Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

ሆስፒታል የገቡ የ85 አመት ሽማግሌ ከሆስፒታል አውጥቶ ደብድቦ ከመግደል ...የሲዳማ ጥያቄ የሲዳማ ወጣቶች በስተመጨረሻው የታክቲክ ስህተት ..as stated by Jawar

Post by Za-Ilmaknun » 09 Sep 2019, 15:16

"ጃ-war በሲዳማ ጎረምሶች መሃል ቆሞ እንደ ሙሶሎኒ በሚመስለኝ የዘወትር መወናጭፉ እየተወናጨፈ “በጉልበትም ቢሆን አላማችሁን አሳኩ” ያላቸው ወጣቶች ሰምተውት ጉልበታቸው የሚችለውን ሁሉ ካደረጉ በኋላ በባለፈው ሳምንት የL-TV ቆይታው “የሲዳማ ወጣቶች በስተመጨረሻው የታክቲክ ስህተት ሰርተዋል” ሲል ሊወቅሳቸው ቃጥቶታል፡፡

ሰው ተዘቅዝቆ ሲሰቀልለት እንኳን ቅጭም የማይለው ጃዋር ታዲያ በዚህ ሁሉ ውድመት ውስጥ ያለውን የእሱን ሚና ለመደበቅ “የሲዳማ ጥያቄ የእኔ አያት አንቀልባ ላይ እያሉም የነበረ ነው እንጅ እኔ የፈጠርኩት አይደለም” ሲል ያምታታል; የታክቲክ ስህተት የሚለው ቤተክርስቲያን ማቃጠሉን፣እሱ “ነዋሪዎች” ሲል እንደ ባሪያ የሚቆጥራቸውን ሲዳማ ያልሆኑ የሰው ልጆች ነፍስ እና ንብረት ማውደማቸውን ወዘተ ነው፡፡ለመሆኑ ያኔ በጉልበት አላማችሁን አስፈፅሙ እያለ ስሜቱ እንዳቀበለው ሲደነፋ የነበረው ወጣቶቹ ከዚህ ሌላ ምን እንዲያደርጉ አስቦ ነበር?

የጃ-war ኢትዮጵያ..... እትብታቸው ከተቀበረበት መንደር ራቅ ብለው የሚኖሩ “ነዋሪዎች” የተባሉ ባሮች በህይወታቸው ላይ ተፅዕኖ በሚያደርግ ፖለቲካዊ ነገር ላይ መወሰን አይችሉም:: የሚወስኑላቸው ብሄር ብሄርሰቦች እና ህዝቦች የተባሉ ልዑላን ናቸው፡፡ ነዋሪዎች እንደ ግሪክ ዲሞክራሲ ባሮች እንደ ከብት እየበሉ እየጠጡ፣እየተኙ፣እየተነሱ ልዑላን ብሄር ብሄረሰቦች በወሰኑበት የፖለቲካ መንገድ መጓዝ ብቻ ነው፡፡የጃ-war ኢትዮጵያ ይህችን ትመስላለች!

ቃለ-መሃላ ያልፈፀመው ጠ/ሚ ጃ-war ይህንን ሲል አንድ እንዲመልስልኝ የሚፈልገው አበይት ጥያቄ አለ:: ይኽውም እስከ ዛሬ ስንት ሃገራዊ ምርጫ ሲደረግ ነዋሪዎች በሃገራዊ ምርጫ ድምፅ እንዳይሰጡ ያላሳሰበው ለምንድን ነው? እሱ አዛዥ ናዛዥ ከሆነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረገው በሚቀጥለው ሃገራዊ ምርጫስ እኛ ነዋሪዎች መምረጥ እንችል ይሆን አይሆን የሚለውን በጊዜ ቢያሳውቀን ደግ ነው፡፡በህገ-መንግስቱ መምረጥ የሚችሉት ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ናቸው ከተባለ እኛ ነዋሪዎች እስከ ዛሬ ስንመርጥ የነበረው እሱን ምን አፍዝ አደንግዝ ይዞት ነው? ነዋሪዎች በሪፈረንደም እንዳይሳተፉ የሚለውን የዛሬውን የጃ-war ፅሁፍ ሳነብ ከጃ-war ኢትዮጵያ ይልቅ ነዋሪዎች እንዳይመረጡ ግን እንዲመርጡ መብት የሰጠቸው የመለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ የተሻለች መሆኗን ተገንዝቤያለሁ፡፡"

https://www.satenaw.com/amharic/archives/70508

simbe11
Member
Posts: 2088
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: ሆስፒታል የገቡ የ85 አመት ሽማግሌ ከሆስፒታል አውጥቶ ደብድቦ ከመግደል ...የሲዳማ ጥያቄ የሲዳማ ወጣቶች በስተመጨረሻው የታክቲክ ስህተት ..as stated by Jawar

Post by simbe11 » 09 Sep 2019, 15:33

ቃለ-መሃላ ያልፈፀመው ጠ/ሚ ጃ-war

In Ethiopia their were a few that raised their hands before parliament but none were elected.
ነዋሪዎች በሪፈረንደም እንዳይሳተፉ የሚለውን የዛሬውን የጃ-war ፅሁፍ ሳነብ ከጃ-war ኢትዮጵያ ይልቅ ነዋሪዎች እንዳይመረጡ ግን እንዲመርጡ መብት የሰጠቸው የመለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ የተሻለች መሆኗን ተገንዝቤያለሁ
I highly doubt about the current revolution and the direction it's heading to. But I would love to give this revolution a chance and would rather lose everything than having the TPLF back, especially Meles.

Post Reply