Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

መንገድ ከምንዘጋ ውሃ በከንቱ እንዳይፈስ እንገድብ! ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ!!!!

Post by Hameddibewoyane » 17 Oct 2019, 11:47

ለዘመናት ደምና ኣጥንት ሲከሰከስበት የነበረው የኤርትራ ምድር እነሆ በቢልዮኖች ኩዪቢክ ሜትር የሚገመት ውሃ ተከምሮበታል። የባርካ፣ የከረን፣ የጋሕቴላይ፣ የሳሕል፣ የደቡብና የደንከል በረሃማ ምድር እንዲህ ለዓይን በሚማርክ መልኩ የውሃ ማቆርያ ሆኗል። ኤርትራ ከምትገኝበት ጂኦግራፊያዊ ኣቀማመጥ ኣንጻር በዓለም ላይ ጥቂት ዝናብ ከሚያገኙ ሃገራት ኣንዷ ናት። ሳያቋርጥ ዓመቱን ሙሉ የሚፈስ ጅረት ኤርትራ ምድር ላይ የለም። ይሁን እንጂ ክረምቱን ብቻ ጠብቆ በሚዘንበው ጥቂት ዝናብ ልማትን ማካሄድ እንደማይቻል የተገነዘበው የኤርትራ መንግስት ግድቦችን መስራት የቅድሚያ ስራው ኣድርጎት ቆይቷል። ዛሬ 85% ከኤርትራ ህዝብ የንጹህ ዉሃ ተጠቃሚ ሆኗል።

በጣልያን ግዜ ወደ ኤርትራ የገባው ዘመናዊ የኣትክልትና የፍራፍሬ ልማት በሩቅ የገጠር መንደሮችም ባህል እየሆነ ነው። ይህ ሁሉ የሆነውና እየሆነ ያለው የወጣቱን ትኩስ ሃይል በመጠቀም ነው። የወጣቱን እምቅ ሃይል ለጥፋት ሳይሆን ለልማት ካዋሉት ተኣምር ሊሰራ እንደሚችል ኣንዱ ማሳያ ነው። ወጣቱን ሜንጫና ዱላ ሳይሆን ኣካፋና ዶማ ካስያዙት ተራራውን ይንዳል፣ ሁዳዱን ወደ ገነት ይቀይራል። ወጣቱን መንገድ መዝጋት ሳይሆን ውሃን መዝጋት ካስተማሩት የተፈጥሮን መልክ መቀየር ይችላል። ወጣቱን ሰላሳ የቢራ ፋብሪካ ከፍቶ በየድራፍት ቤቱ ከማጎር፣ በየጫት ቤቱ ከማደንዘዝ ትራክተር መንዳት ቢያለማምዱት የራሱንና የመጪውን ትውልድ ህይወት መቀየር ይችላል።

ልማትና ብልጽግና በትላልቅ የእዩልኝ የቦንድ ፕሮጀክቶች ሳይሆን ሰፊውን ህዝብ ተደራሽ ባደረገ መልኩ ሲካሄድ ጥቅሙ ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በዘለለ የእያንዳንዱን ዜጋ ህይወት ይቀይራል። እነዚህ በጥቂቱ ምስላቸውን የለጠፍኩዋቸው የውሃ ግድቦች ካለምንም የውጭ እርዳታ በሃገር ውስጥ ኣቅም ብቻ ወጣቱን በማደራጀት የተሰሩ ናቸው። እነዚህ የውሃ ግድቦች ከቤት ውስጥ ፍጆታ በተጨማሪ ዘመናዊ የእርሻ ልማት በማካሄዱ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ውሃ የህይወት መሰረት ነው።

ውሃ ሲኖር ነው የልማት ፕሮጀክቶችን መተለምና ማሳካት የሚቻለው። በረሃማ የኣየር ንብረትን መቀየር የሚቻለውም ውሃን በመያዝ ነው። የብዝሃ ህይወትንም መጠበቅ የሚቻለውም ተፈጥሮን በመንከባከብ ነው። መኖርያ ቤትና ኢንዱስትሪ መስራት የሚቻለው የማያቋርጥ የውሃ ኣቅርቦትን በማረጋገጥ ነው። ለዚህም ነው የኤርትራ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው። እና ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መንገድ ከምትዘጉ ልማት ላይ በመሳተፍ በከንቱ የሚፈስ ወንዞች ገድቡ!!!!!!





Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: መንገድ ከምንዘጋ ውሃ በከንቱ እንዳይፈስ እንገድብ! ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ!!!!

Post by Za-Ilmaknun » 17 Oct 2019, 12:51

"ወጣቱን ሜንጫና ዱላ ሳይሆን ኣካፋና ዶማ ካስያዙት ተራራውን ይንዳል፣ ሁዳዱን ወደ ገነት ይቀይራል። ወጣቱን መንገድ መዝጋት ሳይሆን ውሃን መዝጋት ካስተማሩት የተፈጥሮን መልክ መቀየር ይችላል። ወጣቱን ሰላሳ የቢራ ፋብሪካ ከፍቶ በየድራፍት ቤቱ ከማጎር፣ በየጫት ቤቱ ከማደንዘዝ ትራክተር መንዳት ቢያለማምዱት የራሱንና የመጪውን ትውልድ ህይወት መቀየር ይችላል።ወጣቱን መንገድ መዝጋት ሳይሆን ውሃን መዝጋት ካስተማሩት የተፈጥሮን መልክ መቀየር ይችላል። ወጣቱን ሰላሳ የቢራ ፋብሪካ ከፍቶ በየድራፍት ቤቱ ከማጎር፣ በየጫት ቤቱ ከማደንዘዝ ትራክተር መንዳት ቢያለማምዱት የራሱንና የመጪውን ትውልድ ህይወት መቀየር ይችላል።" Very true !

This is what civilized countries do. TPLF/OLF led Ethiopia has only been good at fostering division and inciting hate among citizens. The forces of fantasy and greed are the central component of the parties. Unless these dark forces are dealt with decisively, Ethiopians can't contemplate about development and change.

Post Reply