም) ጨቋኝ ከመባል ኣልፈዉ ኣህጉር ኣቋርጦ እንደመጣ ቀኝ ገዢ ተብለዉ ነበር።
፫ኛ፥ ነጉሰ ነገስታት ሃይለሰላሴ
በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ ብሩህ ተማሪዎች የተባሉትን ለመጀመርያ ጊዜ ያፈራ ከፍተኛ ትምህርት ለፍተዉ ኣስፋፍተዉ እነዚሁ ብሩህ ተማሪዎች በቀሰቀሱት ወይም በተሳተፉበት ኣብዮት ግርግር ምክንያት የነጉሰ ነገስታቱም ህይወት ተቀሰፈ፣ ከነዚሁ ብሩህ ተማሪዎች ወስጥ ብዙሃን የኣብዮቱ መስዋዕት ሆኑ።
ይህ ታሪክ እዉነት ከሆነ ወይም እዉነትነት ካላዉ እንቆቅልሾች ኣይመስሉም?