
በሁለቱ ሃገራት የተደረገው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህይወትን ከመቅጠፍ በተጨማሪ የሁለቱን እህትማማችና/ወንድማማች ህዝብም እንዳይገናኙና ተቆራርጠው እንዲቀሩ ምክንያት ሆኗል።
ከአንድ አመት በፊት የሁለቱ ሃገራት መንግሥታት ሰላም እናወርዳለን ማለታቸውን ተከትሎም ተቆራርጠው የነበሩ ቤተሰቦች ስሜታቸውን መግለፅ ከብዷቸው፤ እግራቸው ክዷቸው መሬት ላይ ሲንበረከኩ፤ ቃላት አጥሯቸው ሲያነቡ የነበሩና ሌላም ብዙ የብዙዎችን ስሜት የነኩ ሁኔታዎች ታይተዋል።
ከቤተሰቦች መገናኘት በተጨማሪ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የነበረውም ንግድም እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል።
ይሁን እንጂ እንጂ ሁለቱን ሃገራት በመንገድ የሚያገናኙት ዛላምበሳ ሰርሓ፣ ራማ ዓዲ ዃላ እንዲሁም ሑመራ ኦምሓጀር መስመሮች “ሕጋዊ አሰራር ሊበጅለት ነው” በሚል ምክንያት ደርቶ የነበረው የንግድ ግንኙነት እንዲቋረጥ ሆኗል።
ሕጋዊ አሰራር ሊበጅለት ነው በሚል ምክንያት የተቋረጠው ግንኙነትም እስካሁን ተግባራዊ ባይሆንም የሁለቱም ሃገራት ህዝቦች ግንኙነታቸው እንደቀጠለ ነው።
ኤርትራውያን በመቐለ ከተማ
ተዘግተው የነበሩ ድንበሮች መከፈታቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ጎርፈዋል።
ከትግራይ ነዳጅ ጨምሮ ዳቦ፣ እንጀራና ሌሎች የሸቀጥ አይነቶች ሲጓጓዙም እንደነበር ብዙዎች ይናገራሉ።
በተለይም በዛላምበሳ በኩል ወደ ዓዲግራት ብሎም ወደ መቐለ ከተማ የገቡት ኤርትራውያን ቁጥራቸውን በትክክለ መንገር ባይቻልም በሺዎች እንደሚገመቱ ይነገራል።
ወደ ትግራይ የመጡት ኤርትራውያን መቐለን ማእከል አድርገው በቋሚነት እየኖሩ ሲሆን በተለያዩ የስራ ዘርፎችም እንደተሰማሩ ቢቢሲ ለመገንዘብ ችሏል።
ከነዚህ ውስጥ አርሴማ ሰመረ አንዷ ነች። ከኤርትራ መጥታ በከተማዋ እምብርት ሮማናት አደባባይ አካባቢ በፀጉር ስራ ተሰማርታለች።
ከሃገር ወጥቶ ኑሮን መመስረት ቀላል ባይሆንም ለአርሴማ ብዙ አልከበዳትም።
ኤርትራውያን በመቀሌ
“መቐለ ለስራ ምቹ የሆነች ከተማ ነች፤ እንደ ሃገሬው ዜጎች ነው የምንስተናገደው እና በተጨማሪ የምጠየቀው ነገር የለንም” በማለት ትገልፀዋለች።
አስመራ በነበረችበት ወቅት በዋነኝነት በአንድ የባህል ቡድን በድምፃዊነት እና በተወዛዋዥነት ትሰራ ነበር።
መቐለም ከመጣች በኋላ ከፀጉር ስራው በተጨማሪ አልፎ አልፎ በምሽት ክበቦች እና ጭፈራ ቤቶች በተወዛዋዥነት ትሰራለች።
በቅርቡም አንድ ነጠላ ዜማ ሰርታ ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነች ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ገልፃለች።
የሁለቱን ሃገራት እርቀ ሰላም ተከትሎ መቐለ የከተመው ሌላኛው ኪዳነ ገብረ ሚካኤል ነው።
በተለምዶ 16 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢከም በፀጉር ስራ ተቀጥሮ በመስራት ይገኛል።
“እዚህ ስንሰራ በመንግስት ይሁን ቀጣሪ ድርጅቶች የምጠየቀው ወረቀት ስለሌለ ምንም የምንቸገረው የለም” ይላል።
የኑሮ ሁኔታ
በትግራይ ክልል የተለየ የሕግ አሰራር ባይወጣም እንደ ሃገር ኤርትራውያን ከሌሎች ሃገራት ስደተኞች በተለየ ሁኔታ ሰርተው የሚለወጡበት እና ሀብት የሚያፈሩበት የሚደነግገው አዋጅ ተሻሽሎ ቀርቧል።
የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ባለፈው አመት በትግራይ ስታድየም ባሰሙት ንግግር ኤርትራውያን ወደ ክልሉ መጥተው እንዲሰሩና ሃብት እንዲያፈሩ እንዲሁም በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
ምንም እንኳን ኤርትራውያን በነፃነት መንቀሳቀስ ቢፈቀድላቸውም ከስደተኞች መጠለያ ውጭ ከተማ ውስጥ ለሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኛ መሆናቸውን የሚገልፅ ወረቀት ይዞ መንቀሳቀስ ግዴታ እንደሆነ ኪዳነ ይናገራል።
ከዚህም በተጨማሪ በአንዳንድ የስራ ዘርፎችም ለማሳተፍ እንዳማይችሉም ይገልፃል።
“የራሳችን ድርጅት እንድንከፍት አልተፈቀደልንም። በቅርቡ ይፈቀዳል የሚል መረጃ ስላለ ይፈቀድልናል ብለን በተስፋ እየጠበቅን ነው” ይላል።
ምንም እንኳን ሁሉ አልጋ ባልጋ ባይሆንም የሁለቱ ሃገራት ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ መመሳሰል ከሃገር ርቆ ሁለተኛ ሃገር የሆነላቸው አልታጡም፤ ከነዚህም መካከል ሰላም ብርሃነ አንዷ ናት።
በአሁኑ ወቅት በአንድ መፅሃፍት ቤት ተቀጥራ ብትሰራም መጀመሪያ ስትመጣ የመቆየት ሃሳብ አልነበራትም።
ተመሳሳይ ቋንቋ መናገራችው፣ የህዝቡ አኗኗር ዘዬ በአጠቃላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ትስስር በመረዳቷ መቀሌ ለመቆየት እንደወሰነች ትናገራለች።
“መቀሌን ስለወደድኳት እዚሁ ቀረሁኝ፤ የትግራይና የኤርትራ ህዝቦች ግንኙነትም ከፍተኛ ትስስር እንዳለው ተረድቻለሁ”ትላለች።
በመጀመሪያ ወደ መቀሌ ስትመጣ ለከተማዋም ሆነ ለህዝቡ ምንም አይነት ግምት ባይኖራትም በአሁኑ ወቅት ግን እንደ ሃገሬው ህዝብ ስለተቀበላትም ደስታዋ ከፍ ያለ ነው።
ለረጅም ዓመታት ሰላምም ሆነ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ከመኖራቸው አንፃር ህዝቡ እንዲህ በቀላሉ ይወዳጃል ብላ እንዳልጠበቀችም ሰላም ትናገረለች
“የትግራይ ህዝብ ሰው አክባሪ እና ለኤርትራውያን ትልቅ ክብር ያለው ህዝብ ሆኖ ይሰማኛል” በማለት ትዝብትዋን አካፍላናለች።
በመቀሌም ብዙ ጓደኞችን አፍርታ ተስፋዋን ሰንቃ ሃገሬ ብላ እየኖረች ነው።
ምንም እንኳን ስደተኛ መሆናቸውን የሚመሰክር ወረቀት ይዘው መንቀሳስ ቢችሉም የባንክ ሂሳብ ደብተር ለማውጣት የሚፈቅዱላቸው አንዳንዶች መሆናቸውን ይገልፃሉ።
ኪዳነ በበኩሉ ምንም እንኳን ስደተኛ ቢሆነም ስደተኛነቱን ይህንን ያህል እንደማያስተውሰው ገልጿል።
“ኤርትራዊ ሆነህ እዚሁ ሀገር ለመስራት ብዙ አስቸጋሪ አይደለም፤ ራስህን ከህብረተሰቡ ተለይተህ እንደ ስደተኛ አታስብም፤ ስደተኛ መሆኔን ትዝ ብሎኝ አያውቅም” ይላል።
በግንኙነቱ እስካሁን ከተሰራው ይበልጥ ከተሰራበት ተስፋ ሰጪ ዕድሎች እንደሚታየውም ኪዳነ ይገልጻል።
“ለስራም ብዙ አልቸገርም፤ እንደ ዜጋው ነው የምትኖረው። ስደተኛ በመሆንህ የሚፈጠር ልዩነት የለም፤የወረቀት ማስረጃ እና ዋስ አቅርበህ ስራ መቀጠር እንችላለን” በማለት አብራርታለች።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠባቂ በደብረዘይት ባልታወቀ ምክንያት ተገድሎ ተገኘ ተባለከስደት ከተመለሰ በኋላ ቻይና በመሄድ ተጨማሪ ስልጠና ወስዶ የጠቅላይ ሚንስትር ታማኝ ጠባቂ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደነበረ ነው እስከ አሁን ባላወቅኩት ምክንያት ተገድሎ ተገኘ ነው የተባለው። አዲሱ አለሙ ይባላል በትላንትናው እለት ባልታወቀ ምክንያት በደብረዘይት ተገድሎ መገኘቱን ስሰማ ልቤ እጅግ አዘነ። ከአዲሱ…Mereja
ሁለት ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ።በሙስኝነት ግንባር ቀደም የሆኑትና ከፍተኛ ዘረፋ ሲፈጽሙ የነበሩት ሁለት ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰማ። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ እና የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ለጠቅላይ…Mereja
አሳፋሪው የዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር በሚሊኒየም አዳራሽ ያደርጉት መላው ኢትዮጵያውያንን ያስከፋ መሆኑን ተነገረአሳፋሪው የዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር በሚሊኒየም አዳራሽ ያደርጉት መላው ኢትዮጵያውያንን ያስከፋ መሆኑን ተነገረMereja
ኦነግ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ስርዓት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ያዳምጡ ኦነግ ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ስርዓት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ያዳምጡMereja
አፋጣኝ መፍትሔና መሠረታዊ ለውጥ የሚሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች እና የመንገደኞች አቤቱታአፋጣኝ መፍትሔና መሠረታዊ ለውጥ የሚሻው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰራተኞች እና የመንገደኞች አቤቱታ (ምንልክ ሳልሳዊ ) በብልሹ አሰራር የበሰበሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት ሀያ አመታት በሰራተኞቹ እና በመንገደኞች ላይ መንግስታዊ ወንጀል ሲፈፅም የኖረ ተቋም ነው ። በአቶ ተወልደ የሚመራው የተቋሙ ማኔ…Mereja
. 
