Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42557
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የእጮር አቦ በቅዱሱ ምድር ምድረ ከብድ! ማየት ማመን ነው!

Post by Horus » 15 Mar 2026, 14:09

ታላቁ የምድረ ከብድ ገዳም ያባታችን ቅዱስ አቡነ ገብረ መንፈስ መካነ መቃብር ስለሆነ ይህ የእረፍታቸው ቀን መታሰቢያ ንግስ ነው! እስከ 1 ሚሊዮን ኣማኝ ይገኝበታል ። የክስታኔዎቹ አገር የሰላምና የፍቅር ምድር ነው! ለእኔ ደሞ የቅድመ አያቶቼ አገርና አጽም ያረፈበት ቦታ ነው! ምድረ ከብድ ቅዱስ ምድር ማለት ነው!

እጮር መጋቢት ማለት ነው! በሶዶ አቦ ባመት ሁለት ግዜ ይነግሳል! የጥቅምት አቦና የእጮር አቦ !


Horus
Senior Member+
Posts: 42557
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የእጮር አቦ በቅዱሱ ምድር ምድረ ከብድ! ማየት ማመን ነው!

Post by Horus » 15 Mar 2026, 14:37

ከምድረ ከብድ ገዳም 6 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኘው ጮቢ በአታ ለማሪያም ገዳም ደሞ ይህን ባሲሊካ ዘ ክስታኔ እየተገነባላት ነው! ይህ ካቴድራል ካፍሪካ 1ኛ ይሆናል እየተባለ ነው! በነገራችን ላይ አዳዲ ማሪያምን ፣ ዝቋላ አቦና ምድረ ከብድ አቦን በአባታችን የተገነቡት 1460ቹ ውስጥ ነው ። 3ቱም በ1530ቹ በግራኝ አህመድ ተቃጥለው አሁን ያሉት ህንጻዎች በምኒልክ ፣ ባልቻና ሃበተ ጎርጊስ ተመልሰው የተገነቡ ናቸው



Post Reply