Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Selam/
Senior Member
Posts: 17276
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

ቆምጬ

Post by Selam/ » Today, 10:01

ገራገሩ ቆምጬ እንደምን ከርመሃል
ስትፀልይ ከልብህ ወፎች ይሰሙሃል
ፎጣም ልበስ ቁምጣ ሁሉም ያምርብሃል
ግርማና እርጋታህ መንፈስን ያረካል
የምቀኛን ቅስም ይሰብራል ይገድላል
ጮማም ብላ ጥሬ ፈገግታህ ያስቀናል
ለአናሳ ጎጠኞች ደም ፍላት ይሰጣል
ሲመሽም ሲነጋም ስምህን ያነሱታል

Selam/
Senior Member
Posts: 17276
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ቆምጬ

Post by Selam/ » Today, 18:41


Axumezana
Senior Member
Posts: 18984
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ቆምጬ

Post by Axumezana » Today, 19:12

ቆምጬ ታታሪ ነው አገር ይቀልባል
አአ አትግባ ቢሉት በርግዶ ይገባል
አገር ነፃ አውጥቶ ፍትህን ያነግሳል
ናቂ ውዳቂ ነው ተቀምጦ ያገሳል
Last edited by Axumezana on 04 Mar 2026, 19:13, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 17276
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ቆምጬ

Post by Selam/ » Today, 19:13




Misraq
Senior Member
Posts: 17375
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: ቆምጬ

Post by Misraq » Today, 19:26

ቆምጬ ገራገሩ ያገር ጠባቂው
ረሃብ ቸነፈር ግፍ ያልበገረው
ቂምን የማይቋጥር መቻቻል ባህሉ
አግብቶ ተጋብቶ በሃገሩ ሁሉ
ሕዝብን አንድ አድርጎ በድንቅ ባህሉ
ይኖረው ነበረ በሃገሩ ሁሉ

Selam/
Senior Member
Posts: 17276
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ቆምጬ

Post by Selam/ » Today, 19:44

ደጉ ገራገሩ ፣ ቆምጬ ባላገሩ
ቢያጣ ቢገረጣ ፣ ፈገግታው ማማሩ
ዕኩል ሁሉን የሚያይ ፣ ስብዕናው ኩሩ
ጎጠኛ ሲንጫጫ ፣ ሲያፍር በሃገሩ
ባለ ቁምጣው ጎበዝ ፣ ጅንን ስመ ጥሩ




Last edited by Selam/ on 04 Mar 2026, 19:55, edited 1 time in total.

Selam/
Senior Member
Posts: 17276
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ቆምጬ

Post by Selam/ » Today, 19:52


Post Reply