Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

MINILIK SALSAWI
Senior Member
Posts: 12640
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

አዲስ አበባን ከሌሎች ክልሎች በተለየ የኦሮሚያ የባለቤትነት አጀንዳ አገር የማፍረስ ፕሮጀክት የመጨረሻው ክፍል ነው!

Post by MINILIK SALSAWI » 11 Aug 2026, 23:55

አገር የማፍረስ ፕሮጀክት ነው!
አዲስ አበባን ከሌሎች ክልሎች በተለየ የኦሮሚያ የባለቤትነት አጀንዳ አገር የማፍረስ ፕሮጀክት የመጨረሻው ክፍል ነው!
1) ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያና በሌላው አካባቢ በእምነትና ብሔራቸው እየተጠቁ ነው። ግጭቶች ተበራክተዋል። የግጭት ማዕከል ከሆኑት ንፁሃን በማንነት ከሚጠቁባቸው ክልሎች አንዱና ዋነኛው ኦሮሚያ ነው። በሚደረገው ቅስቀሳ ምክንያት ኦሮሚያ ለዜጎች ሲሆን በሆነችበት ይህን የጥላቻ ፖለቲካ ወደ አዲስ አበባ ማምጣት ግጭቱን ጭምር ማዛመት፣ መከራውን ወደ ማዕከል ማዛመድ ነው። በመሆኑም ወለጋና አርሲ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም የግጭት ማዕከል እንዲሆን ማድረግ ነው።
2) አዲስ አበባ ላይ በቁጥር ከኦሮሞ በላይ አማራና በአጠቃላይ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ኦህዴድ አሁን በሚሄድበት ማጭበርበር ከተማቸውን የሚቀሙ ዜጎች ዝምታን አይመርጡም። ብልፅግና አጭበርብሮ ቢወስን ነገ "የእናንተ ከተማ ነች" የሚባሉ የኦሮሞ ብሔርተኞች የአዲስ አበባን ህዝብ ሀብትና ማንነቱን ልቀማ ነው የሚሉት። ይህ ደም አፋሳሽ ግጭት፣ አገር አፍራሽ እልቂት ያስከትላል።
3) ብልፅግና ለስሙ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መመስረት እፈልጋለሁ ይላል። አዲስ አበባ በሌሎች አካባቢዎች ያልተለመዱ ኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳዮችን የሚጋሩባት፣ በዚህ ሁሉ ነውጥ ሚዛን አስጠባቂ የሆነች ከተማ ነች። ይህን እሴት ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኞች ይጠሉታል። አደጋ ነው ብለው ያምናሉ። አዲስ አበባን አጭበርብረውም ሆነ በግድ የኦሮሞ ነች ካሉ ይህ ትስስር ሻሸመኔ ላይ እንዳፈረሱት ብትንትናውን ያወጡታል። በዚህ የግጭት ማዕበል ውስጥ ሚዛን የሆነውን ማዕከል አፍርሰው አገር ያፈርሳሉ።
4) ሀረርን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ሀውልትና ቅርሶችን አፍርሰዋል። በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ ሞክረዋል። ኦህዴድ አጭበርብሮ አዲስ አበባን የኦሮሚያ ነች እንዳለ ቅርስና ሴቶችን፣ ሀውልትና ሙዚየሞችን ለማፍረስ የሚመጣው የተቀሰቀሰ ኃይል ይታወቃል። ይህ አገር ሊያፈርስ የሚችል ግጭት ይቀሰቅሳል።
5) ኢትዮጵያውያን የጋራ ቋንቋ፣ የጋራ ሰንደቅ፣ የጋራ መዝሙርን ጨምሮ ሌሎች ለአገር ግንባታ የሚጠቅሙ እሴቶችን ለተናጠል እንዲያዳብሩ ተደርገዋል። እነዚህ እሴቶች የጋራ የሚሆኑት አዲስ አበባ ላይ ነው። ኦህዴድ በአሁኑ የማጭበርበር ጉዞው አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች ካለ የጋራ የሚያደርጉት እሴቶች ያሏት አዲስ አበባም አዲስ የኦሮሞ ብሔርተኞች መነሃሪያ ትሆናለች። የጋራ እሴቶቹ ይመታሉ። የአገር አንድነት እሳቤ፣ የጋራ እሴት ወዘተ ይመታል። ኢትዮጵያውያን የቀራቸውን ማስተሳሰሪያ ገመድ ይበጥሳል።
6) በጦርነቱም ሆነ በሌሎች ችግሮች የተማረሩ ባለሀብቶችና ሌሎች ዜጎች የመጨረሻ አማራጫቸው አዲስ አበባ ነው። የሚመርጡት የኢኮኖሚ እድሉን ብቻ አይደለም። ከሌሎች አካባቢዎች በተሻለ ውጣልኝ የሚል ስለሚቀንስ፣ አዲስ አበባ ባላት ሁኔታ ለደህንነታቸው የተሻለች ስለሆነች፣ የአብሮነት እሴቱን ተማምነው ነው። ትልልቅ እሴቶችን በመገንደስ የሚታወቀው ኦህዴድ አጭበርብሮም ደልሎም አስፈራርቶም የማይሆን ውሳኔ ካሳለፈ ይህን የአዲስ አበባን ማዕዘንነት ሰብሮ አገር ያፈርሳል።
7) አዲስ አበባ የኤምባሲዎችና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት መገኛ ነች። የኢንቨስትመንት ፍሰቷ የተሻለ ነው። በኦህዴድ ባለባትነት ቀመር ከወደቀች ይህን ተከትሎ በሚመጣ ግጭት የውጭ ተቋማትም ዘግተው ይወጣሉ። ከለላዎቿ ይሳሳሉ። ወለጋና ሎሎቹ ላይ እንደከረመው የግጭት ቀጠና ትሆናለች። አገር ወጥሮ ከያዘው ከማዕከሉ መፍረስ ይጀምራል።
ኢትዮጵያውያን መረባረብ ያለባቸውም የኦህዴድ አካሄድ በዚህ መንገድ አገር እንዳያፈርስ ነው!

Post Reply