Borkena
2h
·
#አሳዛኝ_መረጃ ወጣቱ በፖሊስ አባል የግፍ ግድያ ተፈፀመበት
በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "ሽሮ ሜዳ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተገኝ ባልቻ (ኦሮሮ) የተባለ ወጣት በአንድ የፖሊስ አባል በትናንትናው ዕለት ተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።
ሟች ተገኝ ባልቻ ቀደም ሲል በሽሮ ሜዳ አካባቢ ስኬታማ የነጠላ ነጋዴ እንደነበርና ራሱንና ቤተሰቡን ከመደገፍ አልፎ ለጓደኞቹና ለተቸገሩት ደራሽ እንደነበር ይነገራል።
ይሁን እንጂ በልማት ምክንያት የንግድ ሱቁ በመፍረሱና ንብረቱ በመጥፋቱ ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራና ለስነ-ልቦና ቀውስ መዳረጉን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።
ይህንን ተከትሎ በገባው ከፍተኛ ቁጭትና ንዴት ውስጥ ሆኖ፣ ከአንድ ወር በፊት "ሞተር ተራ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከአንድ የፖሊስ አባል ጋር በፈጠረው አለመግባባት ለቀናት ታስሮ እንደነበር ገልፀዋል።
ወጣቱ በቁጥጥር ስር ውሎ በነበረበት ወቅት አባቱ ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን፣ ተገኝ የአባቱን የቀብር ስነስርዓት እንኳን ሳይታደም በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ ሀዘኑን እንዲያሳልፍ ተገዷል።
ከሳምንታት በፊት በዋስትና ተፈቶ የአባቱን መቃብር በመጎብኘት ሀዘኑን እየተወጣ ባለበት ወቅት ነው ድንገተኛው ግድያ ጥቃት ደርሶበታል ብለዋል።
ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ተገኝ ከጓደኞቹ ጋር በለመደበት ስፍራ ተቀምጦ እያለ በፓትሮል መኪና የመጡ የጸጥታ አካላት "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" በሚል ወደ ሽሮ ሜዳ (02 ጣቢያ) ወሰዱት" የሚሉት የመረጃ ምንጭ፣ ቀደም ሲል ከሟች ጋር ፀብ ነበረው የተባለው የፖሊስ አባል በጣቢያው በር ላይ በነበረበት ወቅት ሽጉጡን አውጥቶ አራት ጊዜ በመተኮስ ወጣቱን ህይወቱን እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ከአካባቢው መሰወሩ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ሽሮሜዳ ትላንት አንድ የጋሞ ተወላጅ በፖሊሶች ተገድሎ በመሞቱ አካባቢው ውጥረት መንገሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በድርጊቱ እጅግ ማዘናቸውንና ድርጊቱን የፈጸመው የህግ አስከባሪ በህግ እንዲጠየቅ ጥሪ አቅርበዋል።