ወይን የማጥፋት ሴራ ራስን ለማጥፋት ነው
አብይ ፈጠን ብልህ ከወይን ታረቅ
ጦርነት አገርሽቶ ኢትዮጵያ እንዳትደቅ
ኢሳያስ ደስታው ነው አገር ቢበተን፥
ግብጽም ደስተኛ ናት ብንበታተን
ወይንን ይዘህ ነው አገር የምታድን
ይች መገለጥ መጣች 8 አመት በፊት በእንጠጦ ተራራ
መንፈስ ቅዱስ አዞት ሲቃትት አንተ እንድትመራ፥
ጥቂት ሳምንታት ቀድሞ ስላንተ ሳይወራ
አዲስ አበባ ተዘግታ በቄሮ ተወጥራ
ከወይን ሳትታረቅ መንግስትህ አትፀናም
ከትግራይ ሳትታረቅ መንግስትህ አትፀናም
ትሆንለህ ተቅበዝባዥ እንደ ሳኦል እረፍት የለሽ
ሰይጣን እያሰቃየው ቀንም ሌሊትም ተናካሽ
ወይንን ሳታጠፋ መንግስትህ አትፀናም ያለህ
የጋለ ሰይፍህን በትግራይ ላይ በጭካኔ ያስነዘረህ
የቴድሮስ መንፈስ ነው ጎንደር የለከፈህ
Axumezana የኢየሱስ አገልጋይ ማንም የማያውቀው
ይችን ከነገረህ ውርድ ከራሴ ብሎ መፅሐፉን ዘጋው
