እኔ ስለ ሳይንስ ተመራማሪ የነበርኩኝ እንጂ ስለ መንፈሳዊ ወይም መለኮታዊ ነገር የተመራመርኩኝ ሰዉ ኣይዴለሁም።
ትርፍ ግዜ ሳገኝ ስለ ጥንት ታሪክ እያነበብኩኝ፣ ተዓምራዊ ገጠመኞችን እያሰላሰልሉኝ ምናልባትም እየተመራሁ ስለ መንፈሳዊ ወይም መለኮታዊ ነገሮች የተገነዘብኩኝ ይመስለኛል።
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቃሉ የማይቀለበስ ቃሉ ያለዉን ዛሬ ኣስታዉሼ ለመጀመርያ ግዜ ቃሉ ያለዉ ወይም ያስባለዉ ፀሓይን ይሆን ኣልኩኝ።
የኢትዮጵያ የአሓዱ ኣምላክ ቀዳማዊ ነብይ ቃሉ ፀሓይ ነበር።
አዲስ አበባ የሚል ስም ኣወጡ የተባሉት የኢትዮጵያ እቴጌ ስማቸዉ ፀሓይቱ ነበር።
እኔ ያስተዋልኳቸዉ በርካታ ተዓምራት የምያመለክቱት ወደ ኢትዮጵያ ቀዳማዊ ነብይ እንጂ ወደ እስራኤላዊዉ ኣዳኝ የተባለዉ ኣይዴለም።
ቀዳማዊዉ የኢትዮጵያ ነብይ እስራኤላዊ ፕሮፌት ሙሴ ወይም በእስልምና ነብዩ ሙሳ የተባለዉ ነዉ።
በዚህ ስምንተኛዉ ሺህ ወይም የፍርድ ዘመን የተባለ ግዜ እስራኤላዊ ፕሮፌት ሙሴ የተባለዉ ተገልጦ ኢትዮጵያዊ ነብይ ነበር ማለት ከስደት ዘመን በፊት የነበረ ቅዱስ መንፈስ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ያብባል ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
ይህ ከሆነ የኢትዮጵያ ቀዳማዊ ነብይን የከዳ ወይም የከዳች ኢትዮጵያዊ ንስሃ ግባ ወይም ግቢ ማለት ምክር ሊሆን የሚችል ይመስለኛል።