Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 44070
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ትክክለኛው ሸባል!

Post by Horus » 01 Jul 2026, 00:02

የቃል ትርጉም፣
ሸባል = ሰርግ (በሃረሬኛ ሸዋል የሚሉት እኛ አዳብና የምንለው መተጫጫ በዓል ነው) ቃሉ ግን ሸባልና ሸዋል አንድ ነው !
አዘመኘ = ሰርገኛ

እዚህ ቪዲዮ ላይ እንደ ምታዩት በተራራማው የጉራጌ አገሮች ከህዳር ጀምሮ ማታ ማታ ውርጩ ከዜሮ በታች ስለሚወርድ የእንሰት ቅጠሎች ሁሉ ያቃጥላል ፣ ያደርቃቸዋል ። ይህ ሰርግ በዚያን ሰሞን እነደ ተደረገ ያሳያል ።

እንደ ምታዩት ወንዱ ሙሽራዋን ይዞ ማምሻው ላይ ከገባ በኋላ ያገሬ ጎረምሳ ሁሉ እስከ ሚነጋ ክትፎ እየበላ ሲጨፍር ያድራል! ዘፈኑም ናዛኙ ናሻኙ ይባላል! እናነጋለን እናነጋለን ማለት ነው!

የወንዱ ዋና ሚዜ ለሙሽራዋ እንደ ወንድሟ ማለት ነው በሕይወት እስካሉ ድረስ እንደ ወንድሟ ነው የሚጠብቃት! ፈረሱ ላይ አቅፎ ይዟት የምታዩት ነው።