Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44040
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በትናንሽ ነገር ግዜውን የሚያባክን ለትላልቅ ነገር ግዜ አይኖረውም፡ አቢይ አህመድ አሊና ቀይ ባህር!

Post by Horus » Today, 12:11

ይህን የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ አላማ ያሳካ ቀን አቢይ አህመድ አሊ የታላቅ መሪነት ማማ ላይ ይወጣል! አለምንም ጥርጥር! አጼ ንጉሰ ነገት አይሆንም ነገር ግን ከንጉስ ምኒልክ ቀጥሎ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ በታሪክ ይዘገባል!


Horus
Senior Member+
Posts: 44040
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በትናንሽ ነገር ግዜውን የሚያባክን ለትላልቅ ነገር ግዜ አይኖረውም፡ አቢይ አህመድ አሊና ቀይ ባህር!

Post by Horus » Today, 12:47

ኢትዮጵያ የዉሃ ስልጣኔ ነች ።

ኢትዮጵያ በዉሃዋ የጥንታዊ ግብጽና ኑባ ስልጣኔን የፈጠረች አገር ብቻ ሳትሆን ዛሬም የግብጽና ሱዳን ሕልውና በመዳፏ ውስጥ ይዛ ያለች ኃያል አገር ነች። ያለ ኢትዮጵያ ግብጽ ወይም ሱዳን የሚባሉ የሰው መኖሪያ አገሮች ሊኖሩ አይችሉም ።

ኢትዮጵያ የመላ አፍሪካ አህጉር ተራሮችን 75% ባለቤት የሆነች ብቸኛዋ ያፍሪካ የዉሃ ባለሃብት አገር ስትሆን በአንድ ቃል የ21ኛውና ከዚያም ማዶ አንዱ የአለም የዉሃ ስልጣኔ ነች ።

ከዚህ በኋላ አለምን የሚገዛው የተፈጥሮ ሃብት ዘይት ወይም ወርቅ አይደለም ፤ የዉሃ ተፈጥሮ ሃብት ነው ። የሰው ልጅ ሁሉ ምግቡን የሚፈጥረው በዉሃ ነው። የሰው ልጅ መንቀሳቀሻ ኃይሉን ሁሉ የሚፈጥረው በዉሃ ነው ። WATER IS THE SOURCE OF ALL ENERGY. የኑክሌር ኃይል እንኳን ለመፍጠር ያለ ዉሃ አይሆንም ።

ዋናው የዉሃ ኃይል ግን የቴክኖሎጂ ኃይል ማመንጨቱ አይደለም ! የሰው ልጅ ሕይወት እራሱ የሚመነጨው ከዉሃ ነው። የሰው ልጅ አካል 2/3ኛው ውሃ ነው ። ዉሃ ጠፋ ማለት ሕይወት ጠፋ ማለት ነው። ስለሆነም ...

ኢትዮጵያ በጥቂት አመታት ውስጥ ውሃን እንደ ፔትሮሊየም በቱቦና በበርሜል ለአለም ገበያ ታቀርባለች! ዛሬ ላይ ኦይል ታንከር የሚባሉት ግዙፍ መርከቦች ዋተር ታንከር ተብለው በሚሊዮን ቶን የሚለኩ የኢትዮጵያ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ተሸክመው በቁቂያኖሶች ላይ ይንጎማለላሉ! ምናልባትም በእኛ እድሜ!

ኢትዮጵያ ይህን መሰል እጅግ ገናና እጅግ ግዙፍ ነገ የሚጠብቃት አገር ነች!

ስለህነም ታላቁ የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን እና ለመባል ይህ የኢትዮጵያ ታላቅነት ነገን እንደ ብርሃን ማየት የግድ ነው!

አቢይ አህመድ አሊ ይህን ራዕይ እያየው ይሆን?



Post Reply