Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7878
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቀዳማዊ መስራች እና ቀዳማዊ ነብይ ቅዱሳን ፈረዖዎች

Post by Naga Tuma » 12 Aug 2026, 12:59

ቀዳማዊ መስራች ቅዱስ ፈረዖ ያልኩት ታላቁ ፈረዖ ምነስን ነዉ። የጥንት ግዜ የታች እና የላይ ግብጦች የተባሉትን ኣዋህዶ የመጀመርያዉ ስሩወ መንግስት ወይም ዳይናስቲ የተባለዉን ያቋቋመ ነበር ይባላል።

ከዚህ ፈረዖ በፊት የመንግስት መዋቅርን ያቋቋመ ሌላ መሪ ምድር ላይ የነበረ መሆኑን ኣላዉቅም።

ስርዓት ያለዉ የመንግስት መዋቅር ማቋቋም ቅዱስ ነዉ ብዬ ስለማስብ ይህ ፈረዖ ቅዱስ ነበር ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ቀዳማዊ ነብይ ቅዱስ ፈረዖ ያልኩት ታላቁ ፈረዖ አክናተንን ነዉ።

ይህ ፈረዖ ደግሞ ምድር ላይ የመጀመርያዉ የአሓዱ ዓምላክ ነብይ የነበረ እና ለስደት የተዳረገ ነዉ የሚል ታሪክ ግልጽ ሆኗል።

የኢትዮጵያዉ ሎቴት ቃሉ ለካ ኣንተ ነህ! ያለዉ ይህ የአሓዱ ዓምላክ አባት ነብይ ታላቅ ፈረዖ በኋላ የተሰሙት የኣይሁዶች ቶራ፣ ክርስትና፣ እስልምና ሁሉም አሓዱ ዓምላክ ማለት ቅዱስ ነዉ ስለሚሉ ይህ ፈረዖም ቅዱስ ነበር ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ብዙ መለኮታዊ ምልክቶችን እያጠናሁ በዚህ የፍርድ ዘመን የተባለዉ ግዜ እግዝኣብሔር ፍርዱን እየሰጠ ያለዉ ለእነዚህ ቅዱሳን ፈረዖዎች መንፈስ ይመስለኛል።

እንተርኔት ዉስጥ የሚታይ የቅዱስ ፈረዖ ምነስ ምስል፥

https://www.google.com/search?q=pharaoh ... b&ie=UTF-8

እንተርኔት ዉስጥ የሚታይ የቅዱስ ፈረዖ አክናተን ምስል፥

https://www.google.com/search?q=pharaoh ... b&ie=UTF-8

የሁለቱንም የጥንት ቅዱሳን ፈረዖዎች ምስሎችን ትክክለኛ መሆናቸዉን እኔ እርግጠኛ ኣይዴለሁም።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7878
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ቀዳማዊ መስራች እና ቀዳማዊ ነብይ ቅዱሳን ፈረዖዎች

Post by Naga Tuma » 17 Aug 2026, 17:57

የጥንታዊ ኢትዮጵያ ህዳሴ ብሎም ለዐለም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ ማለት በጣም ጥልቅ ጽንሰ ሀሳብ ነዉ።

እነዚህ የጥንት ኢትዮጵያ ቅዱሳን ፈረዖዎች ያልኳቸዉ የኖሩት ሶስት ሺህ ዓመታት በፊት ነዉ። ከስደት ዘመን በፊት ነዉ።

እየሱስ የተወለደዉ ሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ነዉ።

ከስደት ዘመን እስከዚህ ዘመን ከፀሓይ መዉጫ እስከ ፀሓይ መጥለቅያ ብናየዉ የጥንት ኢትዮጵያ ህዳሴ ብሎም ለዐለም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የሚጀምረዉ ከፀሓይ መዉጫ ሲሆን ክርስትና የሚጀምረዉ ፀሓይ ወጥታ ረፋድ አረት ሰዓት ላይ ይሆናል።

ለማነጻጸር ያህል የጥንት ግሪክ ጎደስ አቴና የኖረችዉ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት ነዉ።

ስለዚህ አምስት መቶ ዓመታት ገደማ በፊት ኣዉሮፓ ዉስጥ የተደረገዉ የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የጀመረዉ ፀሃይ ወጥታ ረፋድ ሁለት ሰዓት ገደማ አከባቢ ነዉ።

የጥንት ኢትዮጵያ ህዳሴ ብሎም ለዐለም ሁለተኛዉ ሬይነሳንስ የምያርመዉ ከፀሓይ መዉጫ እስከ ረፋድ አራት ሰዓት ያለዉን ታሪክ እና የሃይማኖት ታሪክን ይሆናል።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ የሳተዉን ከፀሓይ መዉጫ እስከ ረፋድ ሁለት ሰዓት ገደማ ያለዉን የሚሞላ ይሆናል።

ይህን እርማት ማድረግ ተቀባይነት የማያገኘዉ በእነማን እንደሆነ መገመት ያስቸግራኛል። ምክንያቱም ይህን እርማት ማድረግ ጽድቅ የሚሆን ይመስለኛል።

የማስተዉላቸዉ መለኮታዊ ምልክቶችም የዚህ ጥልቅ ህዳሴ ይመስሉኛል።

Post Reply