Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Hameddibewoyane
Member
Posts: 3890
Joined: 25 Sep 2019, 02:42

ሰበር ዜና: ህወሓት ኢትዮጵያን የማተራመስ ስራውን ቀጥሎበታል!

Post by Hameddibewoyane » 16 Oct 2019, 10:01

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 5/2012 በራያ ሕወሓት ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሯል። ጥይት፣ የወታደር ዩኒፎርም፣ ቃሬዛ እና አካፋ ለታጣቂዎች እያከፋፈለ ነው። የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ደጀኔ አሰፋ የሕወሓትን የጦርነት ዝግጅት የፌደራል መንግሥት እና አዴፓ ሊያውቁት ይገባል ሲል መረጃውን ይፋ አድርጉዋል። ሰሞኑን ለአንድ ሳምንት ስብሰባ ላይ የቆየው ሕወሓት ትላንት ባወጣው መግለጫ የኢህአዴግን ውህደት ተቃውሞ፣ ሕዝቡ ለመራራ ትግል ይዘጋጅ ሲል ጥሪ ማድረጉ አይዘነጋም።