የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን በየእስር ቤቱ ያጎረ መሪ፣ በአደባባይ የተቹትንና የነቀፉትን ሁሉ እያሳደደ የገደለ፣ ያስገደለ፣ ያሰደደና ያዋረደ፣ ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን የመንግስት ሹሞች፣ የክልል ባለሥልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦችን ጭምር ባዘጋጃቸው የኮሬነጌኛ አይነት ስውር ገዳይ እስኳድ ሕይወታቸውን እየቀጠፈ ያስወገደ፣ በሕዝቦች መካከል ጥላቻ እንዲነግስና ግጭት እንዲባባስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚሰራና ግጭቶችን ሆነ ብሎ የሚጠነስስ፣ ተፋላሚ የፖለቲካ ሃይሎችን በንቀት አይን እያየ ለሰላም ውይይትና ድርድሮች ሆን ብሎ እንቅፋቶችን የሚፈጥር፣ ለሥልጣኑ ሲል አገር ቢበተን እንኳ ግድ የማይሰጠው፣ ባጭሩ ጨካኝና መዋሸት የማይሰለቸው አምባገነን መሪ ባለበት አገር በብሔራው ምክክር ስም "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" ማለት የአመቱ ያፈጠጠ የፖለቲካ ቧልት ነው።
በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የሚነግዱ ልሂቃን የዚህ ጥፋት ተባባሪዎች ናቸው። ....... የብልጽግና ደጋፊ፣ አባልና ብልጽግናን ቢያንስ ባለመቃወም የሚታወቁ ሰዎችን በሕዝብ ስም ሰብስቦ ብሔራዊ ምክክር ማድረግ በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ መቀለድ፣ ሕዝብን መናቅና መዶለት እንጂ አገሪቱን ለማዳን የሚደረግ ምክክር ሊሆን አይችልም። የዚህን የግፍ አገዛዝ እድሜ ለማራዘም የሚተጉ ተቋማትና ልሂቃን በትውልድም፣ በታሪክም መጠየቃቸው አይቀርም።
(Via @Yared Hailemariam )
-
MINILIK SALSAWI
- Senior Member
- Posts: 12362
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact:
-
MINILIK SALSAWI
- Senior Member
- Posts: 12362
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact: