Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

፡የህወሃት አመራሮች ማንነት እኩይነት ብቻ አይደለም-የሚፈልጉትን ጠንቅቆ የማወቅ ብቃታቸውን ባንወዳቸውም ልንቀበለው የሚገባ ሃቅ ነው፡

Post by Za-Ilmaknun » 09 Sep 2019, 14:15

"አማራው ራሱ የተቆፈረትን ጉድጓድ እሰከማያጤን ድረስ ብአዴን በሚባል ፓርቲ ስር ተደራጅቶ ራሱ የሚታረድበትን ቢለዋ ሲስል፣ የሚቀበርበትን ጉርጓድ አርቆ ሲቆፍር የኖረው አስማት በሆነው የህወሃት አደናጋሪ፣ ተለዋዋጭ እና መሰሪ የፖለቲካ ስትራቴጅ ሳቢያ ነው፡፡ ህወሃት በ1968 የፃፈውን ማኒፌስቶ እያነበበ አዲስ አበባ እንደማይደርስ አሳምሮ የሚያውቅ ክሱት ፓርቲ ነው፡፡ ይህን ማኒፌስቶ መሳቢያ ውስጥ አስቀምጦ አማራውን በተመለከተ አቋሙን እየቀያየረ አዲስ አበባ ገባ ማለት ግን በ1968ቱ ማኒፌስቶ ላይ ያስቀመጠው ስለ አማራ ህዝብ ያለው ትክክለኛ አመለካከት ተቀይሯል ማለት አይደለም፡፡ የተቀየረው ክፉ ስራውን የማስፈፀሚያ በጎ ስትራቴጅዎች ማውጣት ብስለት ላይ የደረሰው የአቶ መለስ ጭንቅላት ነው፡፡

መሰረታዊ ክፋቱ የማይቀየረው የአቶ መለስ ጭንቅላት ጠላቱን ወዳጅ አስመስሎ መያዝንም ያውቅበት ነበርና የሚጠላቸው አማሮች ታላቁ መሪ እያሉ አቤት ወዴት ሲሉለት እንዲኖሩ የሚያደርግ ጥራዝ እየፃፈ ይግታቸው ነበር፡፡ ይህ የአቶ መለስ ብልጫ ቢሆንም ከመላው ህወሃት መሰሪነት የሚቀዳ ነገርም አይጠፋውም፡፡ ሌሎቹ የህወሃት መሪዎች እንደ አቶ መለስ ያለ የቆርጦ ቀጥልነት ብቻ ሳይሆን የማንበብ ብልፅግና ባይኖራቸውም ጠላትን ወዳጅ አስመስሎ ማሻሸቱ ላይ ከአቶ መለስ እምብዛም የማይርቅ እኩይነት አያጡም፡፡የህወሃት አመራሮች ማንነት ግን እኩይነት ብቻ አይደለም-የሚፈልጉትን ጠንቅቆ የማወቅ ብቃታቸውን ባንወዳቸውም ልንቀበለው የሚገባ ሃቅ ነው፡፡ ህወሃቶች የሚፈልጉትን ያውቃሉ፤ ለዛም ሳያቋርጡ ጠንክረው ይሰራሉ፡፡ ሰፋ አድርገን እንየው ከተባለ ደግሞ እንደ አንድ ሰው የሚሰራ፣ በጥቅሻ የሚግባባ ካድሬ እና ደጋፊ በክልላቸው መስርተዋል፡፡ ካድሬዎችቻቸውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው የፓርቲ አመራሮቻቸው የሚያመጡት የስትራቴጅ ለውጥ በድሮ በሬ ለማረስ ካለመቻሉ የተነሳ ለጋራ ግብ ሲሉ ያደረጉት እንደሆነ ለመረዳት እንጨት አይጨርሱም፡፡ ይህ የደጋፊዎቻቸው ነገር የመረዳት ብቃት የህወሃት አመራሮች በስልጣን ሳሉ መንገዳቸውን ቀና አድርጎላቸው ኖሯል፤ አሁን ከስልጣን ከወረዱም አቃፊ ደጋፊ መጠለያ ሆኗቸዋል፡፡

የኦሮሞ ብሄርተኞችን ግን ከወቅታዊ የፖለቲካ ተለዋዋጮች ጋር የሚሰናሰሉ ትርጉም ሰጭ ስትራቴጅዎችን ነድፎ ወደ ስኬት መንገድ በመጓዙ ብልሃተኝነት ረገድ እንደ ባልንጀሮቻቸው እንደ ህወሃቶች ክሱቶች አይደሉም፡፡ አላማን ጠንቅቆ በማወቅ ረገድም የሚቀራቸው ብዙ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ፖለቲካቸው ህወሃት ያየውን ስኬት ማየት አልቻለም፡፡ አላማችን የሚሉት ህወሃትም አላማው እንደሆነ የሚታወቀው የአማራን ሁለመና መፍራት እና ማሳደድ ነው፡፡ ልዩነቱ ህወሃት አማራን የመጥላቱን ስሜት ስልጣን ላይ እንዳይሰነብት ደንቃራ እንዳይፈጥርበት በተቻለ መጠን አምቆት ጥላቻውንም ስልጣኑንም ሳያጣ ረዥም ዘመን መንበር ላይ መቆየት ችሏል፡፡ ህወሃት ይህን የሚያደርገው ከላይ በተጠቀሱት የአማራ ጥላቻ ተረኮቹን ተጠቅሞ አማራውን ራሱን እየሸነሸነ በሚያደናግርበት ስትራቴጅው ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ህወሃቶች ከኦሮሞ ብሄርተኞች የሚለዩት ስልጣን ላይ መሆናቸው ረባሽ እንዳይሆኑ የሚከለክል ትልቅ ክብር እንደሆነ ማወቃቸው ነው፡፡