Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42716
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ ይህን የመሰለች የደስታ ሲቃ የምታሲዝ አገር ሆናለች! እኔ መላ ሕይወቴን ያደረኩት መስዋዕትነት ተመልሶልኛል!

Post by Horus » 22 Mar 2026, 18:50

ሕዝቦቼ ይህ እንዲሆኑ ነበር መላ ሕይወቴን ፖለቲካ ውስጥ ያጠፋሁት! አሚን :!: :!: :!: :!:

Last edited by Horus on 22 Mar 2026, 19:17, edited 3 times in total.


Naga Tuma
Member+
Posts: 7367
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ኢትዮጵያ ይህን የመሰለች የደስታ ሲቃ የምታሲዝ አገር ሆናለች! እኔ መላ ሕይወቴን ያደረኩት መስዋዕትነት ተመልሶልኛል!

Post by Naga Tuma » 23 Mar 2026, 05:09

Horus wrote:
22 Mar 2026, 18:50
ኢትዮጵያ ይህን የመሰለች የደስታ ሲቃ የምታሲዝ አገር ሆናለች! እኔ መላ ሕይወቴን ያደረኩት መስዋዕትነት ተመልሶልኛል!
Horus wrote:
22 Mar 2026, 18:50
ሕዝቦቼ ይህ እንዲሆኑ ነበር መላ ሕይወቴን ፖለቲካ ውስጥ ያጠፋሁት! አሚን :!: :!: :!: :!:
ኣዲሱ ኪዳኑ፣ ዛሬ ደግሞ አሙን ኣልክ?
ፕሮፌሰር ቃሎ በኖረበት ዘመን እየኖርክ?

ባለፉት ብዙ ዓመታት አረም እያልክ፣ ልንቀል እያልክ ስትለፋ ኖረሃል።

እየለፋህ ስትዋዥቅ፣ ለሃገር ጽናት ስትመከርም ኖረሃል።

የሃገር ጽናት ዋጋን እንደ አየር ጠባይ እና መርካቶ ሸቀጥ ስትቀያይርም ኖረሃል።

ዛሬ አሙን ያልክ የአሙን ደብዳቤ ሚዛናዊ መሆኑን ኣዉቀሃል?

በአሙን ከለላ ስር በሰበብ ኣስባቡ የሙሉ ህይወት ትግል ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በጥቂቱ፥

ኣፄ ቴዎድሮስ፣ ኣፄ ዮሓንስ፣ አቡነ ጴጥሮስ፣ ዘርዓይ ደረስ፣ ኣፄ ሀይለ ስላሴ፣ ጄነራል አማን ኣንዶም፣ ጄነራል ታደሰ ብሩ፣ ዶክተር ሀይሌ ፍዳ፣ ዶክተር ሰናይ ልኬ፣ ጄነራል ደምሴ ቡልቶ፣ ጄነራል ፋንታ በላይ፣ በዾ ደቻሳ፣ ባሮ ቱምሳ፣ ነዺ ገመዳ፣ ቡሪሶ ቦሩ፣ ሀየሎም አርዓያ፣ ከኤርትራ በረሃ እስከ ትግራይ ተራራ፣ ስንቶችን ታሪክ ይቁጠር።

ስ ህን አመኑ ያ ዱአ፣ ኢትዮጵያ ጣዖት ናት፣ ታቦት ጣዖት ነዉ ያለዉ ወዳጅህ እነዚህን ሁሉ ብያንስ በስም የማያዉቅ ኣይዴለም።

የሚገርመዉ የማይነጥፉ የአሙን ተዓምራት የተገለጡት በኣንተ በኩል ሳይሆን ለሃገር ጽናት ሰበበኛዉ መንግስቱ ሀይለማርያም ባሰራዉ ትምህርት ቤት በሉል መሆኑ ነዉ።

ethiopianunity
Senior Member
Posts: 10949
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ኢትዮጵያ ይህን የመሰለች የደስታ ሲቃ የምታሲዝ አገር ሆናለች! እኔ መላ ሕይወቴን ያደረኩት መስዋዕትነት ተመልሶልኛል!

Post by ethiopianunity » 23 Mar 2026, 09:07

ጦርነት በሱዳንና በአኢትዮዽያ ድንበር ተጀምሯል ይለናል አንዱ እውነት ከሆነ፣ ህዝብን ለማስተኛት ይሆን አላስፈላጊ ሽርጉድ አገርውስጥ በተለይ በአገራችን ጉረቤትና አጠገባችን አረብ አገራት ጦርነት እየተጧጧፈ እኛን የማይነካን ይመስለሀል?

Post Reply