ውሃው አለ ወንዙ ግን የለም- አማርኛ አለ አማራ የሚባል ግን የለም (የዴናቁርት ኦነግ እና ትህነግ ወያኔ ተጠየቅ/ ሎጅክ)
ለእራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ይሉሃል ይኸ ነው። ኦሮምኛ የሚባል ቋንቋ አለ ግን ኦሮሞ የሚባል ህዝብ የለም ወይን ትግርኛ አለ ግን ትግሬ የሚባል ህዝብ የለም ቢባል ምን ዓይነት ቅቡልነት ይኖረዋል? ግመል ሰርቆ አጎንብሶ መሄድ አይሆንም እንዴ 50 ሚልዮን በላይ ያለውን አማራ ህዝብ የት ውስጥ ሊያገቡት ነው ወይስ በወረቀት ላይ ለመጨረስ ነው?