Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Mesob
Member
Posts: 3048
Joined: 23 Dec 2013, 21:03

ኧረ ጉድ ነው ፡ ዓረብ አገር እንጂ በክርስትያንዋ ኢትዮጵያ በሐበሻ ምድር ?

Post by Mesob » 01 Jun 2026, 19:24

ኧረ ጉድ ነው ፡ ዓረብ አገር እንጂ በክርስትያንዋ ኢትዮጵያ በሐበሻ ምድር ይሄ ይታሰባል እንዴ?
እንዴት ተብሎ ? መሳፍንቶቹ አገርና ሃይማኖት ያራክሳሉ?
ኣቶ መለከት ይሄ ነገር ከየት ጎረጎሩት?

Meleket wrote:
09 Apr 2025, 03:25
ከ170 ዓመታት በፊት የነበረን እዉነታ የሚገልጽ ታሪክ ነው። የአጤ ቴዎድሮስን ታሪክ የጣፉት ደብተራ ዘነብ፡ "ከጥንት ከጠዋቱ ግብረሰዶማዊነት በጦቢያ የነገሥታት ሰፈር ነበር" ነው እያሉን ያሉት። ይገርማል የ“ቅድስት ኢትዮጵያ” ነገር!


https://en.wikipedia.org/wiki/Ali_II_of_Yejju

ምስሉ ላይ የሚታዩት ሰዉዬ ግብረሰዶማዊ ነበሩ የተባሉት ኢትዮጵያዊው ራስ ዓሊ ናቸው። ይህ ክዋኔ ከዛሬ 170 ዓመታት በፊት “ግብረሰዶም” የሚለውን ቃል መእመናን ከኖህ ታሪክና ከሓዋርያዉ ጳውሎስ መልእክት ጋር በማዛመድ ብቻ ያዉቁ በነበረበት ወቅት፡ ይህ ኣጸያፊ ተግባር በጦቢያ ምድር እንደነበረ ፍንትዉ ኣድርጎ የሚያሳይ ኢትዮጵያዊ መረጃ ነው።

ከዛሬ 170 ዓመት በፊት ይህ እርኵስ ተግባር ጦቢያ ውስጥ ከነበረ፡ ኣሁን ላይ ሃይማኖት በቅጡ ካልተሰበከና ካልተኖረ፡ ምን እዬሆነ እንዳለ ለመገመት ኣያዳግትም።

ታላቁ ቋንቋ ኣማርኛ ሲወላገድ ኣያምርበትም! ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊት ልዩነት አለው። ኤርትራዊና ኤርትራዊትም እንዲሁ። ለሴት ኢትዮጵያዊት ወይም ኤርትራዊት ይባላል እንጂ ጽሑፉ ርእስ ላይ እንዳለው ለሴት ኢትዮጵያዊ ወይም ኤርትራዊ ኣይባልም። መልካሙን ሁሉ ለሰላም ተመኘንላት ለአንባብያንም እንዲሁ! የዚህ ጽሑፍ ዓላማ እንዲያዉ ታሪኩን መልክ መልኩን ለማስያዝ እንጂ ለእንካ ስላንትያ ኣይደለም።

Meleket wrote:
08 Apr 2025, 07:42
ለእንካ ስላንትያ ኣይደለም፡ እግረመንገዳችንን አንድ መጠሃፍ ላይ ያገኘነውን ታሪክ ለማጋራት ያህል ነው። ማስረጃው ታሪኩ መልክ መልኩን እንዲይዝ ያግዘናል።

[የቴዎድሮስ ታሪክ። በብርሊን እንደሚገኝ አብነት፡ ኣሳታሚው ዶክቶር እኖ ሊትመን። በፕሪንስቶን ከተማ፤ ከኡኒቤርሲታ መጣፎች ቤት። በኙዩርክ ከተማ ከሻርልስ ስክሪብኔር ልጆች። በላይፕጺግ ከተማ ከኦቶ ሃረሲቢትጽ በ፲፱፻ወ፪ ዓመት። የቴዎድሮስ ታሪክ በደብተራ ዘነብ ገጽ ፪-፫]

እራስ ጕግሣም በሞቱ ጊዜ ልጃቸው ይማም ባልጋው ተቀመጡ፡ ፪ዓመት ተዘጠኝ ወር ገዙ ሞቱ። እራስ ማርዬ ወንድማቸው ባልጋው ተቀመጡ ወደ ትግሬ ዘመቱ ከሰብአ ጋዲስ ጋር ደብረ ዓባይ ላይ ተዋጉ። የሰብአ ጋዲስ ልጅ ሐጐስ በነፍጥ ገደላቸው እራስ ማርዬን። ሐጐስንም የራስ ማርዬ ሰው ገደለው። ሰብአ ጋድስም ተያዙ። ብዙ ሰው አለቀ። ድሉ የራስ ማርዬ ሆነ። በነጋው ኣዛዥ ውብ እሸት ሰብአ ጋዲስን ገደላቸው። እራስ ማርዬም ፫ዓመት ታንድ ወር ገዙ። በራስ ማርዬ አልጋ ወንድማቸው እራስ ዶሪ ተቀመጡ፡ ፫ ወር ገዙ ሞቱ። በእራስ ዶሪ ኣልጋ። እራስ አሊ የወንድማቸው የአሉላ ልጅ ተቀመጡ። ፳፪ ዓመት ገዙ። ጕግሣም ኣሉላን፥፡ ይማምን ማርዬን ዶሪን ወለዱ። አሉላም እራስ ኣሊን ወለደ ተወይዘሮ መነን። አሉላም አርዝም አደንድን የሚባል እንጨት ስለ ምንዝር በአፉ ነክሶ ወደ ሴት በደረሰ የእንጨቱ ወሀ ከሆዱ ገባ አፍጥጦ ገደለው። እራስ አሊም የማይገባ ጳውሎስ እንደተናገረው ወንዶች በወንዶች ነውር ያደርጋሉ እንዳለ ባደረጉ ጊዜ ዘመዶቻቸውም እጅግ ድኃ በበደሉ ጊዜ፤ የአበሻ ሰዎች ሁሉ ፍርድን መልካም መስራትን እግዚአብሔርን መፍራትን በተዉ ጊዜ፡ በስም ክርስቲያን ተብለው በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ፈንታ አስማት ምንዝር ስካር ቧልት ጥመት ባደረጉ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ቀናዒ ነውና ንጉሥ ቴዎድሮስን ኣስነሣ ሁሉን የሚቀጣ።[የቴዎድሮስ ታሪክ በደብተራ ዘነብ ገጽ ፪-፫]

Meleket
Member+
Posts: 5158
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ኧረ ጉድ ነው ፡ ዓረብ አገር እንጂ በክርስትያንዋ ኢትዮጵያ በሐበሻ ምድር ?

Post by Meleket » 02 Jun 2026, 02:39

Mesob wrote:
01 Jun 2026, 19:24
. .. .
ኣቶ መለከት ይሄ ነገር ከየት ጎረጎሩት?

Meleket wrote:
09 Apr 2025, 03:25
...
Meleket wrote:
08 Apr 2025, 07:42
...

[የቴዎድሮስ ታሪክ።
በብርሊን እንደሚገኝ አብነት፡ ኣሳታሚው ዶክቶር እኖ ሊትመን።
በፕሪንስቶን ከተማ፤ ከኡኒቤርሲታ መጣፎች ቤት።
በኙዩርክ ከተማ ከሻርልስ ስክሪብኔር ልጆች።
በላይፕጺግ ከተማ ከኦቶ ሃረሲቢትጽ በ፲፱፻ወ፪ ዓመት።
የቴዎድሮስ ታሪክ በደብተራ ዘነብ ገጽ ፪-፫
]


ወዳጃችን Mesob የታሪኩን ምንጭ ያገኘንበትን መጸሓፍ ርእስ እላይ እንዳመለከትነው ቁልጭ አድርገን አስቀምጠነዋል እኮ። እርስዎ ደግሞ ከዚህ viewtopic.php?f=2&t=340014 ጎርጉረውና ጠቅሰው አምጥተውታል።

የኛ ዋንኛ ዓላማ የአሁኗን ነፍሲኄርት ኤርትራዊት ኢጣሊያዊት የፊልም ኢንዳስትሪ እና የውበት ፈርጧን የዘውዲ ኣርአያን ስም ለማጠልሸት፡ ከዚያም ጋር አስታኮ ኤርትራዊነትን ለማሸማቀቅ የተወረወረ የቃላት ሚሳይልን በተመሳሳይ መልኩ በታሪካዊ ሓቅ ታጅበን ማምከን ላይ ያተኮረ ብቻ ነበር። ለእንካ ሰላምትያና ለመነቋቆርም አልተነሳንም። ነገር ግን የእህቶቻችን የልጆቻችንና የእናቶቻችን ስም ለማጠልሸት የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት ተንኮል ለማምከን ሁሌም በቅን መንፈስ እንነሳለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Post Reply