Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 34438
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

[PHOTO] "በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ! " ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለመስጊድ አፍራሹ ታከለ ኡማ

Post by Revelations » 09 Aug 2019, 14:29

ጋዜጠኛ እና የድምፃችን ይሰማ አባል የነበረው ሳዲቅ አህመድ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ እየተደጋገመ የመጣውን የመስኪድ መፍረስ አስመልክቶ «በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ» በሚል አሳሳቢነቱን ገልፆል።

ጋዜጠኛ ሳዲቅ ይቀጥልና ማህበረሰቡ ግዜያዊ ማስታገሻዎችን፣ የግዜያዊ ችግሮችን መፍትሔ ለማግኘት ይጣር እንጂ የሚፈጸምበትን አስተዳደራዊ በደል ለማስቀረት በመደራጀት ላይ አይደለም። ለጉዳዩ ተጠያቂ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆኖ ሳለ በምጽዋት የሚሰጥ ፖለቲካዊ ጥቅም ያለ እስኪመስል ድረስ «ለውጡን ለማደናቀፍ የተሰገሰጉ አካላት» ብሎ ምክንያት መስጠቱ ፖለቲካዊ-ሚስኪንነት ነው።ምላሹ መሆን ያለበት ተነስ፣ ተደራጅ፣ እራስህን ለምርጫ ኮሮጆ አዘጋጅ ነው ይላል።

በዘመነ ታከለ ኡማ አዲስ አበባ ውስጥ አራት መስጊዶች ፈረሱ፤ ይህ ደግሞ ታከለ ኡማ በጊዜያዊነት በከንቲባነት ተቀምጦ ሳለ ነው። ታከለ ኡማ እስከ ምርጫ ደርሶ ምርጫን ቢያሸንፍና ህጋዊ እውቅናን አግኝቶ ለአመታት ከንቲባ ሆኖ ቢቀጥልስ? ይህ ታስቦበታልን?

በዚህ ተንኳሽ (provocative) ሙከራ ምን ለመስራት ታስቧል? ሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል እርቀሰላም ሰፍነ፣ ለአያሌ አመታት መጅሊስን አስመልክቶ ሲጠየቅ የነበረው ጥያቄ ፈር ያዘ ሲባል ማህበረሰብን ለጸብ የሚጋብዝ ተግባር መፍጸሙ በአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት ላይ የተቃጣ ስንኩል ተግባር አይደለምን ሲልም ይጠይቃል።

ግዜው የአመት በዓል ነ፤ ኢድ ከቀናት በኋላ ይውላል። አዲሱ የመጅሊስ አመራርና ሌሎች ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ለሐጅ ወደ መካ አቅንተዋልዩ ብዙ ሰዎች ኢድን ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ለማክበር ወደ ገጠር አቅንተዋል።

መስጊድን ከኢድ በፊት ማፍረስ አጋጣሚ ነው ወይስ ለውጥ መጣልኝ ብሎ ተስፋ የሰነቀው ሙስሊም ማህበረሰብ በቁጭትና በምሬት እንዲብሰለሰል የማድረግ ሴራ ? በማለት የታከለ ኡማ ኬላ የለሽ (free pass) ውሳኔ ይቀጥላል ሲል ተችቷል።

ከንቲባው የጠቅላይ ሚንስትሩ ፖለቲካዊ ምሶሶም ስለሆነ እምብዛም ላይሰጋ ይችላል። ከንቲባውን በአንክሮ ለተመለከተ ደግሞ ረጅም ፖለቲካዊ ምኞች ያለው ይመስላል። ከምእራብ አገራት በተኮረጁ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎቹ ለወደፊቱ አገር ለመምራት የምርጫ ዘመቻ ላይ ያለ ወጣት ፖለቲከኛ ይመስላል። ‹የልብን አድርሶ ይቅርታ› እንደሚባለው ሰሞኑን የፎቶ ግርግር ( photo op) ፈጥሮ፣ ከምእምናን ጋር ተቃቅፎ ነገሩን ለማበራረድ ቢሞክር አይገርምም ብሏል።

ጋዜጠኛ ሳዲቅ ይቀጥላል፤ ጥያቄው ይህንን ለቀጣዩ የከንቲባነት ምርጫ ዘመቻ በተግባር «በገድሎ ማዳን» ትርክት የሚንቀሳቀሰውን ከንቲባ እንዴት አድርጎ በድምጽ መቅጣት ይቻላል? የሚለው ሊታሰብበት ይገባል ያለው ጋዜጠኛው አዲስ አበባ የፖለቲካ ካፒታል ናት ብሏል።

የአገሪቷ ፖለቲካ አዲስ አበባ ወደነጎደችበት ይነጉዳል በሚል ስጋት እነ መለስ ዜናዊ በ1997ቱ ምርጫ የፈጸሙት ወንጀል አይዘነጋም፤ ሌሎችም የፖለቲካ ሐይላት ባለ በሌለ ሐይላቸው አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ሲረባረቡ ይስተዋላል ሲል ጽሁፉን ይቀጥልና ተቃዋሚዎቹ ስላቅ በሚመስል መልኩ ገና በ«ማ» እየተጨቃጨቁ ነው፤ ስለዚህ በቀጣዩ ምርጫ 23ቱ ወረዳዎች የማን ይሆናሉ? የእምነት ተቋም ፈረሰብኝ እሮሮው ወደ ምርጫ ኮሮጆ ሲያቀና ብቻ ነው የተሻለ መልስ የሚገኘው ብሏል።

መማረሩ፣ ለውጡን ሊያደናቅፉ የሚሹ ሐይላት አፈረሱብን እያሉ ምክንያት መስጠቱ ያብቃ፤ ግርማ-ሞገስ ያለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ይጀመር፤ ያኔ ምድረ-አስመሳይ ፖለቲከኛ ጠብ-እርግፍ ሲል ይታያል፤ ልብ ያለው ልብ ይበል በማለት ፁሁፋን ያጠናቅቃል።






Revelations
Senior Member+
Posts: 34438
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [PHOTO] "በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ! " ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለመስጊድ አፍራሹ ታከለ ኡማ

Post by Revelations » 09 Aug 2019, 14:47



የከተማውን አስተዳደር ከሕዝበ ሙስሊሙ ጋር ለማጣላት እና በጋራ ኮሚቴው የተሰራውን ሥራ ለማጠልሸት የሚሞክሩ፣ የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም መልካም ስም ለማጉደፍ የሚኳትኑ እንዳሉ ልንገነዘብ ይገባል።

የእኩይ ተግባር ሥራ አንዱ መስጅድ በማፍስ እና የተጀመረውን መግባባት ለመናድ መሞከር ቢሆንም ግን እንደማይቻል ሊታወቅ ይገባል።

ነገ ጠዋት የመጀመሪያ ሥራችን የተሻለ ቦታ በመስጠት ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ያለንን የማይነቃነቅ ድጋፋችንን እናሳያለን።

ለማንኛውም ለተፈጠረው ስህተት እና ዕኩይ ድርጊት በራሴ እና በከተማችን አስተዳደር ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ።

በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉት እና ድርጊቱን ያስፈፀሙት በሕግ እንዲጠየቁ እና ተልዕኮአቸውን ለማጣራት ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏል።

ኢ/ር ታከለ ኡማ

Revelations
Senior Member+
Posts: 34438
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [PHOTO] "በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ! " ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለመስጊድ አፍራሹ ታከለ ኡማ

Post by Revelations » 09 Aug 2019, 15:05

የታከለ ኡማ አስተዳደር መስጂድ ማፍረሱን ቀጥሏል!

Ustaz Ahmedin Jebel

ታከለ ዑማ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ ቢያንስ የምናውቃቸው 4 መስጊዶች የማፍረስ ሂደት በአስተዳደሩ አማካኝነት ተፈፅሟል። በወረዳም ይሁን በክፍለ ከተማ የተቀመጡ አመራሮች በራሳቸው እንዲህ አደረጉ ብሎ ማሰብ አይቻልም። የአዲስ አበባ አስተዳደር በዝምታ ሲታለፍ እኛንም ሊያለማምደን ያሰበ ይመስላል። ታከለ ዑማም ሆነ ከርሱ ጋር ያሉ የከተማው አስተዳደር አመራሮችን ከዚህ በላይ በዝምታ ማለፍ አይቻልም። ጊዜ እየጠበቁ መስጊድ እያፈረሱ ሙስሊሙን የሚዳፈሩና የሚያስቆጡት ላይ ታከለ ዑማ በይፋ እርምጃ ካልወሰደና ራሱ ታከለ ዑማ ቆሞ የፈረሱትን ቢያንስ 4 መስጊዶችን ካላሰራ እንዲሁም ይህን መሰል መስጂድ የማፍረስ ሂደትን በማያዳግም ሁኔታ ካልገታ፣ ታከለ ራሱ ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር ለመጣላት መርጧል ከማለት ዉጭ ሌላ የምለው የለኝም። በአዲስ አበባ አስተዳደር አማካኝነት በዚህ አንድ ዓመት ዉስጥ ከፈረሱት መስጂዶች እና ህዝበ ሙስሊሙን ካስቆጡት መካከል እነኚህን እናስታውሳለን።

1) ሒጅራ መስጂድ... ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01

2) አሊፍ መስጂድ .ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01

3) ዑመር መስጂድ...ቦሌ አራብሳ ወረዳ 15

4)የ አብዱልቃድር መስጂድ ማስፋፊያ..በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ

ታከለ ህዝቡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል የተገባውን የዓመታት ጥያቄ የሆነውን የኢድ መስገጃና የታላቅ መስጂድ መስሪያ ቦታ ተሰጥቶ ግንባታ ከዛሬ ነገ ይጀመራል ብሎ በጉጉት እየጠበቀ ባለበት ባንተ ተሹሞ የተቀመጡ ሰዎች በተደጋጋሚ መስጊድ እያፈረሱ የእምነት ተቋማትን እየተዳፈሩ ህዝቡን ሲያስቆጡ የነርሱ አለቃ የሆንከውን ያንተን ምላሽ ህዝበ ሙስሊሙ የሚጠብቅበት ጊዜ ላይ ነው። ታከለ ዑማ ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር መጣላት ካልፈለግክ በስተቀር እንደተለመደው "አዝነናል። እናጣራለን።" ብለህ ለማለፍ አትሞክር። ይቅርታ ጠይቅ። እርምጃ ዉሰድ።ራስህ ቆመህ አሰራ። ይኸው ነው።



Masud
Member+
Posts: 8502
Joined: 18 Jun 2013, 09:06

Re: [PHOTO] "በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ! " ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለመስጊድ አፍራሹ ታከለ ኡማ

Post by Masud » 09 Aug 2019, 15:12

Everyone must obey the rules and regulations. No one one is above the law. This applies for everyone--Muslim, Christian, Waqeffata, etc. If illegal land grab and illegal building of church is crime for Christian, illegal land grab and illegal building of mosque is also crime. There shouldn't be double standard. Every one must be treated equally. Sadiq must not expect special treatment and bribe. Such crime is haram for Muslims.

Revelations
Senior Member+
Posts: 34438
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [PHOTO] "በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ! " ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለመስጊድ አፍራሹ ታከለ ኡማ

Post by Revelations » 09 Aug 2019, 17:45

ወይ ጣጣችን! ደግሞ ብለን ብለን እናንተን ተናባችሁ እንድት ሰሩ እንርዳ?! ታኬ ጎማው ማርሽ ቀይሮ በሌላ ጎዳና ተጉዞ "ነገ በጠዋት ያፈረስነውን መስጅድ መልሰን እንሰራለን:: እኔም በቦታው ተገኝቼ ማገር አቀብላለሁ" ብሏል እኮ ማሱድ ከርፋፋው! ቅቅቅቅ!
Masud wrote:
09 Aug 2019, 15:12
Everyone must obey the rules and regulations. No one one is above the law. This applies for everyone--Muslim, Christian, Waqeffata, etc. If illegal land grab and illegal building of church is crime for Christian, illegal land grab and illegal building of mosque is also crime. There shouldn't be double standard. Every one must be treated equally. Sadiq must not expect special treatment and bribe. Such crime is haram for Muslims.

Revelations
Senior Member+
Posts: 34438
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: [PHOTO] "በምርጫ ኮሮጆ እንገናኝ! " ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ለመስጊድ አፍራሹ ታከለ ኡማ

Post by Revelations » 09 Aug 2019, 18:44


Post Reply