Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 43084
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ቴዲ አፍሮና ዲለን ፔጅ ፡ 2ቱ የኢትዮጵያ እውነታዎች ሙግት!

Post by Horus » Today, 14:29

ኢትዮጵያ የዘመናቶች ውስብስብ ችግር ሰለባ የሆነች አገር ነች ።

ኢትዮጵያ እጅግ በትንሹም ቢሆን የመፍትሄ መንገድ በመሻትና ጥቂት መፍትሄዎችን በመፍጠር ላይ ያለች አገር ነች ።

ኢትዮጵያ የሚሊዮኖች ድሃ ሕዝብ አገር ነች ።

ኢትዮጵያ የጥቂት ሃብታም ሕዝብ አገር ነች ።

ኢትዮጵያ የዚህ ሁለት ተቃራኒ እውነታዎች ውሁድ (ውህደት) አገር ነው ።

ቴዶ አፍሮ ድሃዋ ኢትዮጵያን ገልጿል ።

ዲለን ፔጅ (ወይም አዶናይ) ሃብታሟን ኢትዮጵያ ገልጿል።

ሁለቱም ፣ ቴዲ አፍሮም ዲለን ፔጅም የኢትዮጵያ ሪያሊቲ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ናቸው ።

ትልቁ ነገር ፣ እጅግ ትልቁ ነገር የነዚህ ሁለት ተጻራሪ እውነታዎች ሙግትና ፍጭት ሳይታፈኑ መካሄዳቸው ነው !

ድህነት እስካልጠፋ ድረስ ሃብታምነት ብቸኛው እውነታ ሊሆን አይችልም!

ሃብታምነት እስካልተደገፈና እስካልገነነ ድረስ ድህነት ሊጠፋ አይችልም!

እነዚህ 2 የኢትዮጵያ እውነታዎችን መካድ አላዋቂ ሰጎን መሆን ነው።

መፍትሄው ሃብታምነትን ማበረታታት እና ድህነትን ለማጥፋት አንድ ሕዝብ ፣ አንድ ሃስብ ፣ አንድ ሰራተኛ መሆን ነው!

ቴዲ አፍሮ የችግራችን ገላጭ ብርሃን ነው!

ዲለን ፔጅ የስኬታች ገላጭ ተስፋ ነው!

ስለዚህ 2ቱም አንድ ናቸው! ሁለቱም የኢትዮጵያ ውስጥና ውጭ ፣ ፊትና ኋላ ናቸው!



Last edited by Horus on 23 May 2026, 15:00, edited 1 time in total.



Horus
Senior Member+
Posts: 43084
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮና ዲለን ፔጅ ፡ 2ቱ የኢትዮጵያ እውነታዎች ሙግት!

Post by Horus » 51 minutes ago

ይህን ዜማ 28 ሚሊዮን ግዜ በአንድ ወር ተሰምቷል! ይህ ለምን እንደ ሆነ ምክኛት አለው! ሪያሊቲ ስለሆነ ነው!



Horus
Senior Member+
Posts: 43084
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮና ዲለን ፔጅ ፡ 2ቱ የኢትዮጵያ እውነታዎች ሙግት!

Post by Horus » 11 minutes ago

ቶቶት! አሸናፊ ! እጹብ ድንቅ !

Post Reply