Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Prosperity Party & EZEMA made electoral pact not to compete. PP won't field candidates to allow Ezema leaders win seats!

Post by sarcasm » 29 Mar 2026, 11:03

In politics, a pact not to compete—often called an electoral pact—is an agreement between two or more political parties where they decide not to field candidates against each other in certain constituencies. The goal is typically to avoid "splitting the vote" and to maximize the chances of defeating a common opponent.

Ethiopian Citizens for Social Justice (EZEMA) is an 'opposition' political party in Ethiopia founded in May 2019. It was formed through the merger of seven political parties, including the Patriotic Ginbot 7 and the Semayawi Party. EZEMA focuses on social justice and aims to foster a united, democratic Ethiopia.


ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ
የአዲስ አበባ ከተማ ካሉት 23 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በሦስት የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ። ብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎቹን ካላቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች ሁለቱ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ እና ምክትላቸው የሚወዳደሩባቸው ናቸው።
ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት ወር 24፣ 2018 በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ፤ አዲስ አበባን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለከተማይቱ ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎቹን የማስተዋወቂያ መድረክ ያካሄደው ከአንድ ሳምንት በፊት መጋቢት 3፤ 2018 ነበር። በከተማ ደረጃ ከተካሄደው ከዚህ መድረክ በኋላ የፓርቲው ዕጩዎች በየሚወዳደሩባቸው ክፍለ ከተሞች በመገኘት በተመሳሳይ መርሃ ግብሮች ሲሳተፉ ቆይተዋል።
ገዢው ፓርቲ ለዘንድሮ ምርጫ የአዲስ አበባ የፓርላማ መቀመጫ ካቀረባቸው 20 ዕጩዎች መካከል 16ቱ በስድስተኛው ዙር ምርጫ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ያልነበሩ መሆናቸውን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ፓርቲው ካሰራጫቸው መረጃዎች ተገንዝባለች። ከእነዚህ አዲስ የፓርላማ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱ ሚኒስትሮች ሲሆኑ ሦስቱ ደግሞ ሚኒስትር ዴኤታዎች ናቸው።
ከሚኒስትሮቹ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተመራጮች መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ይገኙበታል። በአዳዲሶቹ ተመራጮች ዝርዝር የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነሩ አቶ ደበሌ ቃበታ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተካትተዋል።
ለዘንድሮ የአዲስ አበባ የፓርላማ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ ዶ/ር ሳሙኤልን ጨምሮ ስምንት የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸውን ተወዳዳሪዎችን አቅርቧል። የሦስተኛ ዲግሪ ባለቤቶችን ለውድድር የማቅረብ አካሄድ፤ በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ የወቅቱ ገዢ ፓርቲ ተገዳዳሪ በነበረው የቅንጅት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ አባላት ከታየ በኋላ በሌሎችም ፓርቲዎች በስፋት ሲዘወተር ቆይቷል።

https://www.facebook.com/ethiopiainside ... qDs1g5VsSl