Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7781
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ይድረስ ለትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን እናቶች፥ እግዝያር ኣለ ማለት እና እግዝያር ዬለም ማለት መሃል መንገድ ዬለም

Post by Naga Tuma » 23 Jun 2026, 18:48

እዚህ መድረክ ላይ መላልሼ እንደጻፍኩኝ ለእኔ እንደገባኝ ከሆነ የዚህ የፍርድ ዘመን የተባለዉ መሠረታዊ ጥያቄ እግዝያር ኣለ ወይስ እግዝያር ዬለም ሆኗል።

እግዝያር ለጥንታዊ የኢትዮጵያ ነብይ ተገልጦ ነበረ ማለትን የሃይማኖት መጽሓፎች ዘግበዉት ስያስተምሩ ኖሩ።

በዚህ ዘመን የመንግስት ስልጣን ላይ ተጽዕኖ ያለዉ እግዝያር ዬለም ያለ ኢትዮጵያዊ መኖሩን ኣልሰሙም ይሆን?

የእኔ ክርክር በዚህ የፍርድ ዘመን የተባለ ግዜም እግዝያር ተዓምራትን እያስቆጠረ ተገልጧል ነዉ።

የጥንቱ መገለጥ ኣምላክ ኣንድ ነዉ ያስባለ ነበር።

የዚህ ዘመን መገለጥ እግዝያር ዬለም ላለዉ ዳያብሎስ ተዓምራትን የምያስቆጥር መሆኑ ነዉ።

ስለዚህ እግዝያር ኣለ ማለት እና እግዝያር ዬለም ማለት መሃል መንገድ ዬለም።

ፈርሃ እግዝያር የሆናችሁ ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን እናቶች መጠየቅ ያለባችሁ መለኮታዊ ጥያቄ እግዝያር ዬለም ያለዉን ዳያብሎስን መሆን ኣለበት ማለት መልካም ምክር ይመስለኛል።

እግዝያር ዬለም ካለ ከዳያብሎሱ ጋር የተዳበሉ ልጆችሽ ተዓምራዊ በሚመስሉ መንገዶች ዘላለማዊ ፍርድ ያገኙ መሆናቸዉ ለእኔ ግልጽ የሆኑ ናቸዉ።

ከኢትዮጵያ ነፃነት ትግል ብለዉ ብዙዎች ለመታገል ቆራጦች ሊሆኑ ይችላሉ።

ከኢትዮጵያ ነፃነት ለማለት ወይ ትግል ሜዳ ዉረድ ወይም ቀምሴ ስር ግባ ወኔ ቀስቃሽ ነዉ።

እግዝያር ማለትን እግዝያር ኣለ ከሚል ኢትዮጵያዊ ነፃ ማድረግ ይቻላል?

እግዝያር ማለትን ከወላድ እናት በላይ የምታዉቅ ያለች ኣይመስለኝም።

ይህ ግምት ትክክል ከሆነ ከኣብራኮችሽ የተገኙ፣ የተዋጣላቸዉ ምሁራን የማይባሉ፣ እግዝያር ዬለም ያለ ዳያብሎስ መንጋ ሲሆኑ አረ ልጆች እግዝያር ኣለ በሉ ማለት መልካም ምክር የማይሆን ይሆን?

በተጨማሪ የእግዝያር ቁጣ ምልክቶች ሲገለጡ የማያጤኑ ወይም የማይሰሙ የቁጣ ምልክቶች የምያስከትሉት ምን ይሆን ማለት ብልህነት ነዉ።

እንደ ኣንድ ግለሰብ የእኔ ምኞት መልካሙን ነዉ።

ወደፊት የሚሰማ መለኮታዊ ነገር ከኣንድ ግለሰብ ቁጥጥር ዉጪ ነዉ።

ተዓምራቱ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ ናቸዉ።

ዉሳኔ 96 እና መለስ ዜናዊ ከታሪክ መጽሓፍ የማይፋቁ ናቸዉ።

ፍትሃዊ ሆነ ፍርደ ገምድል ፍርድ መስጠት እንጂ ፍርድ መቀበል የለመደ ለማይመስል ኢሳያስ ሜይ 18፣ 2026፣ የተገለጠዉ ለዘላለሙ መፋቅ የማይችል ብይን ነዉ።

የዳያብሎስ ሥራ ምን ዐይነት እንደሆነ የሚከተለዉ ቪድዮ ዉስጥ የታጨቁ ወደ ሃጥዓት የሚመሩ ማዳመጥ ብቻ በቂ ነዉ።

እግዝያር ዬለም ማለቱ እንዳለ ሆኖ ማለት ነዉ።



ይህ ቪድዮ መጀመርያ የተለጠፈዉ እዚህ ነዉ፥ Explosive!