እኔ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም።
ትላንት የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ምርጫ አድርጓል ። የፖለቲካ ምርጫ የአንድ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ካልቸር ነው ። እሱም የፖለቲካ ውሳኔ መወሰኛ ዘዴ ወይም ስልት ማለት ነው።
ሶስት ሺ ዘመን እድሜ ያላት ኢትዮጵያ ሰባት ግዜ ብቻ ብሄራዊ የፖለቲካ ምርጫ ማድረጓ ኢትዮጵያ የምርጫ ካልቸር እንደ ሌላት መቶ በመቶ የሚያረጋግጥ መረጃ ሃቅ ነው።
ዘመናዊ ፖለቲካ እንደ ዛፍና አበባ በራሱ ተፈጥሮ የሚያድግ ነገር አይደለም ።
የፖለቲካ ስርዓት ሆን ተብሎ በእቅድ ፣ በኢንቴንሽ ፣ ታስቦበት የሚፈጠር ማህበራዊ ስራ ነው ። የፖለቲካ ስርዓት መሰረቱ የፖለቲካ ሃሳብ ፣ የፖለቲካ ፍልስፍናና የፖለቲካ ቲኦሪ ቢሆንም ሃሳብ በራሱ ካልቸር አይሆንም።
የፖለቲካ ካልቸር የሚፈጠረው፣ የሚያድገው በስራ ነው ፤ በፕራክቲስ ነው፤ በሙከራ ፣ በጥረት ፣ ነው ፤ በተሞክሮ ነው።
ኢትዮጵያ እውነቱን እንናገር ከተባለ ፣ ብሄራዊ የፖለቲካ ፍልስፍና የላትም፤ ብሄራዊ የፖለቲካ ቲኦሪ የላትም ፤ ብሄራዊ የፖለቲካ ካልቸር የላትም ።
ለምሳሌ ትላንት የሆነውን እንመልከት ...
ምርጫ ካልቸር ነው ብያለሁ ፣ ካልቸር ደሞ የሚሰራው በስራ ፣ በተግባር ነው ብያለሁ ። ትላንት የሆነው ያ ነው። አንድ ትንሽዬ የምርጫ ካልቸር የመፍጠር ትንሽዬ ሙከራ ።
በሌላ በኩል ሰላማዊ ተፎካካሪዎችና የአመጽ ተፎካካሪዎችን ተመልከቱ ...
ሰላማዊ ተፎካካሪው አንድ ብሄራዊ ፓርቲ ማደራጀት ስላልቻለ በምርጫው ውስጥ ነበረ ማለት ስህተት ነው ። የምርጫ ካልቸር ለመፍጠር ጥረት አደረገ ማለት ፍጹም ስህተት ነው ። ካልቸር በወረቀት ላይ ሃሳብን ጽፎ መበተን አይደለም ። ካልቸር ስራ ነው ። ካልቸር ተግባር ነው።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሰላማዊ ተፎካካሪ የፖለቲካ መደብ በኢትዮጵያ ገና አልተወለደም ። ይህም የሆነው ብሄራዊ የፖለቲካ ፍልስፍናና ቲኦሪ ያረቀቀ ብሄራዊ ተፎካካሪ ፓርቲ ስለሌለ ነው ።
በአመጽ ተፎካካሪው በመሰረቱ ኢትዮጵያ ለሶስት ሺ ዘመን ያገዛዝ ስርዓት ያከናወነችበት ቅድመ ፊውዳልና የፊውዳሊዝም ፖለቲካ ካልቸር ነው ። በትግሬ ፣ አማራና ኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ገንኖ ያለው የአመጽ ተፎካካሪነት ካልቸር አልነቀል ያለው የፊውዳልና ቅድመ ፊውዳል ካልቸር ነው ። ይህ ደሞ እነዚህን ማህበረሰቦች በኋላ ቀርነት እስር ቤት ከርችሞ ያሰረ ታሪካዊ ችግር ነው ።
በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሪያሊቲ ይህ ነው።
ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍልስፍና የላትም ፤ የፖለቲካ ቲኦሪ የላትም ፣ የዘመናዊ ፖለቲካ ካልቸር የላትም ።
ብልጽግና ምንም አይነት ተፎካካሪ የሌለው፣ ያልነበረው ስለዚህ ነው ።
ካልቸር ሃሳብ አይደለም ፤ ምርጫ ግን ካልቸር ነው! የአበሻ ችግር ደሞ ይህ ነው!
Last edited by Horus on 02 Jun 2026, 13:46, edited 8 times in total.
Re: ካልቸር ሃሳብ አይደለም ፤ ምርጫ ግን ካልቸር ነው! የአበሻ ችግር ደሞ ይህ ነው!
ትላንት በምርጫው እለት ፖስት ያደረኩት ...
ምርጫ ካልቸር ነው።
ፖለቲካ ካልቸር ነው።
የፖለቲካ ምርጫ የፖለቲካ ካልቸር ነው።
ምርጫ ፍጥረት አይደለም ፤ ምርጫ ዛፍ አይደለም፣ ምርጫ ህዋስ አይደለም ፣ ምርጫ ተፈጥሮ አይደለም
ምርጫ አንድን ውሳኔ መወሰኛ ዘዴ ነው።
የፖለቲካ ምርጫ አንድን የፖለቲካ ውሳኔ መወሰኛ ዘዴ ነው።
ዛሬ የተካሄደው የፖለቲካ ምርጫ አንድ በኢትዮጵያ የተካሄደ የፖለቲካ ካልቸር ነው።
ባለም ላይ ከ180 በላይ አገሮች አሉ ። ከ180 በላይ የፖለቲካ ካልቸሮች አሉ ። እያንዳንዱ አገር የራሱ ካልቸር አለው ፣ የራሱ ፖለቲካ ክላቸር አለው።
የኢትዮጵያ ምርጫና የኬንያ ምርጫ አንድ አይነት ካልቸሮች አይደሉም ። የሚወስኑት የፖለቲካ ውሳኔ አንድ አይነት አይደለም ፤ የሚኖሩት የፖለቲካ ኑሮ አንድ አይነት ስላልሆነ።
አውሮፓዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ ስለማይኖሩ ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካል ስላልሆኑ ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ካልቸር ውስጥ የሉበትም።
የኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ምርጫ የኢትዮፕያዊያን ፖለቲካ ውሳኔ ነው ። ፖለቲካ ሌላ የተፈጥሮ መለኪያ የለውም ። የተፈጥሮ ሳይንስ ካልቸር ቢሆንም ፣ የፖለቲካ ካልቸር ግን ሁሉን የሚገዛ ሳይንስ ወይም እውቀት አይደለም።
የፖለቲካ ካልቸር ዘዴ ነው። አንድ ሕዝብ ፖለቲካውን ለመስራት የሚጠቀምበት ፣ የመረጠው ዘዴ ነው ።
ዛሬ የተወሰነው ምንድን ነው?
ለሚቀጥለው 5 አመት የኢትዮጵያ ዋና መሪ ፣ ያገር ራስ ፣ ርዕሰ ብሄር ማን መሆን እንዳለበት ሕዝብ የወሰነበት ዘዴና ተግባር ነው ።
አንድ ሰውም ሆነ አንድ ሕዝብ የሚወሰነው ውሳኔ ጥሩ ነው ? መጥፎ ነው? ትክክል ነው? ስህተት ነው የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው ።
ስለሆነም የኢትዮጵያ ዋና መሪ ማን ይሁን በሚለው ላይ በግልጽ አቢይ አህመድ ይሁን የሚሉ ቢኖሩም ሌላ ግለሰብ በግልጽ ያገር ራስ መሪ መሆን አለበት ተብሎ ሲጠቀስ አልሰማሁም።
ኢዜማ ፓርቲ ቢሆንም ብርሃኑ ነጋ ጠ/ሚኒስት ይሁን ብሎ ካቢይ ጋር ሲያወዳድር አልሰማሁም
ከዚህ በተረፈ በመላ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃ ሁ ያልገባው ፖለቲካኛ ባይ ነኝ አንዱም በግልጽ ወጥቶ የራሱን የፖለቲካ ፍልስፍናና ፕላን አሳውቆ ካቢይ አህመድ ተጻራሪ ቆሜ ተለክቼ ስለምበልጠው እኔን ለራስ መሪነት ምረጡኝ ያለ አንድም ግለሰብ የለም ።
ያለው የፖለቲካ ደንቆሮች ጫጫታ ነው ።
ያለው በግድና በግልበት በጦር መሳሪያ ራስ መሪ መሆን አለብኝ የሚል የ21ውኛው ዘመን አህያ ነው።
ያለው ምንም የማይመለከተው ቅኝ ገዥ ነጭ የራሱን የፖለቲካ ካልቸር አበሾች እንደ ኃይማኖት ተቀብለውት በሱ ክላቸር እንደንገዛ የሚፎግረው ፈረጅና የሱ ደቀመዝሙር ነው ።
ዛሬ የተፈጸመው የፖለቲካ ካልቸር ካልተስማማቸው የሚያሻሽሉትም ሆነ የሚለውጡት እራሳቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ናቸው ።
ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን የቆመው ለዚያ ነው ።
ይህም ሆነ ያ ኢትዮጵያ ሁልግዜ ፣ ምንግዜም በራሷ የፖለቲካ ካልቸር ፣ በራሷ የፖለቲካ ምርጫ መንግስት አቁማ ራስ መሪ መርጣ እንደ አገርና ስርዓት መጽናት አለባት ።
የሆነውም የሚሆነውም ያ ነው!