Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሶስት ወጣቶች 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸናቸው ታወቀ

Post by MINILIK SALSAWI » 11 Aug 2026, 23:22

(መሠረት ሚድያ)- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ኢሰብአዊ እና ዘግናኝ ድርጊት መፈጸሙ ተሰምቷል።

ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት የአማራ ክልል ተወላጆች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በግፍ መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው አገና በተባለችው ልዩ ቦታ ሲሆን ወንጀሉን የፈጸሙት የመንግስት ኃይሎች ከአካባቢው የአበሽጌ አገና ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተጠቅሷል።



ንጹሐኑ ዜጎች ከተሳፈሩበት መኪና ከወረዱ በኋላ እጃቸውን ወደኋላ በገመድ በማሰር አሰቃቂ እንግልት እንደፈጸሙባቸው እና በመጨረሻም ጭንቅላታቸውን በጥይት በመምታት በግፍ እንደረሸኗቸው ታውቋል።

የግፉ አፈጻጸም በዚህ ብቻ አላበቃም።

"ገዳዮቹ የሟቾቹን አስከሬን ወደ ትውልድ ቀያቸው ናቻ ቀሊት ቀበሌ ወስደው በመጣል ማንም ሰው አስከሬናቸውን እንዳያነሳና እንዳይቀብር ጥብቅ ክልከላ ጥለው ነበር" ብለው ለሚድያችን ቃላቸውን የሰጡት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ናቸው።


"በዚህም ምክንያት የተገደሉት ሰዎች እጃቸው እንኳን ሳይፈታ ለሦስት ሙሉ ቀናት ክፍት ቦታ ላይ ተጥለው በእንስሳ እንዲበሉ እዛው እንዲቆዩ ተደርጓል" በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።

አስከሬኖቹ በተለይም ጭንቅላታቸው አካባቢ በተመቱበት የጥይት ምት ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመጎዳቱ ገጽታቸውን ለማየት እና ለመለየት ጭምር የሚያስቸግር እና አሰቃቂ እንደነበር ተሰምቷል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የመድረክ ውይይቶችና የምክክር ሂደቶች ስለ ሰላም ቢወራም ከጀርባ ግን የዜጎች ህይወት በዚህ መልኩ በስውር ማለቁና ኢሰብአዊ ጥቃት መፈጸሙ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ሀዘንና ስጋት ዳርጎታል።

| መሠረት ሚድያ |

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

በቅርቡ አበሽጌ ወረዳ ውስጥ የተገደሉት ሶስት ወጣቶች ቤተሰቦች ግድያውን አስተባብሉ የሚል ጫና እየደረሰባቸው መሆኑ ታወቀ

Post by MINILIK SALSAWI » 13 Aug 2026, 05:09

(መሠረት ሚድያ)- ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት የአማራ ክልል ተወላጆች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በግፍ መገደላቸውን ሚድያችን ከሁለት ቀን በፊት መዘገቡ ይታወሳል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በመንግስት ሀይሎች የተፈፀመው ይህ ኢሰብአዊው እና ዘግናኝ ድርጊት በብዙዎች ዘንድ ቁጣ እና ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን አሁን ደግሞ እነዚሁ አካላት ቤተሰቦቻቸውን በገንዘብ፣ በሽምግልና እና በመሬት እያባበሉ እንዲሁም አልፎ ተርፎ እያስፈራሩ መሆኑ ታውቋል።

"ገዳዮች የሟች ቤተሰቦችን በገንዘብ፣ በሽምግልና እንዲሁም በመሬት ስጦታ እያባበሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ ጥፋተኞቹ በህግ ከተጠየቁ በህይወት መኖር እንደማይችሉ ቤተሰቦችን እያስፈራሯቸው ነው" በማለት አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ እና ድርጊቱ ሲፈፀም ዝም ብሎ መመልከት ህሊናዬ አልፈቀደም ያሉ የመንግስት የመረጃ ምንጭ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።


በተለይም ለሟች ቤተሰቦች "የሞቱበትን ምክንያት አናውቅም፣ መንግስት አልገደላቸውም በሉ፣ አሊያ ግን እኛ ከታሰርን እናንተው ትሞቷታላቹሁ" በማለት ቀጥተኛ እና ከባድ የሞት ዛቻ እያቀረቡባቸው እንደሆነ እኚሁ ምንጫችን ተናግረዋል።

ድርጊቱ እጅግ ዘግናኝ እንደነበር የሚገልፁት መረጃዎች ንፁሀን ዜጎቹ ከመኪና ከወረዱ በኋላ እጆቻቸውን ወደኋላ በገመድ በማሰር አሰቃቂ እንግልት እንደተፈፀመባቸው ይናገራሉ፣ በመጨረሻም ጭንቅላታቸውን በጥይት በመምታት በግፍ ተረሽነዋል ብለዋል።

አንደኛው የአካባቢው ነዋሪ እንደተናገሩት "ገዳዮቹ የሟቾችን አስከሬን ወደ ትውልድ ቀያቸው ዳኖ ቀበሌ ወስደው በመጣል ማንም ሰው አስከሬናቸውን እንዳያነሳና እንዳይቀብር ጥብቅ ክልከላ ጥለው ነበር" ብለው ቃላቸውን ሰጥተዋል።

"በዚህም የተነሳ የሟቾቹ አስከሬን እጃቸው እንደታሰረ ለሶስት ሙሉ ቀናት ክፍት ቦታ ላይ ተጥሎ ለአውሬ እንዲጋለጥ መደረጉ ሁኔታውን ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል" ይላሉ።

አስከሬኖቹ በተለይም ጭንቅላታቸው አካባቢ በተመቱት የጥይት ምት ምክንያት ሙሉ በሙሉ በመጎዳቱ ገፅታቸውን ለማየት እና ለመለየት የሚያስቸግር ሁኔታ ላይ እንደነበሩ ተጠቁሟል።

ሚድያችን የሟቾቹን ቤተሰቦች በዚህ ዙርያ ለማናገር ሙከራ ያረገ ቢሆንም ካለባቸው ስጋት የተነሳ ለግዜው አልተሳካም።

በሌላ በኩል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ይህን የሚድያችንን መረጃ በተመለከተ በዛሬው ዕለት ማብራሪያ ሰጥቷል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ዋልጋ እና ዳርጌ አካባቢ ከተለያዩ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት ጫካ የገቡና ራሳቸውን ቀስ በቀስ "ፋኖ" እያሉ የሚጠሩ ሽፍታዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል።



አቶ ተመስገን ካሳ

ኃላፊው አክለውም እነዚህ አካላት በኦሮምኛ፣ ከምባትኛ እና በሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች ላይ ብሔር ተኮር ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር ተናግረው መንግስት እነዚህ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ማድረጉን እና የሰላም አማራጭ መቅረቡን የፀጥታ ቢሮው አስታውቋል።

አማራጩን የተቀበሉት የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ህዝቡ እንዲቀላቀሉ ሲደረግ መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ አንቀበልም ባሉት እና በግድያ ላይ በተሰማሩት ሽፍታዎች ላይ ግን ህግን የማስከበር እርምጃ መወሰዱን ቢሮው አረጋግጧል።

መንግስት የሚወስደው እርምጃ ብሔርን የለየ ነው ተብሎ 'በሀሰተኛ ሚዲያዎች' የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ እና የክልሉን መልካም ገፅታ ለማጠልሸት ያለመ መሆኑንም አስተባብሏል።

የቢሮው ሀላፊ ይህን ይበሉ እንጂ ሶስቱ ወጣቶች ስለመገደላቸው ቀጥተኛ ማስተባበያ አልሰጡም።

| መሠረት ሚድያ |

Post Reply