Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: የእለቱ ትኩስ ዜና ሲተነተን [VIDEO]

Post by Revelations » 01 Oct 2019, 13:01

የቅማንት ስምን እንደሽፋን በመጠቀም ከፀረ አማራ ኃይሎች ጋር በመተባበር ከሱዳን ተነስተው በወዲ ከውሊ ስናር በኩል ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ለመግባት ሙከራ ያደረጉ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ከስፍራው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ስዓት አካባቢ ታጣቂዎች ከሱዳን ተነስተው በወዲ ከውሊ ስናር አድርገው ወደ ምዕራብ አርማጭሆ ኮርሁመር አካባቢ ለመግባት ያደረጉት ሙከራ መክሸፉ ተገልጧል።

የጠላት ተልዕኮ አንግበው የጓንግን ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ አርማጭሆ በወዲ ከውሊ ስናር በኩል ሲገቡ የነበሩ 7 የሚሆኑ በቅማንት ስም የሚንቀሳቀሰው የሽብር ቡድን ታጣቂዎች ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በሚኒሻ፣ ልዩ ሀይሉ እና በአካባቢው ገበሬዎች ቅንጅት በቁጥጥር ስር ያዋሉ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከተያዙት ታጣቂዎች መካከልም ተልዕኮው ምን፣ለምንና ከማን እንደተሰጠ የሚያመላክት መረጃ መገኘቱንም ምንጫችን ገልፀዋል።

ከፊሎቹ ደግሞ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የጓንግን ወንዝ ባለመሻገራቸው አጋሮቻቸው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሲረዱ ተመልሰው ወደ ሱዳን መግባታቸውን በስፍራው የነበረና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የፀጥታ አካል መረጃውን አድርሶናል።

በተመሳሳይ በኮርሁመር ከተማ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ የአካባቢው ህዝብና የፀጥታ መዋቅሩ አንድ ተጠርጣሪን ይዞ ባደረገው ምርመራ ከቅማንት ኮሚቴ የጥፋት ተልዕኮ የተሰጣቸው ሌላ 19 ግብረ አበሮች እንዳሉ መጠቆሙን ተከትሎ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መድረጉንም ሌላኛው ምንጫችን ገልፀዋል።

የተሰጣቸው ተልዕኮም የሰሊጥ አጨዳ ስራውን ማደናቀፍ፣ የአካባቢውን ሰላም ማናጋትና ማህበራዊ እረፍት መንሳት መሆኑን ፈቅደው በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል ሲሉም አክለዋል።

ስለሁኔታው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለኮርሁመር ቀበሌ አስተዳዳሪ ለአቶ ጌታው ብንደውልም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛቸው ጓንዲ በበኩላቸው ዛሬ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም በኮርሁመር ከተማ አንድ ተጠርጣሪ መያዙን አምነው ከሱዳን በወዲ ከውሊ ስናር በኩል 7 ታጣቂዎች ተይዘዋል የተባለውን ግን መረጃ እንዳልደረሳቸው በመግለፅ አስተባብለዋል።

በተጨማሪም ለምዕራብ ጎንደር ዞን የአስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ለአቶ ደሳለኝ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ለጊዜው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።





Post Reply