Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fiyameta
Senior Member+
Posts: 21670
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

ሾልኮ የወጣው የብልጽግና ሰነድ የያዘው ጉድ ⚔️ ⚙️ የሻዕቢያ እጅ ረጅም ነው ነገር ግን ወደ ፍትህ ያዘነብላል። ⚙️ ⚔️

Post by Fiyameta » 29 Mar 2026, 19:46



2.4: ሻዕቢያ (ኤርትራ) ፡ ከስትራቴጂያዊ ወዲጅነት ወደ ሕሌውና ሥጋት

የሻዕቢያ (የኤርትራ መንግሥት) ወቅታዊ አቋምና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ያለው ጣልቃ ገብነት ለመንግሥት ስልጣን ቀጣይነት እጅግ ውስብስብና አደገኛ ሥጋት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ቀደም ሲል በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት የነበረው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጋብቻ አብቅቶ፣ አሁን ላይ ሻዕቢያ ለሥርዓታችን መውደቅ በግንባር ቀደምትነት እየሠራ መሆኑን የደህንነት መረጃዎች በግልጽ ያሳያሉ፡፡ ይህ የጠላትነት መንፈስ የገነነው በተለይ መንግሥት የባሕር በር ጥያቄን ያለጊዜውና ያለቦታው ማንሳቱን ተከትሎ ነው፡፡

የህወሓት ጉደይ በፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙለ እልባት ሳያገኝና በትግራይ በኩል ያለው ስጋት ሳይወገድ፣ የኤርትራን ሉዓላዊነት የሚነካ በሚመስል መልኩ የባሕር በር አጀንድን ወደ አደባባይ ማውጣታችን ሻዕቢያን የሚያህል ታሪካዊና ልምድ ያለው ጠላት በድጋሚ በላያችን ላይ እንዲቀሰቀስ አድርጓል፡፡

ሻዕቢያ አሁን ላይ የኢትዮጵያን የውስጥ ክፍተቶች በረቀቀ መንገድ እየተጠቀመ ይገኛል፡፡ በተለይም በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ኃይል በሎጂስቲክስ፣ በሥልጠናና በመረጃ በመርዳት የፌዳራልን መንግሥት ወታደራዊ አቅም እንዲዳከም እያደረገ ነው፡፡

ሻዕቢያ ፋኖን እንደ ስልታዊ አጋር በመጠቀም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የብልጽግናን መንግሥት የሚተካና ለኤርትራ ታዛዥ የሆነ ኃይል እንዲመጣ ግፊት እያደረገ ነው፡፡ ከዚህም በላይ፣ ሻዕቢያ ከሱዳኑ አልቡርሃን ቡድንና ከግብጽ ጋር በመቀናጀት ‹‹የሦስትዮሽ የከበባ ስሌት›› በመዘርጋት ኢትዮጵያን በቀጣናው ገለሌተኛ የማዴረግና የማዳከም ሰፊ ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡

የኤርትራ መሪዎች የብሌጽግና ፓርቲን አመራር እንደ ‹‹ታማኝ ያልሆነና ተለዋዋጭ›› አድርገው ስለሚቆጥሩት፣ ማንኛውንም ዓይነት ድርድርና ዲፕልማሲያዊ ግንኙነት ወደ ጎን በመተው ወደ ቀጥተኛና ኢቀጥተኛ ግጭት አምርተዋል፡፡

በመከላከያ አመራሮቻችን በኩል የሚሰነዘሩት ያልተመጠኑ ዛቻዎችና "ቀይ ባሕርን በኃይል እንቆጣጠራለን" የሚል ንግግሮች፣ ሻዕቢያ በትግራይና በአማራ ክልሌ የሚገኙ ፀረ-መንግሥት ኃይልችን እንዲያስታጥቅና እንዲያስተባብር ወርቃማ ዕድሌ ሰጥተውታል፡፡

ይህ ሁኔታ ሻዕቢያ ከቀድሞ ጠላቱ ህወሓት ጋር እንኳ ሳይቀር ‹‹የጋራ ጠላታችንን (ብሌጽግናን) እናስወግድ›› በሚል መርህ ምስጢራዊ ግንኙነት እንዲጀምር በር ከፍቷል፡፡

ሻዕቢያ ያለው ረጅም የሽምቅ ውጊያ ተሞክሮና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያለው ጥልቅ ሰርጎ፡ገብነት፣ ለሥርዓታችን መረጋጋት ትልቁ እንቅፋት ሆኗል፡፡ በመሆኑም ሻዕቢያን ከውስጥ አማፂያን ጋር የሚለጥፈውን የፖለቲካ መስመር ካልበጠስንና የባሕር በር ጥያቄውን በሰከነ ዲፕሎማሲ ካልመለስነው፣ የሻዕቢያ እጅ በሀገሪቱ እምብርት ድረስ ዘልቆ በመግባት የሥርዓቱን ውድቀት ሊያፋጥን እንደሚችል ሊታወቅ ይገባል፡፡


https://www.facebook.com/EritraAmazing/ ... 652488430/



Post Reply