Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 11059
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አቶ ሽመልሽ አብዲሳ፤ በንግግርህ ላስቀየምከው ህዝብ ትልቅ ይቅርታ በይፋ ወጥተህ መጠየቅ ይኖርብሀል፡፡ (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

Post by MINILIK SALSAWI » 06 Oct 2019, 11:25

ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ሽመልሽ አብዲሳ፤ (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

የተወሰንን ግለሰቦች ኦሮአማራ እያልን ስንጮህ ሕውሃት እና የኦነግ አጋሮች ሲሰድቡን ከረሙ፡፡ የእነርሱ መንጫጫት እንብዛም አሳስቦን አያውቅም ነበረ፡፡

አሁን ደግሞ በሚያስደነግጥ እና በሚያሳፍር ትችት እና ዲስኮርስ የአማራን እና የኦሮሞን ግንኙነት ለማክሰም ሞከርክ፡፡ ሆኖም ግን ለብዙ ዘመናት በአብሮነት የኖሩት ህዝቦች፤ በፓርቲና በግለሰቦች ፈቃድ ቀድሞውንም ያልተመሰረተ በመሆኑ ሊፈርስ አይችልም፡፡

እንደዚህ አይነት ሕውሃታዊ፤ኦነጋዊ እና አክራራዊ ገለፃ አንተ ይዘህ በመቅረብህ እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ስትሾም “እንኳን ደስ ያለህ” ብለው መልዕክት የላኩልህ የፍልስፍና አሰተማሪዎችህም በእጅጉ አዝነውብሃል፡፡

አማራ ተባለ ነፍጠኛ በታሪኩ ለማንም ተንበርክኮ አያውቅም፤ ይህንን እውነታ እንኳንስ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ያለ ሕዝብ ይቅርና፤ ቱርኮችም፣ ግብፃችም፣እንዲሁም ጣሊያኖችም ጠንቅቀው ያውቀሉ፡፡

ልጅ ሽመልስ እንደአስተማሪህ ያለኝ ምክር፡- በንግግርህ ላስቀየምከው ህዝብ ትልቅ ይቅርታ በይፋ ወጥተህ መጠየቅ ይኖርብሀል፡፡ በተጨማሪም ራስህን ሁን፣ ለሙገሳ እና የግለሰቦችን ቅቡልነት ለማግኘት ስትል ሌላውን ሰው ለመሆን አትሞክር፤ በተቻለህም መጠን የአክራራዊነት መንፈስ ከራስህ ላይ አርቅ፤ መጠቀሚያም አትሁን፡፡

በመጨረሻም፤
ስለሽመልስ አብዲሳ በሰጠሁት አስተያየት አሳስተህናል ለምትሉ ወገኖቼ ትልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ለነገሩ የተከሉት ዛፍ ቀጥ ብሎ ይወጣል ሲሉ ከፍ ሲል ሊጎብጥ ይችላል እና እንዲሉ፡፡

Abere
Senior Member
Posts: 14781
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: አቶ ሽመልሽ አብዲሳ፤ በንግግርህ ላስቀየምከው ህዝብ ትልቅ ይቅርታ በይፋ ወጥተህ መጠየቅ ይኖርብሀል፡፡ (ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

Post by Abere » 06 Oct 2019, 11:37

የዐማራ ህዝብ ምንም ዓይነት ይቅርታ ከኦነግ አይቀበልም። በፍፁም ይቅርታ አይፈልግም አይቀበልም። ዶር ዳኛቸው ከዐብይ ጋር ሆድህ አልቆርጥ ካለ ዝም በለህ አርፈህ ተቀመጥ። ስንት ጊዜ ነው እነኝህ ሊህቃን ምና ምን እያሉ አማራን እንዴ ኳስ መጫዎች ለማንም ተራ ወንበዴ የሚዳርጉ። ወይ እፈሩ ወይ እረፉ። ለአማራ መፍትሄው እራሱ አማራ ብቻ ነው። የወንበዴ ይቅርታ አይሰረይም።

Post Reply