Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7778
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቃሉ ማለት ምን ማለት ነዉ?

Post by Naga Tuma » 29 Jun 2026, 19:46

የዚህን ቃል ትርጉም ጥልቀት እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ኣላስተዋልኩም።

የማያው ቻለም ባለም ታሪክን ኣንበቤ ለመጀመርያ ግዜ ጥልቀት እንዳለዉ ኣስተዋልኩኝ ወይም ያስተዋልኩኝ ይመስለኛል።

የእኔ የታሪኩ አረዳድ ስህተት ካልሆነ ቃሉ ማለት ስለ ሰዉ ሳይሆን ከሰዉ አፍ የሚወጣ የኣምላክ መንፈሳዊ ምልክት ወይም መልዕክት ነዉ።

ቃሉ ማለት ከኣምላክ ወይም እግዝኣብሔር ጋር መንፈሳዊ ግንኙነት ኣለኝ የሚል ሰዉ ነዉ።

ቃልቸ ወይም ቃሉ የተባለ ሰዉ ከኣምላክ ጋር መንፈሳዊ ግንኙነት ኣለኝ የሚል ከሆነ ቃልቸ ወይም ቃሉ ማለት መልኣክ ነኝ ማለቱ ይሆናል።

የሰዉ ልጅ ከኣምላክ ጋር መንፈሳዊ ግንኙነት ያለኝ ነዉ ማለት ይችላል።

ከባዱ ጥያቄ ከኣምላክ ጋር ግንኙነት ኣለኝ የሚል የሰዉ ልጅ መልዓክ ነኝ ካለ ኣምላክ የምያዉቀዉ ወይም ለምልክቶቹ መንገድ የምያደርገዉ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል ይሆናል።

በእኔ አሰላሰል መልስ ሊሆን የሚችለዉ መልዓክ ነኝ ያለ ሰዉ ሳይሆን ያ ሰዉ የሚናገረዉ ቃል የኣምላክ መንፈሳዊ መልዕክት ምልክት ያለዉ መሆን የሚችል ከሆነ ነዉ።

ይህ ማለት ሰዉ ማጤን ያለበት ቃሉዉን ሳይሆን ያ ሰዉ የሚናገራቸዉ ቃላት ዉስጥ መንፈሳዊ ምልክቶች ኣሉ ወይ መሆን ኣለበት።

ጥንታዊ ሆኖ እንደ ባህል የሚገመት ዉስጥ ሁሉም ሰዉ ቃሉ መሆን ኣይችልም።

ካልተሳሳትኩ ያ ሰዉ ንጹህነት ያለዉ መሆን ኣለበት።

ኣሁንም ካልተሳሳትኩኝ ቃሉ በበስመ ዓብ እና በቅዱስ መንፈስ የምያምን ነዉ። በወወልድ ማመኑን ኣላዉቅም።

በኣንድ ዓምላክ ወይም አሓዱ ዓምላክ ማመን መጀመር የጥንት ኢትዮጵያ ቃልቸ ወይም ቃሉ የተባለዉን ለስደት የዳረገ ሆነ።

መንፈሱ ከስደት መመለሱ በስመ ዓብ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ እና አሓዱ ኣምላክን ማመንን የተሳካ ያደርገዋል።

ወወልድ እና በወወልድ ምክንያት ዐለም ላይ የዘመናት ትርምስን በ325 ኤ ድ የተደረገዉን የኒስያ ካዉንስል ምናልባት ነብይ የነበረ በግምት ወወልድ ተብሎ ይሆናል በማለት ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።