Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ ..... ከ አፋብን ፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

Post by MINILIK SALSAWI » 15 Aug 2026, 23:29

"በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል"

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ !

ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም

ዘረ ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል ስም በኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂደው የድራማ መድረክ የህዝብ ውክልና የሌለበት፣ ተጨማሪ ቀውስ የሚያዋልድ እና የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም የተነደፈ የአረመኔው አገዛዝ የፖለቲካ አሻጥር መሆኑን ከዚህ በፊት ባወጣነው መግለጫ አቋም መውሰዳችን ይታወቃል።

ሆኖም ግን አገዛዙና አጋሮቹ ይህንን ከጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ ያቀረብንላቸውን ጥሪ በመተው ''በምክክር'' ስም የከተሞችንና አካባቢዎቻቸውን የታሪክ፣ የዴሞግራፊ፣ መልክአምድራዊና የይዞታ ቅርፃቸውን ለማዛባትና በተለይም ነባር የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችንና የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጥፋት መንገድ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል።

አዲስ አበባ ከተማ እንደገና ከመቆርቆሯና ከአሁኑ መጠሪያዋ ቀደም ብሎ ''በራራ'' በመባል የምትታወቅ፣ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በጦርነት ሳቢያ እስከወደመችበት ጊዜ ድረስ የአማራ ነገስታት መቀመጫና የአማራ ህዝብ ጥንተ-ርስት እንደሆነች የታሪክ መዛግብትና አርኪዮሎጂያዊ ማስረጃዎች በግልፅ ያረጋግጣሉ።

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ብጡል አዲስ አበባ ከተማን በድጋሚ ሲቆረቁሯት፣ ባዶ መሬት ላይ ሳይሆን የአባቶቻቸውን ታሪካዊ ይዞታ፣ ርስትና ውርስ መነሻ በማድረግ ነው። ይህ ታሪካዊ እውነት ሊሸረሸርም ሆነ ማንም አምባገነናዊ አገዛዝ በጊዜያዊ ስልጣን ህዝብ ባላመነበት ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰርዘው የማይችለው ፅኑ የታሪካችን አንድ አካል ነው።

ከተማዋ የአማራ ጥንተ-ርስት መሆኗ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሂደት የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ መኖሪያ፣ የባህልና የኢኮኖሚ ማዕከል፣ እንዲሁም የአንድነት ተምሳሌት ሆና ተገንብታለች። ከዚህ አኳያ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ፣ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መናገሻና የዓለም አገራት የዲፕሎማሲ ማዕክል መሆኗን ሙሉ በሙሉ ያምናል፤ ይቀበላልም።

በዚህ መነሻ፣ ከተማዋ የብዝኃነትና የጋራ እድገት ማዕከል እንጂ የአንድ ዘረ ፈጅ አገዛዝ ብቸኛ መጫወቻ ስፍራ ልትሆን እንደማትችልም ድርጅታችን ያረጋግጣል። የአማራ ህዝብ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ አገሪቱ በስፋት በሚኖርባቸው አካባቢዎች፤ ፍትሐዊ የስልጣንና የሀብት ተጠቃሚነቱ መረጋገጥ እንዳለበት ድርጅታችን ያምናል።

በአሁኑ ወቅት፣ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ አዲስ አበባን በብቸኝነት የአንድ ወገንና ብሔር በበላይነት እንዲቆጣጠራት ለማስቻል የሚሰራው ሕግን የጣሰ፣ የዴሞግራፊና የጂኦግራፊ ለውጥ በምንም መልኩ ሕጋዊ፣ ሞራላዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።

አገዛዙ ''አገራዊ ምክክር'' በሚል የፖለቲካ ሽፋን በከተማዋ ላይ የሚያካሄደው ሴራና አሻጥር
የከተማዋን ነባር ኗዋሪዎች መብት የሚጥስ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያነቷን የሚክድና ታሪካዊ እውነታውን ለማዛባት የተሸረበና የአንድ ቡድን የበላይነትን በህዝባችን ላይ በኃይል ለመጫን ያለመ በመሆኑ፣ የዚህን አምባገነን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር መላው የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንዲያወግዙት፣ እንዲቃወሙትና እንዲታገሉት በድርጅታችን አፋብን ስም ጥሪ እናቀርባለን።

እንዲሁም በከተማዋ ቀደም ብለው ይኖሩ የነበሩትም ይሁን አሁንም የሚኖሩት 80 በመቶ ( በ1999 ዓ.ም በተካሄደው ህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት) የሚሆኑት ነባር ኗዋሪዎች አማራዎች ናቸው። በመሆኑም የህዝብ ስብጥርንም ሆነ ታሪካዊ እውነታን በኃይልና በተሳሳተ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመቀየር የሚደረገውን ማንኛውም የአገዛዙን ሴራ አጥብቀን የምንታገለው መሆኑን እንገልፃለን።

የአማራ ህዝብ በገዛ አገሩ ከገጠመው ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ ባሻገር ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የትጥቅ ትግል ውስጥ ለመግባት ካስገደዱት ምክንያቶች መካከል፦

በአዲስ አበባ ከተማ በአገዛዙ የተደቀነው የዴሞግራፊ ለውጥ አደጋ፣ የከተማዋን ቀደምት ባለቤቶችና ነባር ኗዋሪዎች በማፈናቀልና ማንነታቸውን በማጥፋት፣ የአማራ ህዝብ ከከተማዋ ጋር ያለውን ታሪካዊ እና ማህበራዊ ትስስር በመበጣጠስ ከህዝቦች ተፈጥሯዊ መስተጋብር ውጭ በሆነ መልኩ የባህል፣ የቋንቋና የተለያዩ አመለካከቶችን በኃይል ለመጫን የሚደረገው ሩጫ ይገኝበታል።

በመሆኑም፣ ድርጅታችን አፋብን ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ውስጣዊ አንድነቱንና አደረጃጀቱን ጠብቆ በመጓዝ፣ አምባገነኑና ከፋፋዩን አገዛዝ በጀመርነው ትግል ከስሩ ነቅለን በመጣል፣ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚስማማ፣ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያከብር ሥርዓተ መንግስት በመገንባት ፍትህ፣ እኩልነትና የሕግ የበላይነትን ከመትከል ባሻገር አዲስ አበባ የኗዋሪዎቿ፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ መኖሪያና ዋና ከተማ፤ የአንድነትና የእድገት ማዕከል ሆና እንድትቀጥል ይታገላል።

አገሪቱ ከገባችበት ጥልቅ የህልውና፣ የፍትህና የእኩልነት ቀውስ መውጣት የምትችለው የህዝቧን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በኃይል በማፈን፣ አገሪቱን የማያቋርጥ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት ወደ ገደል እየመራት ያለውን ዘረ ፈጁን የብልፅግና አገዛዝ፤ በሕዝባዊ ትግል ሙሉ በሙሉ መገርሰስ ሲቻል ብቻ መሆኑን አፋብን በፅኑ ያምናል።

በስተመጨረሻ የኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ በአዲስ አበባ ከተማና በህዝባችን ላይ በምክክር ስም የጠነሰሰው ዓይን ያወጣ የፖለቲካ አሻጥር የፈጠረው የህልውና በድርጅታችን ቁርጠኝነት፣ በህዝባችን ፅናትና በፀረ ብልፅግና ብሔራዊ ኃይሎች ትብብር በሚታጀበው የትግላችን አይቀሬ ድል የሚመመከት ይሆናል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)


MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

የአዲስ አበባ ጉዳይ ለምን ያሳስበኛል?

Post by MINILIK SALSAWI » 17 Aug 2026, 23:41

የአዲስ አበባ ጉዳይ ለምን ያሳስበኛል? Befeqadu Z. Hailu
👉🏾 የአዲስ አበባ ነዋሪ ስለሆንኩ፣
👉🏾የአዲስ አበባን እንቆቅልሽ መፍታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት ቁልፍ በር ስለሚከፍት።
አዲስ አበባ ተበድላለች?
👉🏾 አዲስ አበባ ታድላለችም፣ ተበድላለችም፦ የታደለችው የመላው ኢትዮጵያ ሀብት የሚፈስባት፣ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንባት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማዕከል ስለሆነች እና ነዋሪዎቿ አገሪቱ ማቅረብ ለምትችለው የተሻለ ዕድልና ጥቅማጥቅም ቅርብ ተቋዳሾች መሆን ስለሚችሉ ነው።
👉🏾 የተበደለችው ግን፦ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላት ብዝኃ ማኅበረሰብ ያቀፈች ከተማ ብትሆንም፣ ከ30 ዓመታት በፊት በብሔር መሥፈርት እንደተዋቀሩት ክልሎች ነዋሪዎቿ እውነተኛ የራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት አልተጎናጸፉም። ይህም የሆነው ከተማዋ የድኅረ-ብሔር እና የብዝኃ-ማንነት መኖሪያ በመሆኗ ነው።
አዲስ አበባ የማን ናት?
👉🏾 አዲስ አበባ ውስጥ ሁሉም ሰው መጤ፣ ሁሉም ሰው ባለቤት ነው፦ ታሪኳ እንደሚያመለክተው፣ የዛሬይቱን አዲስ አበባ ከብቦ የሚገኘው ሰፊው የሸዋ ግዛት ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በማክዙሚ (Makhzumi) ሡልጣኔት፣ በኋላም በኢፋት ሡልጣኔት ሥር የነበረ ግዛት ነበር። በ13ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ይኩኖ አምላክ የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ካንሰራራ በኋላ፣ የሙስሊም ሡልጣኔቶቹ ተዳክመው ሥፍራው በመካከለኛው ዘመን የክርስቲያን ነገሥታት ማዕከል ሆነ (በተለይ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የደብረ ብርሃንና የየካ/በርአራ ቤተ መንግሥት ይገኛል)። በ16ኛው ክፍለ ዘመን የአዳል ሡልጣኔት መሪው ኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ (አሕመድ ግራኝ) ክርስቲያናዊውን ሥርወ መንግሥት ካዳከመ በኋላ፣ የኦሮሞ ሕዝብ መስፋፋት ተከተለ። በዚህም ወቅት ትውፊታዊውን የገዳ ሥርዓት የሚከተሉ የኦሮሞ ማኅበረሰቦች (በዋናነት የቱለማ ጎሳዎች) በሸዋና አካባቢው ሰፍረው ኖሩ። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ፣ ዳግማዊ ምኒልክ መንግሥታቸውን ከአንኮበር ወደ እንጦጦ፣ በኋላም ፍልውሃ ወደሚገኝበት ፊንፊኔ በማውረድ አዲስ አበባን ቆረቆሩ። ከዚያ በኋላም ኢትዮጵያውያን ከሁሉም ማዕዘናት እየፈለሱ ከተማዋን የጋራ መኖሪያቸው አደረጓት።
አዲስ አበባ ኦሮሞዎችን በድላለች?
👉🏾 አዲስ አበባ የዳግማዊ ምኒልክ መንግሥት መናገሻ ሆና በተቆረቆረችበት እና በፍጥነት በተስፋፋችበት ወቅት፣ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ አርሶ አደሮች ባሕላቸዊ እና ቋንቋዊ ትስስራቸው ተሸርሽሯል። ቀጥሎም ከተማዋ ይበልጥ እየሰፋች በመጣች ቁጥር በርካታ የኦሮሞ ገበሬዎች ያለ በቂ ካሳና ተለዋጭ መተዳደሪያ ተፈናቅለዋል። የዚህ ያልተገባ መስፋፋት አሉታዊ ተፅዕኖ ዛሬም ድረስ በአጎራባች አርሶ አደሮች ላይ ስጋት ያሳድራል።
👉🏾አዲስ አበባ የተቋቋመችበትን ጊዜ ስናስብ ብሔረሰቦችን በአሁን አረዳዳቸው መረዳት የለብንም፤ ይህ አሁን እንደሚስተዋለው የተሳሳተ አጥፊ እና ጠፊ ምስል ይሰጠናል። እነ ዳግማዊ ምኒልክ ብሔረሰባዊ ማንነታቸውን እንደ "ሸዌ" ወይም ግፋ ቢል "ሀበሻ" ነበር የሚያዩት። "አማራ" የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ ክርስትና እምነታቸው ጋር ነበር የሚያያይዙት፤ በዚያን ወቅት የተጻፉ ጽሑፎችም "ሸዌ" እና "አማራ" የሚለውን እንደተለዋዋጭ ሳይሆን፣ እንደ ተለያየ ሕዝብ የሚጠቅሱበት ጊዜ ይበዛል። መንግሥታቸውም ውስጥ (በተለይ በሠራዊታቸው) በርካታ ኦሮሞዎች ነበሩበት፤ እርሳቸውም ኦሮምኛ ይናገሩ ነበር። መንግሥቱ ብሔረሰባዊ ሳይሆን እምነታዊ ቢባል ይሻላል። በወቅቱ ከጎጃም ይልቅ የሸዋ ኦሮሞ የቤተ መንግሥቱ ቤተኛ ነበር ማለት ይቻላል።
ታሪካዊ ችግሮችን ለመዘከር እና ከታሪክ ለመማር ምን ይደረግ?
👉🏾 የነዋሪዎች መብት ለድርድር አይቀርብም፦ አዲስ አበባ ታሪካዊና መዋቅራዊ ዕዳዎች ቢኖሩባትም፣ የነዋሪዎቿ ዴሞክራሲያዊና ዜግነታዊ መብት ግን በምንም መሥፈርት ለድርድር ሊቀርብ አይችልም።
👉🏾 ታሪካዊ እውነታዎችን በቅንነት መቀበል፦ ከተማዋ ታሪካዊ አመጣጧን ሙሉ በሙሉ ዕውቅና መስጠት አለባት። የአዲስ አበባ ሙዚየም ከከተማዋ መቆርቆር በፊት የነበረውን የታሪክ ቅብብሎሽ እና የነባር ነዋሪዎችን ታሪክ በግልጽ አጉልቶ ማሳየት አለበት።
👉🏾 ታሪካዊ በደሎችን መካስና ማረቅ፦ በከተማዋ ፈጣን መስፋፋት የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች ታሪክ ሊዘከር፣ ፍትሐዊ ካሳ ሊያገኙ፣ እንዲሁም ወደፊት የሚደረጉ የልማት መስፋፋቶች ተፈናቃይ የማይፈጥሩ እንዲሆኑ መገታት አለበት።
👉🏾 ብዝኃነትን የሚያንጸባርቁ ተቋማትን መገንባት፦ የከተማዋ አደባባዮች፣ ሙዚየሞች፣ መንገዶችና ፓርኮች የሁሉም ኢትዮጵያዊ መናኸሪያነቷን እና የታሪክ ባለቤትነቷን በእኩልነት የሚያስመሰክሩ መሆን አለባቸው።
👉🏾 ከሸገር ከተማ ጋር የጋራ ዕድገት ፍኖተ ካርታ መዘርጋት፦ ከተማዋ ከጎረቤቶቿ ጋር በሰላምና በቅንጅት ትዘልቅ ዘንድ፣ በአንድና በሁለት ትውልድ ውስጥ ወደ ሙሉ የጋራ ተጠቃሚነት የሚያሸጋግር ግልጽና ሕጋዊ የጋራ ማዕቀፍ መዘርጋት አለባት።
የአዲስ አበባ ሕጋዊ ሁኔታ ምን ይሁን?
👉🏾 አዲስ አበባ ራሷን የቻለች “የከተማ-ክልል” (City-State) መሆን አለባት። አሁን ያለችበት የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ እና የኦሮሚያ ክልል መናገሻ የመሆን ድርብ ተጠሪነት ለጊዜው የፖለቲካ መሸሸጊያ ቢሆንም፣ በዘላቂነት ግን የከተማዋንም ሆነ የኦሮሚያ ክልልን ተቋማዊ ዕድገት የሚያቀጭጭ ነው።
👉🏾አዲስ አበባ ወደ ክልልነት ስትሸጋገር ኦሮምኛ እና አማርኛን እኩል የሥራ ቋንቋ በማድረግ በሁለት ትውልድ ውስጥ እንግሊዝኛን ጨምሮ ባለብዙ ቋንቋ (multilingual) እንድትሆን ፖሊሲ ቀርፆ መሥራት። በዚህም ከተማዋ ከአጎራባች የኦሮሞ ኅብረተሰብ ጋር አዎንታዊ ግንኙነት እንድታዳብር ማድረግ ይቻላል።
👉🏾 አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለች ክልል መሆኗ ምንም ችግር አይስከትልም፤ ሐረሪ ክልልም በኦሮሚያ የተከበበች ነች። እንኳን ክልል አገርም በአገር ውስጥ ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ ሌሴቶ በደቡብ አፍሪካ ሙሉ ለሙሉ የተከበበች ሉዓላዊ አገር ነች።
👉🏾 የፌዴራል ከተማ መቀየር፦ አዲስ አበባ ፌዴራል ከተማ በመሆኗ የፖለቲካም የኢኮሚም ማዕከል የሆነች አውራ ከተማ ሆናለች። ይህንን የዕድገት ዕድል በፍትሓዊነት ለማሳደግ ለሦስቱ የፌዴራል መንግሥት ቅርንጫፎች አንድ አንድ ከተማ (ከሰሜን፣ ከደቡብ እና ከደቡብ ምስራቅ) በመምረጥ፣ እነዚህን ከተሞች የሚያስተሳስሩ ፈጣን የባቡር መንገዶችን በመገንባት እና ከተማዎቹ ባሕላዊ ማንነታቸውን ጠብቀው እንዲያድጉ መሥራትና የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስበት ማዕከሉን በማደብዘዝ የመሐል፣ ዳር አገር ክፍፍል መቀነስ።
👉🏾የኦሮሚያ ዋና ከተማን መቀየር፦ ሌሎች ክልሎች ከተሞቻቸውን በአምሳላቸው ለመቅረፅ የተመቻቸው ቢሆንም፣ ኦሮሚያ አዲስ አበባ ላይ በገባችው የታሪክ እሰጥ አገባ ምክንያት መቀመጫ ብታደርጋትም፣ ከተማዋን ግን የኦሮሚያ ክልል ብዙኃንን አስመስላ መቅረፅ አልቻለችም። አትችልምም። ይህንን ለማድረግ ሌላ ከተማ በመምረጥ እንደገና ማልማት መጀመር ይኖርባታል። ኦሮሚያ አዲስ አበባ ላይ ላፈራቻቸው ሀብቶቿ ካሳ ከተማዋን መጠየቅ የምትችልበት ዕድል በሥምምነት ሊወሰን ይችላል።
አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልል ሆኖ የፌዴራሉ መቀመጫ ብትሆን ምን ችግር አለው?
👉🏾 በአሁኑ የፖለቲካ ሥርዓት ክልሎች የተዋቀሩት በብሔር ማንነት ላይ ተመሥርተው ነው። ይሄ ደግሞ እንደ አዲስ አበባ ካሉ ድኅረ-ብሔር (cosmopolitan) እና ቅይጥ ነዋሪ ካላቸው (heterogeneous) ከተሞች ባህርይ ጋር ፈጽሞ አይጣጣምም።
👉🏾 ከዚህም በላይ፣ የኦሮሚያ ክልል ሕገ-መንግሥት የክልሉን ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት የሚያደርገው “የኦሮሞ ሕዝብን” ብቻ እንጂ “የኦሮሚያ ነዋሪዎችን” አይደለም። አዲስ አበባን በዚህ መዋቅር ሥር ማስገባት የከተማዋን ነዋሪዎች ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት እና የዜግነት መብት የሚያሳጣ አደገኛ አካሄድ ነው።

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አዲስ አበባ በኦሮሚያ ስር ከሆነች መስቀል አደባባይን ጨምሮ በኃይማኖት ስም የተሰየሙ አካባቢዎች ይቀየሩ ተብሎ አጀንዳ ተይዟል።

Post by MINILIK SALSAWI » 17 Aug 2026, 23:59

ውሃብያ የተገባለት ቃል!
በምክክሩ ሂደት እጅግ ፅንፈኛው አቋም ሲያራምድ የሰነበተው ውሃብያ ነው። የአገር ስም፣ የዘመን አቆጣጠርን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን እሴቶችን በሚያጠፋ መልኩ አቅርቧል። ከውሃብያ ፀረ ኢትዮጵያነት ባሻገር ከኦህዴድ ጋር ተመካክሮ የገባበት ነው። ውሃብያ አጀንዳውን በመሰል ጉዳዮች ወጥሮ ኦህዴድ ስራውን እንዲሰራ ጫና እያደረገለት ነበር።
ለዚህ ውለታው አዲስ አበባ በኦሮሚያ ስር ከሆነች መስቀል አደባባይን ጨምሮ በኃይማኖት ስም የተሰየሙ አካባቢዎች ይቀየሩ ተብሎ አጀንዳ ተይዟል። ይህ አጀንዳ አሁንም ለቀጣይ እንዲያልፍ ተደርጓል። ይህ ትብብር የተፈፀመው በኦህዴድና ውሃብያ ስም ነው። ኦህዴድ ውሃብያ በምክክሩ ያግዝ እንጅ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ስትሆን ብሎ ስሞችን ለመቀየር ቃል ገብቶለታል። ውሃብያ በምክክር ስም የሚፈልገው እሴትና ታሪክ ማውደም ነው። ከኦህዴድ ጋር ሲቀናጅ ደግሞ ፀረ ኢትዮጵያዊነታቸውን አስቡት። Getachew Shiferaw

Right
Member+
Posts: 5201
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: በአዲስ አበባ ከተማ እና ነዋሪወቿ ላይ የተደቀነው የህልውና አደጋ ..... ከ አፋብን ፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

Post by Right » 18 Aug 2026, 07:11

My people, please wake up and act as humans.

The Addis project- It is a homework designed by TPLF and inherited by PP.

So many will die and it will be a bloodbath for millions, because of Addis an old city with no sewage and no street number & a hygiene of a medieval town.

In my view, it is unnecessary and needs a critical alternative thinking. Unfortunately, we don’t have leaders capable of thinking that way.

To open up your minds: Egypt is building a brand new city replacing the old Cairo. An old city with partial sewage system & a far much modern city than Addis. Nigeria already have done that. So many others will follow.

The king would be with corrupt Gurages are pouring & wasting millions of borrowed dollars to build shiny buildings and decorate corridors totally ignorance of the fundamentals.

Think twice, if you are interested, I will suggest the alternative. By denying TPLF & PP, Addis & having the bloodbath they are so invested.

Post Reply