Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42712
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ቴዲ አፍሮ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞችና የፖለቲካ ልማት ጥያቄ

Post by Horus » 20 Apr 2026, 01:17

ከዚህ በታች ያሉት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ዝርዝር የራሴ ናቸው ፣ የቴዲ አፍሮ ወይም የሌላ ሰው አይደሉም ። በእኔ እምነት አስተያየትና ግምት አርቲስት ቴዲ አፍሮ ከ1 እስከ 30 ባሰፈርኳቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ ተቃውሞ ይኖረዋል ብዬ አላምንም። የአቢይ አህመድ መንግስትም እነዚያን 30 ያገር ጥቅሞችን ለመፈጸም ከሞላ ጎደል የሚያደርገውን ጥረት ቴዲ አፍሮ እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ የሚደፍና አበጀህ የሚል ሰው እንደ ሆነ አምናለሁ ።

አርቲስት ቴዲ አፍሮ በመንግስት ላይ ሂስና ትችህ ካለው በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ላይ ይሆናል ብዬ አምናለሁ።

አንደኛው ፡ የኑሮ ውድነትና የድሃው ሕዝብ ጭንቀት በተመለከተ ይሆናል

ሁለተኛው፣ በኢትዮጵያ ምንም አይነት የፖለቲካ ልማት ፣ Political development or Political reform አለ መኖርና ያብይ አህመድ መንግስት ይህን ግዙፍ ብሄራዊ ችግርና ቀውስ ለመቅረፍ ምንም አይነት አላማ እቅድ የሌለው በመሆኑ ነው። እነዚህ የፖለቲካ ልማት ችግሮች ከ31 እስከ 34 ቁጥር ባሉት ብሄራዊ ጥቅሞች ሊስት የጠቀስኳቸው ናቸው ። በአንድ ቃል ኢትዮጵያ ሕገ መንግሳታዊ የፖለቲካ ማህበረሰብ አልሆነችም ፣ አይደለችም ። ይህን ከኢኮኖሚው ልማት እኩል የሆነን ብሄራዊ ችግር አዳፍኖ ስለብልጽኛ ብቻ ማተኮር ሄዶ ሄዶ በአገር አቀፍ ቀስና ፍንዳታ መከሰቱ አይቀሬ ነው።

አቢይ አህመድ የፖለቲካ ልማት የሚባለው ያገር ሥራ ማንሳት አለበት ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ከብዙ በጥቂቱ...
1) የኢትዮጵያ ባህር በር እና ባህር ኃይል ጥያቄ
(2) የህዳሴ ግድብና ሌሎች አባይ ላይ ስለሚገነቡ ግድቦች
(3) የኢትዮጵያ የውሃ ህብትና የውሃ ኃይል ጥያቄ
(4) የአረንጓዴ አገር አቀፍ የደን ልማት ጥያቄ
(5) ኮሪደርና የኢትዮጵያ ከተccሞች ዝመና ጥያቄ
(6) የኢትዮጵያ እርሻ ዝመናና የመስኖ ልማት ጥያቄ
(7) የማዳበሪያ ፋብሪካ ግምባታ
(8) የእርሻ ትራክተር ፋብሪካ ግምባታ
(9) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
(10) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የቢሾፍቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
(11) የኢትዮጵያ ቴሌኮም
(12) የዲጂታል ኢትዮጵያ ፕሮጀክት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030
(13) የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ ክህሎት ፕሮጀክት ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ
(14) የኢትዮጵያ እስፔስ ሳይንስ ምርምር ጉዳይ
(15) የኢትዮጵያ ኑክሊየር ኃይል ምርመር ጉዳይ
(16) የኢትዮጵያ እስቶክ ማርኬት ጉዳይ
(17) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮጀክት
(18) የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት
(19) የኢትዮጵያ እስታጽቲክስ ሳይንስ እድገት
(20) የኢትዮጵያ አርትና ስነጽሑፍ እድገት ጉዳይ
(21) የኢትዮጵያ ማዕድን ኢንዱስትሪ እድገት ጉዳይ
(22) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን
(23) የኢትዮጵያ ብረት ኢንዱስትሪ
(24) የነዳጅ ኢንዱስትሪ መገንባት
(25) ግዙፍና ዘመናዊ የአገር መከላከያ ጦር መገንባት
(26) የኢትዮጵያ ምድር ባቡር አካዳሚና የምድር ባቡር ኢንዱስትሪ ልማት
(27) የሴራሚክስ ኢንዱስትሪ ልማት
(28) የኢትዮጵያ ሲሚንቶ ኢንዱስትሪ
(29) የገጠር ኮሪደር (ዘመናዊ ገጠር) ልማት
(30) የጠራ ከፍተኛ ትምህርት ስርዓት
መሰራት ያለባቸው
(1) አዲስ ሕገ መንግስት
(2) ፕሬዚዳንታዊ መንግስት
(3) ኢጎሳዊ ፌዴሬሽን
(4) ኢጎሳዊ የፓርቲዎች ፖለቲካ

Tiago
Member
Posts: 3307
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: ቴዲ አፍሮ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞችና የፖለቲካ ልማት ጥያቄ

Post by Tiago » 20 Apr 2026, 02:04

ተራ ጬኸት :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
Crows / Ravens don't look like rainbows n unicorns, yes, it's that shallow.
little this idiot knows they are smart birds.
What next? the owl and the bat?
eagles are apex predators,that's all.


Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ቴዲ አፍሮ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞችና የፖለቲካ ልማት ጥያቄ

Post by Naga Tuma » 20 Apr 2026, 13:21

ራስ ማሞ፥ እግዜር ከሌለ ፒር ሪቪዉ ያላለፈን የእኔ ነዉ በማለት ልልፋ።

ዳያብሎስነት፥ እግዜር በምን ጆሮዎቹ ይሰማል፣ ባዶ ጩሀት ማለት።

ከ18 ዓመታት በፊት ሁለታችሁም እየሱስ እያላችሁ ሁለታችሁም የተጠየቃችሁት ስለ ጥንት ኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪ ከጥንት ኢትዮጵያ ስደት ነበር።

ቃሉ፣ ለካ ኣንተ ነህ! ሳይሰማ በፊት ነበር።

ከ18 ዓመታት በኋላ በዚህ ግዜም ሁለታችሁም እየሱስ እያላችሁ ሁለታችሁም የተጠየቃችሁት እግዜር ላለመኖሩ ምን ማረጋገጫ ኣላችሁ ነዉ።

የሁለታችሁም ስማርትነት 18 ዓመታት በፊት ሆነ ከ18 ዓመታት በኋላ እየሱስን የላከዉ እግዜር ነዉ እያላችሁ እግዜር ላለመኖሩ ማረጋገጫ ኣለን ማለታችሁ መሆን ኣለበት።

ፕሮፌሰር ቃሎ የተባለዉ እንደታዘበዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7365
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ቴዲ አፍሮ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞችና የፖለቲካ ልማት ጥያቄ

Post by Naga Tuma » 20 Apr 2026, 16:47

ስለዚህ እየሱስ እያሉ እየሱስን የላከ እግዜር ዬለም ከሚሉት ራስ ማሞ እና ዘ ላስት ሉሲፈር ጽምዶ እና ተዓምራትን ማየት እግዜር ቢኖር ነዉ ብሎ ፕሮፌሰር ቃሎ ከተባለዉ ብቸኛ ዬትኛዉ ኣሳማኝ ይሆናል?

Horus
Senior Member+
Posts: 42712
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቴዲ አፍሮ ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞችና የፖለቲካ ልማት ጥያቄ

Post by Horus » Today, 21:29

መንግስት መቃወምና የኢትዮጵያ ንሄራዊ ጥቅሞችን መደገፍ ምን ማለት እንደ ሆነ ለማይገባህ የፖለቲካ መሃይም ይድረስ!


Post Reply